መዝ 111:10 “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፥ ለሚያደርጓትም ሁሉ ደኅና ማስተዋል አላቸው ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል።”
The fear of the LORD is the beginning of wisdom; all who follow his precepts have good understanding. To him belongs eternal praise.
ምሳ 9:10 “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው።”
The fear of the LORD is the beginning of wisdom, and knowledge of the Holy One is understanding.
ምሳ 1:7 “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።”
“The fear of the LORD is the beginning of knowledge.”
ለምንድነው የጥበብ(የእውቀት) መጀመርያ እግዝአብሔርን መፍራት የሆነው?
እስቲ መጀመርያ እግዝአብሔርን መፍራት ማለት ምን ማለት ነው?
እኔ የገባኝን ላሰረዳ እናንተም ጨምሩበት…
እግዝአብሔርን መፍራት በሁለት አይነት መንገድ ልናየው እንችላለን:: የማያምኑ ወይም ያልዳኑ ሰዎች እግዝአብሔርን የሚፈሩት ከፍርዱ አንፃር ነው:: አማኞች ደግሞ እግዝአብሔርን የሚፈሩት መከበር መፈራት ያለበት አምላክ ስለሆነ ነው:: ለምሳሌ አጥፊ አስቸጋሪ የሆነ ልጅ አባቱን የሚፈራው እንዳይገረፍ እንዳይቀጣ ነው:: ነገር ግን ከአባቱ ጋር ጥሩ ግኑኝነት ያለው ጥሩ ፍቅር ያለው ልጅ አባቱን የሚፈራው እንዳይገረፍ ሳይሆን አባቱን ስለሚያከብር ስለሚወድ አና አባቱን ማሳዘን ስለማይፈልግ ነው:: ስለዚህ እግዘአብሔርን መፍራት በሁለት አይነት መንገድ ነው የምንረዳው::
ዕብ 12:28-29 እንዲህ ይላል “ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤ አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።”
ከእዚህ ጥቅስ የምንረዳው እግዝአብሔርን በማክበር እና በፍርሃት እሱን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ፀጋ መያዝ ያስፈለገበት ምክንያት ሲናገር “የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል…“ ይላል ስለዚሀ የአማኞች እግዝአብሔር መፍራት እና ያላመኑ ሰዎች እግዝአብሔርን መፍራት ይለያያል::
አሁን እየተወያየን ያለነው በአማኞች መካከል ስለሆነ ለእኛ ለአማኞች እግዝአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመርያ የሆነበት ምክንያት ምንድር ነው?
እኔ ሲገባኝ የምናመልከው አምላክ ማን መሆኑን በደንብ ካለወቅን ማለት ሁሉን ቻይነቱ ሁሉን አዋቂነቱን የሁሉንም ነገር መጀመርያ እሱ መሆኑን እኛም ምህረት ለማግኘታችን ለመዳናችን ምክንያት እሱ መሆኑን እንዲሁም ደግሞ እሱ ቅዱስ መሆኑን ፃድቅ መሆኑን ሃጥያአትን እንደሚጠላ ልብን ሁሉ እንደሚመረምር ግን ደግሞ ፍቅሩ መጨረሻ እንደሌለው ስናውቅ ልጁ እንዳደረገን ሲገባን ወራሾች እንዳደረገን ስንረዳ እና ሲገባን ያኔ ለእሱ የሚገባውን ክብር እንሰጣዋለን እንታዘዘዋለን የህይወታችን ጌታ አናደርገዋለን መመለክ እንደሚገባው እናመልከዋለን::
ለእዚህ ነው እግዝአብሔርን ማወቅ የጥበብ መጀመርያ የሆነው ብዬ አስባለሁ
ኦሪት ዘዳግም 10:12-13 “እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ አምላክህን እግዚአብሔርን ትፈራ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አምላክህንም እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ በፍጹምም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ ታመልከው ዘንድ፥ መልካምም እንዲሆንልህ ዛሬ ለአንተ የማዝዘውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሥርዓት ትጠብቅ ዘንድ ነው እንጂ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድር ነው?”

"ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፥ ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል። የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል። እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል...." ኢሳ.11፡1-3
እግዚአብሔርን መፍራት መንፈስ ነው። መንፈስ ደግሞ ሰዎች በራሳቸው ሊፈጥሩት የማይችሉት ከእግዚአብሔር ብቻ የሚወጣና የሚገኝ ነው። ልክ እንደ እግዚአብሔር ጽድቅና ቅድስና ሁሉ እግዚአብሔርን መፍራትም ሥጋና ደምን ከለበሰ ሰው ልብና ማነንት የሚወጣ ወይም የሚገኝ አይደለም። እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደዚህ ዓለም ሲልክ ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት የሚሆን ቤዛ እንዲሆን ብቻ ሳይሆን፤ የእግዚአብሔር ሕይወት የሆነው የጽድቅና የቅድስና ምንጭም አድርጎት ነው። እኛም ይህን አምነን ስንቀበል ክርስቶስ በእኛ ያለ የጽድቅና የቅድሰና፣ የጥበብና የማስተዋል... ምንጭ ይሆናል ማለት ነው። እግዚአብሔርን መፍራት የሚገኘውም ከዚሁ የሕይወታችን ምንጭ ከሆነው ከክርስቶስ ነው።
ክርስትና ከእግዚአብሔር አብ ከልጁም ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በመንፈስ ባለን ሕብረት የምንኖረው ኑሮ መሆኑ የታወቀ ነው። ክርስቶስ ከእርሱና ከአባቱ ጋር ያለንን ሕብረት ከገለጠበት መንገድ አንዱ የወይኑ ምሳሌ ነው። በዚህ ምሳሌ ላይ የወይኑ ባለቤት ወይም ገበሬው እግዚአብሔር አብ ሲሆን ወይኑ ደግሞ ክርስቶስና አካሉ የሆነው እኛ ነን። እርሱ ክርስቶስ የወይኑ ግንድ እኛ ደግሞ ቅርንጫፎች!! ለእግዚአብሔር አብ ክብር የሚሆነው የጽድቅ ፍሬ፤ ቅርንጫፎች በሆነው በእኛ ሊታይ የሚችለው ከግንዱ ጋር የተጣበቀ ሕብረትና ግንኙነት (Intimate fellowship) ሲኖረን ብቻ ነው።
"በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም" ዮሃ.15፡4
ክርስትና በእኔ ዓቅምና ጉልበት የምኖረው ሳይሆን፣ ክርስቶስ በእኔ የሚኖረው ሕይወት መሆኑ ከገባኝ ጊዜ ጀምሮ የጸሎት ርዕሴ አንድ ነው፤ "ጌታ ሆይ! በአንተ መኖርን አስተምረኝ!!" በእርግጥም በዚህ ክፉ ዘመንና ዓለም እግዚአብሔርን እየፈራንና እያከበርን እርሱንም ደስ እያሰኘን መመላለስ የምንችለው፤ በእርሱ በክርስቶስ መኖር ሲሆንልን ብቻ ነው!!

No comments:
Post a Comment