በNegussie Alemayehu T ተፃፈ።
*****************%********************
አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ለመረዳት ቀጥሎ ያሉትን ነገሮች ማወቅ ጠቃሚ ነው።
ከለመድነው አመለካከት መውጣት ላይመቸን ይችላል።
መጽሐፍ ቅዱስ ሐሳቡ የእግዚአብሔር፣ ቋንቋው ግን የሰው ነው። የተጻፈው ለሰው ነው። የሚያነበውም ሰው ነው። የሚያነበው ሰው ደግሞ እንዲገባው ያስፈልጋል።
ላንዳንዱ አማኝ መጽሐፍ ቅዱስ በማይገቡ ነገሮችና ውስብስብ አባባሎች የተሞላ፣ ላንዳንዱ ደግሞ አንድ ትልቅ የእንቆቅልሽ ወይም የተወሳሰበ መጽሐፍ ነው።
ግን አይደለም።
እንዲህ ስል የመጽሐፍ ቅዱስን ዋጋ ማሳነሴና ዝቅ ማድረጌ አይደለም።
1፠ Simile ሲምሊ
በዙሪያችን ካሉት ከምናውቃቸው ነገሮች በመነሳት አብዛኛውን ጊዜ "እንደ" እና "ይመስል" የሚሉ ቃላትን በመጠቀም ኃሳባችንን የምንገልጽበት ዘይቤ ነው።
ወንድሜኮ ሲበላ እንደ ጅብ ነው። እሷ ደግሞ እስስት ይመስል ትለዋወጣለች።
የሁለቱም አጠቃቀም ግልጽ ነው። ለማለት የተፈለገውን ለመረዳት በጣም ቀላል ነው።
መጽሐፍ ቅዱስም በዚህ አጠቃቀም የተሞላ ነው።
"ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ። "
(ኢዮ 23)
(ኢዮ 23)
፠ተስፋ የሌለው ሰው ንግግር እንደ ነፋስ ነውና
፠ "የአሕዛብን አንበሳ መስለህ ነበር፥ ነገር ግን እንደ ባሕር ዘንዶ ሆነሃል፤። "(ሕዝ 32:2)
2፠ Metaphor ሜታፎር
ይህኛው አጠቃቀም "እንደ" እና "ይመስል" የሚሉትን ቃላት በፍጹም አይጠቀምም። እንደ ብሎ ከመናገርና ከማመሳሰል ይልቅ በቀጥታ የተወከለውን ነገር ይጠቀማል።
ለምሳሌ እንትናኮ ሲበላ "እንደ" ጅብ ነው ከማለት በቀጥታ እንትና እኮ ጅብ ነው እንላለን። ጅብን በሆዳምነቱ ስለምናውቀው ተናጋሪው ምን ማለት እንደፈለገ ይገባናል። ይህ ዘይቤ ከመጀመሪያው ዘይቤ ይልቅ ኃሳብን የበለጠ ይገልጻል።
ተለዋዋጭ ባሕሪ ያለውን ሰው እስስት ይመስል ትለዋወጣለህ ከማለት በቀጥታ እስስት ነህ እንላለን። ንቁ የሆነውን ቆቅ ፣ ደፋሩንና ጀግናውን አንበሳ፣ የዋሁን ደግሞ በግ ነው ማለት የተለመደ ነው። በነገራችን ላይ የግድ እንስሳትን ብቻ እንጠቀማለን ማለት አይደለም።
ለምሳሌ ሜታፎርን በመጠቀም በቀጥታ "ቃሉ ሰይፍ ነው" ስንል ምን ማለታችን ነው ? እንደ ሰይፍ ነው ማለትም ስህተት አይደለም።
መጽሐፍ ቅዱስ እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ ፣ እናንተ ጨው ናችሁ ሲል የሜታፎር አገላለጽ ነው።
3፠ Personification ፐርሶኒፊኬሽን
ለግዑዝና ለማይታዩ ነገሮች ልክ እንደ ሰው የሰውን ባሕሪ ሰጥተን እንደ ሰው እናናግራቸዋለን።
የሆንኩትን ነገር ይቺ ቤት ትመስክር፣
ብርዱ በጥፊ አለኝ፣
ድህነት በአገሪቱ ላይ እግሮቹን አንፈራጦ ተቀምጧል።
ስንት ጀግኖች እንደተሰዉ ይሄ ሐውልት ይናገር።
ብርዱ በጥፊ አለኝ፣
ድህነት በአገሪቱ ላይ እግሮቹን አንፈራጦ ተቀምጧል።
ስንት ጀግኖች እንደተሰዉ ይሄ ሐውልት ይናገር።
መጽሐፍ ቅዱስም በዚህ አጠቃቀም የተሞላ ነው።
፠ጥበብ በጎዳና ትጮኻለች፤ በአደባባይ ድምፅዋን ከፍ ታደርጋለች። ( ምሳሌ 1:20)
፠ጥበብን አንቺ እኅቴ ነሽ በላት፥ማስተዋልንም ወዳጄ ብለህ ጥራት፥ " (ምሳ 7:4)
4፠ Hyperbole ሀይፐርቦሊ
ለምንናገረው ነገር ክብደት ለመስጠት አንድን ሐሳብ እጅግ በማጋነን በንግግርና በጽሑፍ የምንጠቀምበት የንግግር ዘይቤ ነው። አንባቢውም ሆነ ሰሚው ያንን የተጋነነ ነገር እንደ እውነት አድርጎ አይቀበለውም።
ለምሳሌ "ሰውዬው ሲያስፈራ ብታየው እኮ፣ ተራራ ያክላል።" ስንባል "ባክህ ተራራ የሚያክል ሰው የለም። " ብለን አንከራከርም።
ይህ አጠቃቀም በመጽሐፍ ቅዱስ፦
፠ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ፥ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ።" (መዝ 6:6)
፠ ዘርህንም እንደ ምድር አሸዋ አደርጋለሁ።"( ዘፍ 13:16)
፠ ኢየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸውም ይመስለኛል።" (ዮሐ 21:25)
፠ እግዚአብሔርስ ከወደደን ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ወደዚች ምድር ያገባናል እርስዋንም ይሰጠናል። " (ዘኍ 14:8)
5፠ Apostrophe አፖስትሮፊ
ግዑዙን ወይም የማይታየውን ነገር እንደሰው በቀጥታ ስናናግረው apostrophe ይባላል።
Personification እና apostrophe የተቀላቀሉ አድርገን እንዳንወስዳቸው። ለምሳሌ ሞት መውጊያው ተሰበረ ስንል personification ነው።
ሞትን ግን እንደ ሰው ወስደነው እና ልክ እንደ ሰው ቆጥረነው " ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ? " ስንል apostrophe ይሆናል።
6፠ interrogation ኢንተሮጌሽን
ይህ የንግግርና የጽሑፍ ዘይቤ በጥያቄ መልክ ይቀመጣል ።
ሐብታም ስለሆነ ሕጉ አይመለከተውም ማለት ነው? ይመለከተዋል።
አስተማሪ ስለሆነ ሁሉንም ነገር ያውቃል ማለት ነው? አያውቅም።
መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ አይነቱ የአጻጻፍ ዘይቤ የተሞላ ነው።
፠በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? መልሱ ይታወቃል። የለም ነው።
፠እግዚአብሔርም መለሰ ኢዮብንም እንዲህ አለው። በውኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር ይከራከራልን?
7፠ irony አይረኒ
irony የሚለው ቃል ምጸት ከሚለው የአማርኛ ቃል ጋር ተቀራራቢ ትርጉም ይኖረዋል። በዚህ የአጻጻፍና የንግግር ዘይቤ ተናጋሪው ማለት የፈለገው ተቃራኒውን ነው። ተናጋሪው ያን ነገር ለምን እና በምን መንፈስ እንዳለው እንረዳለን።
የምጸት አነጋገር ንዴትን፣ ማሾፍን ፣ ቅር መሰኘትን እና ማላገጥን ሊገልጽ ይችላል። ምጸት በንግግር ብቻ ሳይሆን አንዳንድ ጊዜ በድርጊትም ሊገለጽ ይችላል።
አንዲት እናት አላጠናም እያለ የሚያስቸግራት ልጇን በፈተና ወድቆ ሲመጣ "ጎሽ የኔ ልጅ አሁንም በዚሁ ቀጥል!" ብትለው ወይም ትከሻውን መታ መታ ብታደርገው ደስታዋን እየገለጸች አይደለም።
ወይ ደግሞ " እሷኮ ታላላቆቿን አታከብርም እንጂ በጣም ጨዋ ልጅ ናት" ስንል irony ወይም ምጸትን እየተጠቀምን ነው።
ለምሳሌ እግዚአብሔር የእስራኤል ሕዝብ ጣዖትን እንዲያመልኩ ያበረታታ ነበር?
፠ ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ሂዱ፥ ከዚህም በኋላ ትሰሙኝ ዘንድ ባትወድዱ ሁላችሁ ጣዖቶቻችሁን አምልኩ። "( ሕዝ 20:39)
ሌሎች ምሳሌዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ፦
፠ምናምንቴዎች እርቃናቸውን እንደሚገልጡ የእስራኤል ንጉሥ በባሪያዎቹ ቈነጃጅት ፊት እርቃኑን በመግለጡ ምንኛ የተከበረ ነው! አለችው። " (2ኛሳሙ 6:20)
፠አምላክ ነውና በታላቅ ቃል ጩኹ፤ ምናልባት አሳብ ይዞታል፥ ወይም ፈቀቅ ብሎአል፥ ወይም ወደ መንገድ ሄዶአል፥ ወይም ተኝቶ እንደ ሆነ መቀስቀስ ያስፈልገዋል እያለ አላገጠባቸው።" (1 ነገ 18:27)
፠የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ እጅ ይነሱት ጀመር፤ ራሱንም በመቃ መቱት ተፉበትም፥ ተንበርክከውም ሰገዱለት። (ማር15፡18)
8፠ synecdochy ሲኔክዶኪ
ይህኛው አጠቃቀም፦
1ኛ፦ አንድ ግሩፕ ፣ ቡድን ፣ ሕዝብ ወይም ሕብረት ሙሉውን እንዲወክል ተደርጎ በአንድ ቃል ወይም መጠሪያ ሲነገር
ለምሳሌ፦
፠ኢትዮጵያ በስብሰባው ላይ እንደማትገኝ አስታወቀች።
፠አሜሪካ ኮርያን አስጠነቀቀች።
፠ኮሌጁ በዚህ አመት አዲስ ተማሪዎችን እቀበላለሁ አለ።
፠ባንኩ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ አተረፍኩ አለ።
፠ድርጅቱ አንድ መቶ ሰራተኞችን አባረረ።
፠አሜሪካ ኮርያን አስጠነቀቀች።
፠ኮሌጁ በዚህ አመት አዲስ ተማሪዎችን እቀበላለሁ አለ።
፠ባንኩ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ አተረፍኩ አለ።
፠ድርጅቱ አንድ መቶ ሰራተኞችን አባረረ።
ምሳሌዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ፦
፠ሊባኖስ አፈረ ጠወለገም፤ " (ኢሳ 33:9)
፠ . . . ምድሪቱም በራብ አትጠፋም። " (ዘፍ 41:36)
፠ ኢየሩሳሌም እጅግ ኃጢአት ሠርታለች፤ ስለዚህ ረክሳለች፤"
(ሰቆ ኤር 1:8)
(ሰቆ ኤር 1:8)
፠ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግዚአብሔርን አመስግኚ፥ (መዝ 147፡12)
፠እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል።"(መዝ 14:10)
፠ ጽዮንም ሆይ፥ ለአምላክሽ እልል በዪ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፥ ልጆችንም በውስጥሽ ባርኮአልና። (መዝ 147፡13)
፠ እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ።" (ማቴ 18:17)
9፠ context አውድ
ስለ context ወይም ስለ አውድ ሲነሳ ቁጣ ቁጣ አይበላችሁ። እንዲህ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባሉት ጥቅሶች ቁጥር ልክ ቤተ ክርስቲያናት እንደሚኖሩ ጠብቁ።
አውድ ቲዎሎጂ ለተማሩ ብቻ የተለቀቀ አይደለም። ያለ አውድ የትኛውም ጽሑፍ፣ የትኛውም ንግግር፣ የትኛውም ስብከት ዋጋ ቢስ ነው። ነውርም ነው።
አውድ ምንድነው?
አውድ ማለት ሌላ ትርጉም የለውም። ተናጋሪው ለማለት የተፈለገው ምንድነው ነው።
የአንዱን ጥቅስ ሐሳብ ለመረዳት ሙሉ ምዕራፉ ስለምን እንደሚያወራ ማንበብና መረዳት የግድ ነው። ከዚህ ውጪ በጋለ ስሜትና ጩኸት ከአውዱ ውጪ ቢሰበክ ለጊዜያዊ ሙቀት ይረዳ ይሆናል።
አንዷን ጥቅስ መዞ በማውጣት "የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ" የሚለው ለማርያም ነው ለሚሉኝ ወዳጆቼ ሙሉ ምዕራፉን አንብቡት ነው የምለው።
አንዳንድ ጊዜ ውስጣችን እያወቀው ይሁን ባለማወቅ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ያላለውን ለማስባል ስንታገል ፣ በተለይ እኛ የምናምነውን የሚደግፍ ከመሰለን አይናችንን አናሽም።
አከራካሪ ጉዳዮች የሉም አላልኩም። ፍጥጥ ብሎ የተቀመጠውን ጉዳይ ግን ላለማየት አይን መጨፈን ይቅር።
ያኔ ብንሳሳት ምንም አይደለም። አቤቱ በልቤ ቅንነት ይህን አደረኩት ብንል ይሰማናል።
ተባረክ ወንድሜ አገላለጽክ ደስ ይላል ከዚህም በላይ እውቀቱን ይጨምርልህ Wkasahun01@gmail.com
ReplyDelete