Saturday, May 26, 2012

Trinity in Amharic Part 1


እግዝአብሔር

መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረን እግዝአብሔር አንድ አምላክ ነው። ይኸው መፅሐፍ ቅዱስ ደግሞ ይህንን አንድ አምላክ በአንድ ጊዜ ሦስት ዘላለማዊ ሰብዕና (personality) (መንፈሳዊ አካል) እንዳለው ያስተምረናል። እኛ ክርስትያኖች ይህንን መረዳት ሥላሴ ብለን እንጠራዋለን።

ሥላሴ ምንድር ነው? አመጣጡስ?

ሥላሤ የሚለው ቃል የሚያሳየው በክርስትና እምነት መሰረት አንድ አምላክ ሦስት ሰብዕና(personality)ያላቸውን ህብረት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ሦስትም አንድ ናቸው፤ አንድም ሦስት ናቸው። እዚህ ላይ መጠንቀቅ ያለብን 1/3+1/3+1/3=3/3(1) ማለት አይደለም። እያንዳንዱ ሰብዕና(personality) ከሌላው ይለያል ግን ድግሞ በማንነታቸው አንድ ናቸው። በሌላ አነጋገር እያንዳንዱ በራሱ ሙሉ መለኮት ነው ግን ደግሞ አንዱ ሰብዕና ሁሉንም ይወክላል ማለት አይደለም። እያንዳንዱ ፈቅራል እንዲሁም እያንዳንዱ “እኔ” “እሱ” የሚለውን አነጋገር ይጠቀማል እንዲሁም ደግሞ እያንዳንዱ ዕውቀት ስሜት አለው። እያንዳንዱ መለኮት ነው፡ ግን ሶስት አማልክት ሳይሆን አንድ አምላክ ነው ያለው። አንድ አምላክ በሶስት ሰብዕና ይገለጻል፣ እሱም  አብ፡ ወልድ፡ መንፈስቅዱስ። አብ አምላክ ከተባለ (ፊሊ 2፡11፣ዮሐ 6:27፣ ኤፌ 4:6፣ 1 ጴጥ 1:2) እሱ ያ አንድ አምላክ (ይሆዋ) ነው፤ ወልድ አምላክ ከተባለ (ቲቶ 2፡13; 2ጴጥ 1፡1; 1ዮሐ 5፡20; ዮሐ 1፡1፣ 18; ዮሐ 20፡28) እሱ ያ አንድ አምላክ (ይሆዋ) ነው፤ መንፈስ ቅዱስ አምላክ ከተባለ (ሐዋ 5፡3-4፤ 2 ቆሮ 3፡17) እሱ ያ አንድ አምላክ (ይሆዋ) ነው። ግን አምላክ አንድ አምላክ ነው ( 1ቆሮ 8፡5-6; ገላ 4፡8; 1ጢሞ 1፡17; ዮሐ 5፡44; 17፡3; ኢሳ 43፡10-11; 44፡6፣ 8; 46፡9) ። ሦስቱም አይሽቀዳደሙም ሦስቱም አይበላለጡም።

ሥላሴ በግሪኩ ትሪያስ (trias) ይባላል ትርጉሙ ሦስት እጥፍ ወይም የሦስት ሰው ቡድን እንደማለት ነው። በ175 ዓ.ም ላይ ትዎፍሎስ ይህን ቃል መጠቀም ጀመረ። በላቲን ደግሞ ትሪኒታስ (trinitas)ይባላል። ትርጉሙ ትራይ (tri) ሦስት ማለት ሲሆን ዩኒታስ (unitas) ደግሞ ህብረት ማለት ነው። ይህን ደግሞ ጠርጡልያን በ210 ዓ.ም መጠቀም ጀመረ። ትሪኒቲ (trinity)ለሚለው የእንግሊዘኛ ቃልም መሠረት ነው።

ቃል ሥጋ ከመልበሱ በፊት አንድ ሰብዕና ነበር የነበረው ሥጋ ከለበሰ በኋላ ተጨማሪ የሰው ሰብዕና ጨምሯል። አንድ ቢሆንም የነበረው ግን ሁለት ተፈጥሮ ነበር። ግማሽ ሰው ግማሽ አምላክ ሳይሆን ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ነበር። በአምላክ ማንነቱ ከአብ ጋር እኩል ሲሆን በሰው ማንነቱ ደግሞ ከአብ ያንስ ነበር። ስለዚህም በአብ ፈቃድ ራሱን ፍፁም አስገዝቷል። 

የመጀመርያዎቹ ክርስትያኖች ስለእግዛብሔር ከይሁዲ (Judaism) እምነት ያላቸውን መረዳት በእየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት ሞትና ትንሳዔ ከዛም በመንፈስ ቅዱስ መሰጠት የተነሣ እንደገና እንዲያስተውሉ አሰገድዶአቸዋል። እንደ ይሁዲነታቸው አንድ አምላክ ብቻ እንዳለ አምነዋል ይህም ደግሞ በእየሱስ ክርስቶስም ትምህርት ተረጋግጦላቸዋል።(ማቴ 12፡29-32፣ 1 ቆሮ 8፡4፣ ኢፌ 4፡6፣ ወዘተ…)ይሁን እንጂ በመንፈስ ቅዱስ ብርሃንነት በተለያየም ጊዜ ስለእየሱስ አምላክነት(እግዛብሔርነት)(Theos በግሪክ)አምነው ፅፈዋል፤ ተናግረዋል(ዮሐ 1፡1,ዮሐ 20፡28,ዕብ 1፡8)። እንዲሁም ጌታ(The Lord)(በብሉይ ኪዳን ይሆዋ ይጠራበት የነበረውን የራሱን ማዕረግ) ከ200 ጊዜ በላይ ለእየሱስን ተጠቅመውበታል። ከዚህ ከሐዋርያት የአዲስ ኪዳን መልዕክት እንደምንረዳው እግዛብሄር ባለ ሦስት ሰብዕና ነው። 

ሥላሤ የሚለውን ቃል አንድም ቦታ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ አናገኘውም። ታዲያ የዚህ ቃል አለመኖር በራሱ ሥላሤ የሚባል ነገር የለም ማለት ያስችለናል? በክርስትና እምነት ብዙ ጊዜ ሃሳብን ለመግለፅ የምንጠቀምባቸው ቃላቶች አሉ። ለምሳሌ ምፅአት(rapture) ትዮኦክራሲ(Theocracy) ኢስካቶሎጂ(eschatology) ወዘተ የመሳሰሉትን ብዙ የተለያዩ ቃላቶች እንጠቀማለን ግን አንድም ቦታ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አናያቸውም ይኽ ማለት ግን እነሱ ሚገልፁት ነገር የለም ማለት አይደለም። እንዲሁም ደግሞ እኛ ክርስትያኖች ስለእግዝአብሔር ሁሉን አዋቂነት ለመግለፅ በእንግሊዘኛው “omniscientእንላለን። ይህንን ቃል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አናገኘውም ይህ ቃል አለመኖሩ ግን እግዝአብሔርን ሁሉ አዋቂ አለመሆኑን አያሳይም። ስለዚህ ይኽን የመሳሰሉ ቃላቶች አንድን ሃሳብ መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚናገረውን ለመግለፅ የምንጠቀምበት አጠቃላይ(general) የሆኑ ቃላቶች ናቸው። ይህም ባጭሩ አንድን ሐሳብ የምንገልፅበት መንፈሳዊ ቃል (Theological shorthand) ይባላል።

አንዳንዶች ሥላሤ የሚለው ትምህርት የመጣው ከአለማውያን (የጣኦት) እምነት ነው ይላሉ። ግን የእግዝአብሔር ቃል እንደሚነግረን ሰይጣን እውነተኛውን እያስመሰለ እንጂ የሚያታልለን በሌለ ነገር ብዙ ጊዜ አያታልለንም። ለምሳሌ በአለማውያን አምልኮ ታሙዝ የተባለ መሲህ ሞቶ እንደተነሳ እምነት አለ። ልክ እንደጥፋት ውኀ አይነትም ታሪክ አለ እንዲሁም ደግሞ እንደሥላሤ አይነትም ትምህርት አለ ትንሽ ለወጥ በማድረግ። ይህ ምንም አያስገርምም። ለምሳል በዚህን አለም የቀን ተቀን ኑሮ እንኳን የሐሰት ብሮች አሉ። ለምሳሌ የሐሰት መቶ ብር አለ ልክ የእውነተኛውን መቶ ብር የሚመስል። ግን ልብ ብለን ከሆነ ለምሳሌ የሀሰት የሰባ ብር ኖት የለም ምክንያቶም እውነተኛ የሰባ ብር ኖት ስሌለለና ሰውም በዚህ ስለማይታለል። በዚህ አተያይ ካየነው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሚመስል በጣዖት አምልኮ ውስጥ ቢኖር ምንም የሚያስገርም ነገር አይደለም።

ስላሤ ሚስጥር ነው?

1 ጢሞ 3፡16 “…የእውነትኛ መንፈሳዊ ሕይዎት ምስጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው…” በርግጥ የእግዝአብሔር ነገር በተገለጠልን መጠን እንጂ እጅግ በጣም ጥልቅና ከእኛ አእምሮ በላይ ነው። ስለዚህ እግዝአብሔር ራሱን በገለጠልን መጠን እንረዳዋለን። ቃሉ የማይለውን ላለማለት በጣም መጠንቀቅ አለብን። እዚሁ ቦታ ወረድ ብሎ 1ጢሞ 4፡1 “በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች እምነትን ክደው አታላይ መናፍስትና የአጋንንትን ትምህርት እንደሚከተሉ መንፈስ በግልጥ ይናገራል” ይላል። ስለዚህ ይህን የሥላሤ ትምህርት ከመጽሐፍ ቅዱስ ድጋፍ ካላገኘን የአጋንንት ትምሕርት ነው መጽሓፍ ቅዱስ የሚደግፈን ወይም የሚያስተምረን ከሆነ ደግሞ አለማመን የአጋንንትን ትምህርት መከተል ነው።

ስላሤን የሚቃወሙ ክፍሎች ሥለሤን በተመለከተ ሲናገሩ ግራ የሚያጋባ ነገር ስለሆነ የሥላሤ ትምህርተ ከእግዝአብሔር አይደለም ይላሉ። ምክንያታቸውም በ1ቆሮ 14፡33 ላይ እንዳለው “እግዝአብሔር የሰላም አምላክ እንጂ የሁከት አምላክ አይደለም።” ሥላሤም ግራ የሚያጋባ ነገር ስለሆነ ከአምላክ አይደለም ይላሉ። ግን የዘላለም የሆነውን አምላክ በእዚች ትንሽ ወይም ውስን በሆነችው መረዳታችን ሙሉ ለሙሉ መረዳት ስላልቻልን ሥላሤ የስህተት ትምህርት ነው ማለት አይደለም። ሥላሤን ስህተትም ሆነ ትክክል የሚያረገው የእግዝአብሔር ቃል ነው። የእግዝአብሔር መጀመርያ መቼ ነው ከየትስ መጣ? ይህን ልንረዳውም ሆነ ልናውቀው አንችልም ግን ቃሉ በመዝ 90፡2 እንደሚል “ገና ተራሮች ሳይወለዱ፣ ምድርንና ዓለምን ከመፍጠርህ በፊት፣ አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነህ።” ስለዚህ እግዝአብሔር ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነው ስለሚለን ቃሉ እኛም እምነት ከመስማት ነው መስማትም ከእግዝአብሔር ቃል ነው ብለን አሜን ብለን እንቀበላለን እናምናለንም። እንግዲህ ሰው ሊረዳው ከሚችለው በላይ ነው ብለን ውስን በሆነው መረዳታችን ሙሉ የሆነ መረዳት ካላገኘን የስህተት ትምህርት ነው ማለት አንችልም። 1 ቆሮ 13፡12 ላይ ጳውሎስ ሲናገር “…አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ እኔ ራሴ ሙሉ በሙሉ የታወቅሁትን ያህል ዐውቃለሁ።” 


ሥላሴን ስናጠና በሁለት ከፍለን እናጠናዋለን። ontological trinity economical trinity
  1. Ontological trinity የሚያተኩረው በአንድ አምላክ ማንነት ምንነት ላይ ያተኮረ ሲሆን
  2. Economical trinity ደግሞ ከሥራቸው ድርጊት ጋር የተያያዘ ነው።

Ontological trinity
አንድ እውነትኛ አምላክ አለ

ምንም እንኩዋ ስለእግዛብሄር ውሱን ዕውቀት ቢኖረንም መጽሓፍ ደግሞ ደጋግሞ የሚነግርን ተጨባጭ እውነት (FACT)”እግዛብሄር አንድ አምላክ ነው”
ኢሳ 43፡10-11,13 እንዲህ ይላል “…ከእኔ በፊት አምላክ አልተሰራም ከእኔም በሁኋላ አይኖርም። እኔ፡ እኔ እግዛብሄር ነኝ ከእኔ ሌላ የሚያድን የለም። …ከጥንት ጀምሮ እኔው ነኝ…”
ኢሳ 45፡5,22 ይህን ሐሳብ ሲያጠናክር “እኔ እግዛብሔር ነኝ፣ ከእኔ ሌላ ማንም የለም፣ ከእኔ በቀር አምላክ የለም …እኔ አምላክ ነኝ፡ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና፡ ትድኑ ዘንድ ወደኔ ተመለሱ።”

ኢሳ 46:9፣ ዘዳ 6:4 ላይም እግዝአብሔር አንድ ስለመሆኑ ይናገራል።

እነዚህ ከብዙ በጥቂቱ በብሉይ ኪዳን የተነገሩ ሲሆን በአዲስ ኪዳን ደግሞ ገላ 3፡20 “…እግዛብሄር ግን አንድ ነው።” እንዲሁም ያቆ 3፡19 “አንድ እግዛብሄር እንዳለ ታምናለህ፡ መልካም ነው፡…”  እንዲህ እያልን ብዙ መጥቀስ ይቻላል  ለማጠቃለል ያህል ግን እግዛብሄር አንድ አምላክ ነው።


1 ጢሞ 2፡5 “አንድ እግዝአበሔር አለና….”  1 ቆሮ 8፡4 “…ከአንዱ ከእግዛብሔር በስተቀር ሌላ አምላክ እንዴሌለ እናውቃለን።”

እንግዲህ አብ አምላክ ከተባለ እሱ ያ አንድ አምላክ ነው። ወልድ(ልጅ) አምላክ ከተባለ እሱ ያ አንድ አምላክ ነው። መንፈስ ቅዱስ አምላክ ከተባለ እሱ ያ አንድ አምላክ ነው።

ዘዳ 6፡4”እስራኤል ሆይ ስማ፡ አምላካችን እግዝአብሔር አንድ (echad) እግዝአብሔር ነው።”  ይህ ስፍራ የሚያሳየን እግዝአብሔር አንድ አንደሆነ ነው። ግን አንድ ለሚለው ቃል በዕብራይስጥ (echad) የሚል ቃል ነው የተጠቀመው ይህ ቃል ደግሞ የሕብረት አንድነት ሊሆን ይችላል(compound unity)።

ለምሳሌ ዘፍ 1፡5 ሌሊቱንና ቀኑን በአንድነት አንድ (echad) ቀን ብሎ ጠራው።
ዘፍ 2፡24 ባልና ሚስት አንድ (echad) ስጋ ይሆናሉ ይላል።
ዘፍ 11፡6 “እግዝአብሔር እንዲህ አንድ (echad) ሕዝብ አንድ ቋንቋ በመናገር ይህን…” የብዙ ሰዎች ጥርቅም አንድ ሕዝብ ይሆናል።

እዝ 3:1 ፣ 1 ዜና 12:38 (echad)

ይህን ስናይ አንድ(echad)እግዝአብሔር ሲል ሌላ ቦታ የሚደግፈን ነገር ካለ የህብረት አንድነት ሊሆን ይችላል። በእርግጥ አንድ በሚለው ቃል በዕብራይስጡ “echad”ፋንታ “yachid”(absolute singular or uniqueness) ቢሆን ኖሮ የተጠቀመው የህብረት አንድነት ማለት አንችልም ነበር።

ዘፍ 22፡12 “…እግዝአብሔርን እንደምትፈራ ተረድቻለሁ፡ልጅህን፣ ያውም አንዱን (yachid) ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሳሳህምና። አለው።” ይስሐቅ የአብርሃምና የሳራ (የተስፋው) አንድያ ልጅ ነው። ሌላ የተስፋው ልጅ የላቸውም።

ዘካ 12:10 (yachid)

ኤር 6:26 (yachid)

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ቦታ ይህ yachid የሚለውን የግሪክ ቃል ከእግዝአብሔር ጋር ተያይዞ አናየውም። እግዝአብሔርን ነጠላ (absolute singular) ማንነት አልተጠራም አልተገለጸም።

በመጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ ሌላስ አምላክ ብለው የተጠሩስ?

መጽሓፍ ሌሎች አምላክ ተብለው የተጠሩ እንዳሉ ይነግረናል። እነሱ ግን በተፈጥሮአቸው (በባሕርያቸው) አምላክ አይደሉም። ገላ 4፡8 “እግዝአብሔርን ከማወቃችሁ በፊት፡ በባህርያቸው አማልክት ላልሆኑት ባርያዎች ነበራችሁ”

እንዲሁም አማልክት (በብዙ ቁጥር) ወይም አምላክ (በነጠላ ቁጥር) ተብለው የሚጠሩ ግን ሰማይና ምድርን ያልፈጠሩ ይጠፋሉ ይለናል የእግዛብሔር ቃል። ዘካ 10፡11 “እናንተም፣ እነዚህ ሰማያትንና ምድርን ያልፈጠሩ አማልክት ከምድር ላይ፣ ከሰማያትም በታች ይጠፋሉ ትሏችዋላችሁ።”

በባሕርይ (በተፈጥሮ) አንድ አምላክ ብቻ ነው ያለው፡ ሌሎቹ በባሕርይ (በተፈጥሮ) አምላክ አይደሉም ። 1 ቆሮ 8፡5-6”መቼም ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች አሉ፡ በስማይም ሆነ በምድር አምላክ ተብለው የሚጠሩ አማላክት ቢኖሩም፡ ለእኛ ግን ሁሉም ነገር ከእርሱ የሆነ፡ እኛም ለእርሱ የሆን አንድ አምላክ አብ አለን፡ ደግሞም ሁሉም ነገር በእርሱ አማካኝነት የሆነ፡ እኛም በእርሱ አማካኝነት የሆን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።”

እዚህ ላይ ስናስተውል ሌሎች አምላክና ጌታ ተብለው የሚጠሩ ቢኖሩም ያለው እውነተኛ አንድ አምላክና እውነተኛ ጌታ አንድ ነው።

*እዚህ ጋር አንድ አምላክ አብን ብቻ እየሱስን ደግሞ ጌታ ብቻ ሲል እነሱ ብቻ መለኮት ናቸው ብሎ ከሌሎች ጣዖታት ጋር እያወዳደረ ነው እንጂ አብ አምላክ ነው ጌታ አይደለም ወይም ደግሞ እየሱስ ጌታ ብቻ ነው አምላክ አይደለም ነው የሚለው ካልን ከሌላ የእግዛብሔር ቃል ጋር ይጋጭብናል ። አብ ጌታ ተብሏል (ማቴ 11፡25ላይ በሌላም ቦታ)፤ እየሱስም አምላክ ተብሏል (ዮሐ 1፡1,ቲቶ 2፡13,ሮሜ 9፡5, 2ጴጥ 1፡1 ላይ በሌላም ቦታ) ። በተለይ በአንድ አይነት ሐሳብ(ታሪክ) ላይ የሚናገረውንና አንዱ ቦታ ጌታ፤ አንዱ ቦታ ደግሞ እግዛብሔር እንዴት አየለዋወጠ እንደተጠቀመባቸው  ማር 5፡19(ጌታ) እና ሉቃ 8፡39(እግዛብሔር) እይ ። እየሱስም ጌታም አምላክም አንድ ላይ ዮሐ 20፡28 ላይ ተብሎአል። እግዛአብሔር አብም ራዕ 4፡11 ላይ “ጌታችንና አምላካችን ሆይ…” ተብሎአል።1ቆሮ 7፡17 ላይም ጌታና እግዛብሔር ባንድ ሃሳብ ተጠቅሰዋል “ብቻ እያንዳንዱ ሰው ጌታ እንደወሰነለት፣ እያንዳንዱም እግዛብሔር እንደጠራው በዚያው ይመላለስ:”። አንዳንዴ ሐዋ 2፡36 በመጥቀስ ”እንግዲህ፣ እግዛብሔር ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን እየሱስን፣ ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ ይረዳ” እየሱስ ከትንሳኤ በኋላ ነው ክርስቶስም ጌታም የሆነው እንጂ በፊት አልነበረም የሚል መከራከርያ የሚያነሱ አሉ። ግን በማቴ 2፡1-6፣ 16፡15-20፤ ዮሐ 1፡41፤ 13፡13-14 ስናይ እየሱስ ከሞቱ በፊትም ክርሰቶስም ጌታም ነበር። ነገር ግን በክብር በኀይል የተገለጠው ከትነሳኤው በኋላ ነው።

እግዛብሔር በብሉይ ኪዳን በብዙ ቁጥርን ተጠቅሷል?

1)ዘፍ 1፡1 “በመጀመርያ እግዛብሄር(ኤሎሂም)ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።” ኤል(El)እግዛብሄር በነጠላ ቁጠር ሲጠራ ነው።
ብሉይ ኪዳን በተፃፈበት በዕብራይሰጥ አፃፃፍ ነጠላ ቁጥር፤ ሁለትና፤ ከሁለት በላይ የተለየ አፃፃፍ ነው ያላቸው። ለምሳሌ ኤሎሂም ከሁለት በላይ የሆን ብዙ ቁጥር ነው።  
ዘፍ 1፡2 “…የእግዛብሄርም (ኤሎሂም) መንፈስ በውሆች ላይ ይረብብ ነበር።”
ዘፍ 1፡3 “ከዚያም እግዛብሄር (ኤሎሂም) ብርሃን ይሁን አለ፡ ብርሃንም ሆነ።”
2)ዘፍ 1፡26”እግዛብሄር(ኤሎሂም)፡ሰውን በመልካችን(ብዙ ቁጥር)፡ባምሳላችን(ብዙ ቁጥር) እንስራ፡…” እዚህ ጋር ከማን ጋር ነው እየተማከረ ያለው? ከራሱ ጋር ፤ ከመላዕክት ጋር፤ ወይስ ከማን?
ከመላዕክት ጋር ነው እንዳንል…
  1) መላዕክት አይፈጥሩም፡ እግዛብሄር ብቻ ነው ፈጣሪ(ኢሳ44፡24)
  2) መጽሓፍ ቅዱስ አንድም ቦታ ሰውን በመላዓክት መልክ እንደተፈጠረ የሚናገርበት ቦታ የለም

በመጽሓፍ ቅዱስ አንድም ቦታ ንጉስ ወይም መሪ በብዙ ቁጥር(እኛ)ተብሎ አልተጠራም
ዘፍ 1፡26-27”እንደ መልካችን ብሎ… እንደ መልኩ ፈጠረው ይላል፡፡” ሰው አንድ መልክ ነው ያለው እሱም የእግዛብሔር እንጂ የእግዛብሔርና የመላዐክት (የመላዕክት አለቃ) መልክ የለውም። ከእግዛብሔር ሌላ ሰው ሌላ መልክ ቢኖረው ኖሮ “እንደ መልካቸው ፈጠሩት” ይል ነበር ቃሉ።
ዘፍ 5፡1”… እግዛብሔር ሰውን ሲፈጥረው በራሱ አምሳል አበጀው፡ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው…” እዚህ ቦታ ላይ “በራሱ” ሲል (ነጠላ) ቁጥር ነው የምናየው፡ ሰውንም የፈጠረው በራሱ አምሳል ነው። ዘፍ 1፡27 ላይ እንደምናየው እንደ መልኩ ነው ሰው የተፈጠረው፡ ዘፍ 1፡26 ላይ ደግሞ እንደመልካችን ሲል ነው የምናየው፡፡
እግዛብሔር በኢሳ 40፡13-14 ላይ ቃሉ እንደሚለን “የእግዛብሔርን መንፈስ የተረዳ፣ አማካሪውስ ሆኖ ያስተማረው ማነው? ዕውቀትስ ለማግኘት እግዛብሔር ማንን አማከረ?...” ይላል። ታዲያ እግዛብሔር ሰውን ለመፍጠር ማንን አማከር?


3) ዘፍ 3፡22 “…ሰው መልካሙንና ክፉውን ለይቶ በማወቅ ከእኛ እንደአንዱ ሆኗል፡…”

4) ዘፍ 11፡7-9”ኑ እንውረድ፡ እርስ በርሳቸው እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እንደባልቀው… እግዛብሄር በዚያ የመላውን ዓለም ቋንቋ ስለደበላለቀ…”
ዘፍ 18፡1-2”…ሳለ እግዛብሄር ተገለጠለት፡ ቀና ብሎ ሲመለከት፡ ሦስት ሰዎች ቆመው አየ…” ዘፍ 19፡1”ሁለቱ መላዕክትም ምሽት ላይ ሶዶም ደረሱ…” ከእግዛብሄር ጋር መላዕክት አብረው ከተገለጹ መላዕክት መሆናቸው ይጠቀሳል።
5) ዘፍ 19፡24 “ከዚያም እግዛብሄር በሶዶምና ጎሞራ ላይ ከስማይ ከእግዛብሄር ዘንድ የሚያቃጥል ዲንና እሳት አዘነበባቸው”

6) ኢሳ 48፡12-16”ያዕቆብ ሆይ የጠራሁህ እስራኤል ሆይ ስማኝ እኔ እኔው ነኝ፡ ፊተኛው እኔ ነኝ፡ ኋለኛው እኔ ነኝ። …አሁንም ጌታ እግዛብሄርና መንፈሱ ልከውኛል።”

7) ኢሳ 63፡7-14 ”የእግዛብሄር ቸርነት፣ እግዛብሄር ስላደረገልን ሁሉ ስለሚመሰገንበት ሥራው፣…ስለዚህም አዳኝ ሆነላቸው።…በጭንቀታቸውም ሁሉ ተጨነቀ የፊቱም መልዐክ አዳናቸው፡ …እነርሱ ግን ዐመፁ ቅዱስ መንፈሱንም አሳዘኑ፡…”

8)ዘካ 2፡8-11 “እግዛብሄር ጸባኦት(Lord Almighty) እንዲህ ይላልና፡ “ካከበረኝና በዘረፉአችሁ አሕዛብ ላይ ከላከኝ በኋላ፡ የሚነካችሁ የዐይኑን ብሌን ይነካል፡ እነሆ፡ እጄን በእነርሱ ላይ አነሣለሁ፡ ባርያዎቻቸውም ይዘርፏቸዋል፡ ከዚያም እግዛብሄር ጸባኦት(Lord Almighty) እኔን እንደላከኝ ታውቃላችሁ። የጽዮን ልጅ ሆይ፡ እልል በይ፡ ደስም ይበልሽ፡ እኔ እመጣለሁና፡ በመካከልሽም እኖራለሁ፡ ይላል እግዛብሄር። በዚያ ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዛብሄር ይጠጋሉ”የእኔም ሕዝብ ይሆናሉ። በመካከልሽ እኖራለሁ፡ እግዛብሄር ጸባኦት ወደ አንቺ እንደላከኝ ታውቃላችሁ።” 
**ወደ ሕዝቡ ተልኮ ለማዳን የመጣው ሁላችንም እንደምናውቀው እየሱስ ነው። እዚህ ቦታ ግን እግዛብሔር ጸባኦት ተብሎአል።**

9) ዘካ 3፡2 እግዛብሄርም ሰይጣንን፡ አንተ ሰይጣን፡ እግዛብሄር ይገሥፅህ፡ኢየሩሳሌምን የመረጠ እግዛብሄር ይገሥፅህ፡…”     

10) መዝ 45፡6-7 “አምላክ ሆይ፡ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይኖራል፡ የመንግስትህ በትር የቅንነት በትር ናት። ጽድቅን ወደድክ፡ አመፃን ጠላህ፡ ስለዚህ እግዛብሔር አምላክህ፡ ከጓደኞችህ ይልቅ አንተን የደስታ ዘይት ቀባህ።”  

11) ሆሴ 1፡6-7 “ጎሜር እንደገና ፀነሰች፡ ሴት ልጅም ወለደች፡ እግዛብሔርም ሆሴዕን እንዲህ አለው፡ ይቅር እላቸው ዘንድ ለእስራኤል ቤት ከእንግዲህ ስለማልራራላቸው፣ ስሟን ሎሩሃማ ብለህ ጥራት። ነገር ግን ለይሁዳ ቤት እራራለሁ፡ በቀስት ወይም በሰይፍ ወይም በጦርነት ወይም በፈረሶችና በፈረሰኞች ሳይሆን በአምላካቸው በእግዛብሔር አድናቸዋለሁ።”

12)ሆሴ 12፡2-5እግዛብሔር በይሁዳ ላይ የሚያቀርበው ክስ አለው፡ ያዕቆብን እንደመንገዱ ይቀጣዋል፡ እንደ ሥራው ይከፍለዋል። በማህፀን ሳለ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፡ ሙሉ ሰውም ሲሆን ከአምላክ ጋር ታገለ። ከመልአኩም ጋር ታገለ፡ አሸነፈውም፡ በፊቱ ሞገስን ለማግኘት አልቅሶ ለመነው፣ እርሱንም በቤቴል አገኘው በዚያም ከእርሱ ጋር ተነጋገረ፣ እርሱም ሁሉን የሚገዛ አምላክ እግዛብሔር፣ የሚታወቅበት ስሙም እግዛብሔር  ነው።”  

እንዲሁም ሌላ ቦታ አሞጽ 4፡10-11፣ ኢሳ 6፡8 እግዛብሄር በብዙ ቁጥር ሲገለጽ እናያዋለን።

እስካሁን ያየነው እንዴት በብሉይ ኪዳን እግዛብሄር በብዙ ቁጥር ይገለጽ እንደነበር ነው።   

Trinity symbol



መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ ሥላሤን የሚያመለክተን ቦታ ቢኖር በማቴ 28፡19 ላይ ነው። “ስለዚህ ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ በአብ ፤ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀመዛሙርቴ አድርጓቸው፤”

1. ልብ ብለን ካየን የሦስቱንም ማንነት ሲጠቅስ በ…፣በ…፣በ….በእንግሊዘኛው (the) እያለ ሦስቱንም ራሳቸውን ችለው ነው የጠራቸው (አብ፤ ወለድና መንፈስ ቅዱስ) ይህም አንዱ ከአንዱ የተለየ ሰብዕና (ማንነት) እንዳላቸው ያሳየናል። 
2. ሌላው ሦስቱን ከጠቀሰ በኋላ የተጠቀመው ስም የሚለውን ነው እንጂ ስሞች አይደለም። ይህም ሦስትም አንድን የሚለውን  በግልፅ ያሳየናል። ሥላሤን የሚቃወሙ እዚህ ቦታ ላይ የተጠቀሰው ስም የሚለውን ለመጠርያ ሳይሆን ለሥልጣንና ለኀይል እንጂ እንደመጠርያነት አይደለም ይላሉ። ለምሳሌ ልክ በሕግ ስም እንደሚባለው ማለት ነው። ይህ መከራከርያ ግን መጽሐፍ ቅዱስ ለሚያውቁ ጠንካራ ነጥብ አይደለም። ምክንያቱም በመጽሐፍ ቅዱስ አፃፃፍ ላይ እዚህ ቦታ ላይ በተፃፈበት በግሪኩ ቃል ስናየው የተጠቀመበት ቃል (onoma) የሚለውን ነው። ይህ ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ 228 ጊዜ ተጠቅሷል። ከአራት ቦታዎች በስተቀር (ማር 14፡32; ሉቃ 1፡26; 24፡13; ሐዋ 28፡7; ራዕ 3፡12) ሁል ጊዜ የሚጠቀምበት ሰብዕና ላለው ነገር ነው። ደግሞም ይህን ቃል በኀይል ወይም በሥልጣን የምንጠቀምበት ከሆነ ሥልጣንና ኀይሉ ሰብዕና ላለው እንጂ ሰብዕና ለሌለው  መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሲጠቀምበት አናየውም። እንግዲህ እንደ ኀይል ወይም ሥልጣን ስንወስደው የሦስቱም ስም ተጠቅሶ ስለሆነ የተፃፈው ይህ የሚያሳየው ሦስቱም እኩል ኀይል እንዳላቸው ነው። ለምሳሌ በእየሱስም ስም እንጸልያለን። በእየሱስ ስም መጸለይ ማለት በእሱ ኀይልና ሥልጣን መፀለይ ማለት ነው። ከዚህ ተነሠተን በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ሲለን የምንረዳው ነገር ቢኖር እያንዳንዱ ስም እኩል ኀይልና ሥልጣን እንዳለው ነው።   

2 ቆሮ 13:14 “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዝአብሔር ፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስ ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን።”


Economical trinity ከሥራቸው ጋር በተያያዘ

እግዝአብሔር አባት እየሱስ ልጅ
ዕብ 1:5 “እግዝአብሔር፣አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤ ወይስ ደግሞ፤እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል ያለው ከመላእክት ከቶ ለማን ነው?”
ማቴ 3:17 “የምወደው ልጄ ይህ ነው።”
ማቴ 16:16,17 ; ማቴ 17:5 ….
እግዝአብሔር ለእየሱስ ሥጋን አዘጋጀ
ዕብ 10:5
አብ ወልድን ላከ
1 ዮሐ4:10፤ ዮሐ 6:44 ፤ 8:18
 ፍርድን አባት ለልጅ ሰጠ
ዮሐ 5:22
እየሱስ ወደ አባቱ ጸለየ
ዮሐ 17:1-26፤ ማቴ 26:39; ዮሐ 11:41
ዓለም ከመፈጠሩ በፊት እየሱስ ከአብ ጋር ነበር
ዮሐ 1:1-3,14; 17:5,24
አብ እንደላከው እየሱስ ደቀመዛሙርቱን ላከ
ዮሐ 17:18; 20:20,21
እየሱስ በአብ ቀኝ ነው
ኤፌ 1:17,20
አብና እየሱስ የየራሳቸው ፈቃድ አላቸው
ማቴ 26:39
አብና እየሱስ ሁለት ምስክሮች ይሆናሉ።
ዮሐ 8:13,16-18,29
አብና እየሱስ አንድ ላይ ራሳቸውን ሲጠሩ እኛ ይላሉ።
ዮሐ 14:23; 17:20-23
አብና እየሱስ መንፈስ ቅዱስን ይልካሉ።
ዮሐ 14:16,26; 15:26; 16:7; 13-15
እየሱስ ከመንፈስ ቅዱስ ይለያል።
ማቴ 12:31,32፣
ዮሐ 14:17,19
ማቴ 1:18
መንፈስ ቅዱስ ለቤተክርስትያን ስጦታን ይሰጣል።
1ቆሮ 12:8-11;
መንፈስ ቅዱስ ፍሬን እንድናፈራ ያደርጋል።
ገላ 5:22-23



እግዝአብሔር ወልድ 

በመጽሓፍ ቅዱስ ወልድ(እየሱስ) “እግዝአብሔር”---“እግዝአብሔር ከእኛ ጋር”---“አምላክ”---“እውነተኛ አምላክ”---“የእግዝአብሔር ልጅ”---ወዘተ… ተብሎ ተጠርቷል። እስቲ እያንዳንዱን ከእግዝአብሔር ቃል ጋር እናስተያየው።

1. “እግዝአብሔር” 

1.1 ዮሐ 1፡1 “በመጀመርያ ቃል ነበር፡ ቃልም ከእግዝአብሔር ጋር ነበር፡ ቃልም እግዝአብሔር ነበር።”
ይህን ለማስረዳት መጀመርያ ሌላ ምሳሌ ልጠቀም “ሄዋን በገነት ነበረች፡ ሄዋንም ከሰው ጋር ነበረች፡ ሄዋንም ሰው ነበረች።” ከዚህ ምሳሌ እንደምንረዳው ሄዋን ከሰው ጋር ነበረች ሲል ከሆነ(specific)ሰው (አዳም) ጋር ነበረች ማለት ሲሆን። ሄዋን ሰው ነበረች ሲል ደግሞ፡ ሄዋን ባጠቃላይ(in general)ሰው ነች ማለት ነው። ዮሐ 1፡1 ስናየው ቃል ከእግዝአብሔር(አብ) ጋር ነበር፡ ቃልም እግዝአብሔር ነበር ሲል በተፈጥሮም(በባህርይም)(in general)እግዝአብሔር ነበር እያለን ነው።
NWT ትርጉም ቃልም ከእግዝአብሔር ጋር ነበር  የሚለው ቦታ ላይ “GOD” ተጠቅመው፡ ቃልም እግዝአብሔር ነበር የሚለው ቦታ ላይ “a god” ተጠቅመዋል። ለዚህም የሚሰጡት ምክንያት ግሪኩ ላይ “definite article” የለም በሚል ምክንያት ነው። ከላይ እንደጠቀስኩት አጠቃላይ(general) የሆነ ስለሆነ  ” መግባት የለበትም ። ግሪኩ ይህን ይመስላል “En(In) archδ(beginning) δn(was)ho(the)logos(word), kai(and) ho(the) logos(word) δn(was) pros(with) ton theon(the God), kai(and) theos(God) δn(was) ho(the) logos(word).” ቃል በቃል ሲተረጎም ይህን ይመስላል። 3ተኛው አረፍተ ነገር ላይ Theos(God) ሲል definite article “the” “ho” ስሌለ “a god” ተብሎ መተርጎም አለበት ይላሉ። እንዲያው ይህ ምክንያት ከነሱ ዶክትሪን ጋር እንዲሄድ ነው እንጂ ዮሐ 16 “ከእግዝአብሔር የተላከ…” በግሪኩ “…para(from) theos(God)” ላይ definite article “the” “ho” ባይኖርም(God) ብለው ተረጎሙት እንጂ “a god” ብለው አልተረጎሙትም። ዮሐ 118 ላይም እንዲሁ ከቶውንም እግዛብሄርን ያየ ማንም የለም…”   “theon(God) oudeis(no one)  heoraken(seen) popote(ever) ላይ definite article “the” “ho” ባይኖርም(God) ብለው ተረጎሙት እንጂ “a god” ብለው አልተረጎሙትም። ስለዚህ ዮሐ 11 “…ቃልም እግዝአብሔር ነበር። ብለው በትክክለኛው ቢተረጉሙት የእነሱን ትምህርት ስለሚያፋልስ  “a god” ብለው ተርጎመውታል።

ሌላው ከእነሱም ትምህርት ጋር በሚስማማ በነርሱም ትርጉም ሉቃ 2037-38 ላይ “…የሕያዋን አምላክ (a God) እንጂ የሙታን አይደለም።ብለው ተርጉመውታል ግን እዚህ ቦታ ላይ “definite article” ባይኖርም አምላክን capital letter “a God” እንጂ small letter “a god” ብለው አልተረጎሙትም። ለምን ወጥ አተረጓጎም አይኖረንም?
ምሳሌዎችን አንድ ላይ ስናያቸው
JOHN 1:6:“There came a man, sent from a God.…”
JOHN 1:18: “No man has seen a God at any time.…”
MATTHEW 5:9: “Blessed are the peacemakers, for they shall be called sons of a God.”
LUKE 20:37-38: “…He is a God, not of the dead, but of the living, for they are all living to him.”

እንዲሁም ደግሞ እየሱስ ከ “definite article” ጋር አምላክ ተብሎ የተጠራበት ቦታ አለ…
· MATTHEW 1:23: “Look! The virgin...will give birth to son, and they will call the name of him Immanuel; which is being translated With us the God.” —Kingdom Interlinear Translation
· JOHN 20:28: “Answered Thomas and he said to him The Lord of me and the God of me!”—Kingdom Interlinear Translation
· JOHN 1:18: “No man has seen God at any time; the only begotten God, who is in the bosom of the Father, He has explained Him.”
· 1 JOHN 5:20; 1:2: “…we are in Him who is true, in His Son Jesus Christ. This is the true God and eternal life.…the eternal life, which was with the Father and was manifested to us.…”
· HEBREWS 1:8: “But of the Son He says, ‘Thy throne, O God, is forever and ever, and the righteous scepter is the scepter of His Kingdom.’ ”


1.2 ኢሳ 403የዐዋጅ ነጋሪው ድምፅ እንዲህ ይላል፣ የእግዝአብሔርን መንገድ፣ በምድረበዳ አዘጋጁ፡ ለእምላካችን አውራ ጎዳና አስተካክሉ።
    እዚህ የሚዘጋጀው መንገድ የእግዝአብሔር (ይሆዋ) ሲሆን

    ማቴ 31-3በዚያን ወራት መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ ምድር አየሰበከ መጣበነቢዩ ኢሳያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረለት እርሱ ነው። በምድረ
   በዳ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጎዳናውንም አስተካክሉ እያለ የሚጮህ ደምፅ
    እዚህ ደግሞ የሚያዘጋጀው መንገድ የእየሱስ ነው። የሚዘጋጀው መንገድ ደግሞ አንድ ስለሆነ እግዝአብሔርና እየሱስ አንድ ናቸው ማለት እንችላለን።


2.እግዝአብሐር ከእኛ ጋር

ማቴ 123 “…ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፡ ትርጉሙም እግዝአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው። በግልጽ እንደምናየው ዮሐ 114 ላይ ቃልም ስጋ ለበሰ በመካከላችንም አደረ እንደሚለው በመካከላችን ያደረው ይህ ቃል ማቴ 123 ላይ እግዝአብሔር ከእኛ ጋር ብሎታል።

3. ጌታዬም አምላኬም

ዮሐ 2028-29 ቶማስም ጌታዬም አምላኬም! አለው።…” ሐዋርያው ቶማስም አምኖ እየሱስን አምላኬ ብሎ ጠራው። እየሱስም እንዲህ ስላለው አልኮነነውም።
ሐዋርያው ጳውሎስ በሐዋ 2028 የእግዝአብሄርን ቤተክርስትያን እርሱ (እግዝአብሔር) በገዛ ደሙ የዋጃትን ጠብቁ ይላቸዋል።“…በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዝብሔርን ቤተክርስትያን ጠብቁ።
Acts 20:28 "to shepherd the church of God which He purchased with His own blood," ይህ ቃል ስጋ የለበሰው ራሱ እግዝአብሔር እንደሆነ ይነግረናል። ሌላ ቦታ ቤተክርስተያን እየሱስ የራሱ እንደሆነች ይነግረናል ማቴ 1618”…በዚህ ዐለት ላይ ቤተክርስትያኔን እሰራለሁ…” እዚህ ቦታ ላይ ቤተክርስትያን የእየሱስ ቤተክርስትያን ናት።

4.የእግዛብሄር ልጅ

ይሆዋ ራሱ ስለልጁ እንዲህ ይመሰክራል ዕብ 18 ስለ ልጁ ግን እንዲህ ይላልአምላክ ሆይ፡ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ፀንቶ ይኖራል…”
መጽሐፍ ቅዱስ እየሱስን አንድያ ልጅ ብሎ ሲጠራው እናያለን (ዮሐ 114, 18316, 18 እና 1 ዮሐ 49) እነዚህ ቦታዎች ላይ ያለው የግሪክ ቃል (monogenes)ነው የሚለው።
ትርጉሙም “monos” በእንግሊዘኛ “only”  በአማርኛ ብቻ ማለት ሲሆን የግሪክ ቃል “genos” ደግሞ በእንግሊዘኛ  “stock” “a class” “kind” በአማርኛ  “ሸቀጥወይም አንድ አይነት ተመሳሳይ ወይም ነገር ክምችትማለት ነው።  monogenes የሚለውን በአንድ ላይ ስንተረጉመው በእንግሊዘኛ unique, one of a kind, one and only ማለት ሲሆን፡ በአማርኛ ደግሞአንድ ብቸኛ የራሱ አይነት ” “ከዛው ነገር አንድ ብቸኛ ወይምየተለየ የዛ ነገር ብቻ ማለት እንችላለን። ስለዚህ ይህን የግሪክ ቃል ተመርኩዘን አንድያ ልጅ የሚለውን ስንረዳው ትርጉሙእንደእግዛብሔር አይነት የሆነ” “አንድና ብቸኛ የእግዛብሔር ልጅ” ብለን እንረዳዋለን። 

የእንስሳ ልጅ እንስሳ ነው። የሰው ልጅ ሰው ነው። የእግዛብሄር ልጅ ደግሞ እግዛብሄር ነው።

ሥላሤን የሚቃወሙ አየሱስ የእግዝአብሔር አንድያ ልጅ ስለተባለ ልጅ ደግሞ ከአባቱ ስለማይቀድም እንዲሁም ልጅ ከሆነ መጀመርያ ስላለው በተመሳሳይም ይስሐቅ የአብርሐም አንድያ ልጅ ተብሎ እንደተጠራው፡ እየሱስም የእግዝአብሔር የመጀመርያ ልጅ ስለሆነ ፍጡር መሆኑን ያሳያል ስለዚህ እየሱስ እግዝአብሔር መሆኑን አያሳይም ይላሉ። ይህንን የመከራከርያ ነጥብ ከአባት እና ልጅ የምድር ሥርአት ጋር እያያዝን ለማስረዳት ከሞከርን ሌላ መመለስ ያለብን ነጥብ ይኖራል። እሱም ከምድር የአባትና የልጅ ሥርአት እንደምናውቀው ሁሉም አባት ልጅ እንዲኖረው የልጁ እናት መኖር አለባት። እየሱስ ሥጋ ከመልበሱ በፈት ስለነበረ መንፈሳዊ እናቱ ማነች? መንፈሳዊ እናት እንዳልነበረችው ሁላችንም ስለሚያስማማን የምድር የአባትና የእናት ሥርአት ለመንፈሳዊውም ማስረጃ ማረግ አንችልም። በዚህም አይነት ለመንፈሳዊው ነገር አባት ከልጅ በእድሜ ይበልጣል ለማለት አንችልም።

ይህን ካልን ታዲያ በዚያን ጊዜ በነበረው አገላለፅ የእግዝአብሔር ልጅ ሲባል ምን ማለት ነው? በአይሁዳውያን የአገላለፅ ሁኔታ “የ….. ልጅ” ማለት በዚያው ተራ፣ደረጃ፣ማዕረግ (of the order) ይም ደግሞ ባህርይ፣ተፈጥሮ (nature of…) ማለት ነው። ስለዚህ እየሱስ ራሱን በዚያ ባህል መሠረት የእግዝአብሔር ልጅ ብሎ ሲጠራ አይሁዳውያን የሚረዱት ራሱን በእግዝአብሔር ተራ፣ደረጃ፤ማዕረግ፣ባህርይ ወይም ተፈጥሮ መሆኑ ስለገባቸው ነበር እርሱን ለመውገር ከአንድ ጊዜ በላይ የሞከሩት። ይሁን ሁኔታ ደግሞ ከባህላቸው አንፃር በሌላ አጠራር ደግሞ እንዴት እንደሚጠቀሙበት እንየው…

1 ነገ 20፡35 “ከነቢያት ልጆች አንዱ….” ይህ የሚያሳየን ይህ አንዱ በነቢያት ተራ፣ደረጃ፤ማዕረግ፣ባህርይ እንዳለው እና ነቢይ እንደሆነ ነው።
ነህ 12፡28 “መዘምራኑን…” “Sons of the singers”  ይህ የሚያሳየን እነዚህ በመዘምራን ተራ፣ደረጃ፤ማዕረግ፣ባህርይ እንዳላቸው ነውና ዘማሪ እንደሆኑ ነው።
ኤፌ 2፡2 “…በማይታዘዙት ሰዎች…” “Sons of disobedience”  ይህ የሚያሳየን እነዚህ ሰዎች በማይታዘዙት ተራ፣ደረጃ፤ማዕረግ፣ባህርይ እንዳሉ ነው።
ዮሐ 6፡62 “..የሰው ልጅ…” ይህ የሚያሳየን እየሱስ በሰው ተራ፣ደረጃ፤ማዕረግ፣ባህርይ ወይም ተፈጥሮ እንደሆነና ሰውም እንደሆነ ነው።
ዮሐ 20፡31 “…እየሱስ ክርስቶስ፣ የእግዝአብሔርም ልጅ እንደሆነ እንድታምኑ…” ይህ የሚያሳየን እየሱስ ክርስቶስ በእግዝአብሔር ተራ፣ደረጃ፤ማዕረግ፣ባህርይ ወይም ተፈጥሮ ልክ እንደሆነ ነው።

እንጊዲህ ይህም ስለገባቸው ነበር ራሱን እየሱስ የእግዝአብሔር ልጅ ብሎ ሲጠራ በዮሐ 19፡7 ላይ እንደምናየው ሊገሉት የፈለጉት “አይሁድም፣ “እኛ ሕግ አለን፤ ራሱን የእግዝአብሔር ልጅ ስላደረገ በሕጋችን መሠረት መሞት አለበት” አሉ።”      
  
5.እውነተኛ አምላክ

    1 ዮሐ 5፡20 “…እኛም እውነተኛ በሆነው በልጁ በእየሱስ ክርስቶስ አለን። እርሱ እውነትኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።”
    2ጴጥ 1፡1”…በአምላካችንና በአዳኛችን በእየሱስ ጽድቅ በኩል እንደተቀበልነው…”
            እየሱስ አምላክም ነው አዳኝም ነው።
    ኢሳ 43፡10, 11 እንዲህ ይላል “…ከእኔ በፊት አምላክ አልተሰራም ከእኔም በሁኋላ አይኖርም። እኔ፡ እኔ እግዛብሄር ነኝ ከእኔ ሌላ የሚያድን የለም።”
              አብም አምላክም ነው አዳኝም ነው።

    ሮሜ 9፡5”አባቶችም የእነርሱ ናቸው፤ ክርስቶስም በስጋ የትውልድ ሐረጉ የሚቆጠረው ከእነርሱ ነው፤ እርሱም፣ ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘላለም የተመሰገነ አምላክ ነው፤ አሜን።”

6.ኀያል አምላክ (Mighty God)

ኢሳ 9፡6”ሕፃን ተወልዶልናልና፤ ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤ አለቅነት በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።” ሁላችንም እንደምንስማማበት ይህ ቦታ እየተረከ ያለው ስለእየሱስ ነው። እየሱስንም ኀያል አምላክ፡( በዕብራይስጥ el gibbor) ብሎታል። ይህ አጠራር ለይሆዋ ብቻ የሚሰጥ አጠራር ነው ምክንያቱም በሚቀጥለው መዕራፍ ኢሳ 10፡20-21 ላይ እግዛብሔርን ኀያል አምላክ ብሎ ጠርቶታል። “… ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ በእግዛብሔር ላይ፣ በእውነት ይታመናሉ። የተረፉት ይመለሳሉ፣ ከያዕቆብ ቤት የተረፉት ወደ ኀያሉ አምላክ( el gibbor) ይመለሳሉ።” እዚህ ቦታ ላይ ኀያል አምላክ ብሎ የጠቀሰው እግዛብሔርን ነው። እንደምናውቀው ደግሞ አንድ እውነተኛ አምላክ የሁሉም ነገር ፈጣሪ ሲኖር ሌሎቹ አምላክ ተብለው የተጠሩ ደግሞ በባህርያቸው አምላክ ያልሆኑ ድግሞም ጠፊዎች፣ ደግሞም ከእግዛብሔር ጋር የሚተካከል መጠርያ የሌላቸው ናቸው።

6.ሁሉን ቻይ አምላክ (Almighty God)

ራዕ 1፡8 “ያለውና የነበረው፡ የሚመጣውም፡ ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ፡ አልፋና ኦሜጋ እኔ ነኝ ይላል” እዚህ ጋር እየተናገረ ያለው ማነው? ሥላሤን የሚቃወሙ ይህ የአብ ንግግር ነው ሲሉ፤ ሥላሤን የሚደግፉ ደግሞ የእየሱስ ንግግር ነው ይላሉ። እየሱስ ስለመሆኑ ምክንያቶቹን ልግለፅ
1. መጽሓፍ ቅዱስ እንደሚነግረን በመጨረሻው ቀን የሚመጣው (ለፍርድ) (ማቴ 16፡27) እየሱስ ነው።
2. አልፋና ኦሜጋ(የመጀመርያና የመጨረሻ) የአንዱ የይሆዋ መለያ ነው፡ እዚህ ቦታ ደግሞ ለእየሱስ ተሰጥቶታል፤ ይህን የምናውቀው ደግሞ በራዕ 22፡12-13 ላይ በተገለፀው መሠረት ነው፦
     ራዕ 22፡12-13”እነሆ፡ ቶሎ እመጣለሁ፡ ዋጋዬ በእኔ ዘንድ አለ፡ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍለዋለሁ። አልፋና ዖሜጋ፡ ፈተኛውና ኋለኛው፡ መጀመርያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።” ካለ በኋላ ቁጥር 16 ላይ “እኔ እየሱስ እነዚህን ነገሮች እንዲመሰክር መልአኬን …” እያለ ከላይ ተናጋሪው እሱ እንደሆነ ያስረግጥልናል። በመቀጠልም ቁጥር 20 ላይ “እነዚህን ነገሮች የሚመሰክርው አዎ ቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን፡ ጌታ እየሱስ ሆይ፡ ና። ”  ስለዚህ በራዕ 1”8 ላይ ተናጋሪው ሁሉን ቻይ የሆነው፣ ይሆዋ የሆነው እየሱስ ነው።

    ኢሳ 44፡6”…የፊተኛውም እኔ ነኝ፡ የኋለኛውም እኔ ነኝ፡ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም” ይህ የይሆዋ ንግግር ነው።
    ኢሳ 48፡12”…እኔ እኔው ነኝ፡ ፊተኛው እኔ ነኝ፡ ኋለኛውም እኔ ነኝ…” ይህ የይሆዋ ንግግር ነው።

    ራዕ 1፡17-18 “… አትፍራ፡ የመጀመርያውም የመጨረሻውም እኔ ነኝ፡ እኔ ሕያው ነኝ፡ ሞቼ ነበር፡ እነሆ አሁን ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ።…”
                እዚህ ቦታ ላይ ደግሞ በግልፅ እንደሚያሳየው ተናጋሪው እየሱስ ነው።

7. የዘላለም አባት

በኢሳ 9፡6”ህፃን ተወልዶልናልና፤ ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤ አለቅነት በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።”
እንደ ዘፅ 4፡22 እግዛብሔር እስራኤልን በኩር ልጄ ብሎ ይጠራዋል “ ስለዚህ ለፈርዖን እንዲህ በለው፤ እግዛብሔር እንዲህ ይላል፤ እስራኤል የበኩር ልጄ ነው፤ ያመልከኝ ዘንድ ልጄን ልቀቀው…”
የዘፅ 4፡22 ሃሳብ እግዛብሔር ከእስራኤላውያን ጋር የአባትና የልጅ ግኑኝነት እንደነበረው ነው የሚያሳየን እንዲሁም ኢሳያስ በ9፡6 እንደሚለን ለእኛ ሲል ለእስራኤላውያን (እኛም በክርሰቶስ ያመንን በመንፈስ እስራኤላውያን ነን)የተወለደው ህፃን የዘላለም አባት (አባታችን)ይባላል እያለን ነው። ስለዚህ እግዛብሔርም የእስራኤል አባት ነው። እየሱስም እንዲሁ የእስራኤል አባት ነው። ይህ አስራኤል ስንት አባት አለው ታዲያ?
በሚልክያስ 2፡10 “ሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለንምን? የፈጠረንስ አንድ አምላክ አይደለምን?...” ስለሚል እስራኤል ሁለት አባት የለውም ሁለት አምለክም አልፈጠረውም። ስለዚህ አብና ወልድ አንድ አምላክ፣ አንድ አባት፣ አንድ ፈጣሪ ካልተባሉ በቀር ከቃሉ ጋር ሊጣረስብን ነው።      

8.ጥንታዌ ጥንቱና የሰው ልጅ  

ዳን 7፡13”ሌሊት ባየሁት ራዕይ፣ የሰዉን ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመና ጋር ሲመጣ አየሁ፡ ወደ ጥንታዊ ጥንቱ መጣ፡ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ሥልጣን፡ ክብርና ታላቅ ኃይል ተሰጠው፡ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች፡ መንግሥታትና ሕዝቦች ሰገዱለት፡ ግዛቱም ለዘላለም የማያልፍ ነው፡ መንግስቱም ፈጽሞ የማይጠፋ ነው። “
እዚህ ላይ ሰገዱለት ሲል በእንግሊዘኛው (worship)የሚለው ሓሳብ ነው ያለው። ሌላ ቦታ ደግሞ ስግደት ለእግዛብሄር ብቻ እንደሆነ ነው መጽሃፍ የሚያስተምረን፡ ስለዚህ እየሱስ (የሰው ልጅ)የእግዛብሄር ማንነት ከሌለው ለሱ መስገድ ሐጢአት ነው።

ጥንታዊ ጥንቱ ከዚህ ቦታ እንደምንረዳው እግዛብሄር አብ ነው። የሰው ልጅ ንግስናውን ተቀብሎ ነግሷል። እዛው ምዕራፍ ላይ ወረድ ብለን ዳን 7፡22 ላይ”ይህም የሆነው ጥንታዌ ጥንቱ አስኪመጣና ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪፈርድላቸው ድረስ ነበር…” ቁጥር 13 ላይ ፈራጅ የሰው ልጅ ነው(ንጉስ ስለሆነ)፡ ስልጣን የተሰጠውም ለእሱ ነው፡ የሚመጣውም እሱ ነው። ቁጥር 22 ላይ የሚመጣው ጥንታዌ ጥንቱ ነው፡የሚፈርደው እሱ ነው። 

9.የፍጥረት ሁሉ በኩር

ቆላ 1፡15-16 “እርሱ የማይታየው አምላክ ምሳሌ ነው፡ ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር ነው፡ ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል ፡ በሰማይና በምድር ያሉ፡ የሚታዩ የማይታዩና፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለሥልጣናት፣ ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።”

ይህንን ቃል በደንብ ስናነበው ሁሉም ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል።  የሁሉም ነገር ፈጣሪ እሱ(እየሱስ)ነው። ዮሐ 1፡3 ይህንን ይበልጥ ይደግፋል ”ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ ከተፈጠረው ሁሉ ያለእርሱ የተፈጠረ ምንም የለም።” ሐሳቡን ለማብራራት የተፈጠረ ነገር አለ እምንል ከሆነ ያ የተፈጠረው በእየሱስ ነው። ፍጥረት የሚባል ነገር ሁሉ ፈጣሪው አንድ ነው ያም ፈጣሪ እየሱስ ነው። ይህንን ነው የሚለን ከላይ የተጠቀሰው የእግዛብሔር ቃል። ታዲያ በኩር ሲል ምን ማለቱ ነው? እንደ መጽሐፍ ቅዱስ በኩር ሁለት ትርጉም አለው።

1ኛው.በኩር፡ በአማርኛ የመጀመርያ ልጅ (የተወለደ) ፡ በእንግሊዘኛ “born first or created” በግሪኩ “prototiktoማለት ነው።
2ኛው.በኩር፡ በአማርኛ ወራሽ፤ የበላይ፤ በእንግሊዘኛ ደግሞ “preeminence”፤ በግሪኩ “prototokos” ማለት ነው።

በአዲስ ኪዳን የመጀመርያ ልጅ (የተወለደ) (በኩር) ለማለት የምንጠቀምበትን የግሪክ ቃል (prototikto)አንድም ቦታ አናገኝም። በእርግጥ አዲስ ኪዳን ውስጥ በኩር የሚል ቃል የተለያየ ቦታ ልናገኝ እንችላለን፡ ታዲያ ሁሉም ቦታ የተጠቀሙበት የግሪከ ቃል (prototokos)የሚለውን ነው። ይህም ትርጉሙ ከላይ እንዳየነው የበላይ፣ ወራሽ ፣ ማለት ነው።   

ለምሳሌ ዘፍ 41፡51-51 እና ኤር 31፡9 እንይ
ዘፍ 41፡51-52 “ዮሴፍም፣ እግዛብሔር መከራዬን ሁሉ፣ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አድርጎኛል በማለት የመጀመርያ ልጁን ስም ምናሴ አለው። እንደዚሁም፣ መከራ በተቀበልኩበት ምድር እግዛብሔር ፍሬያማ አደረገኝ ሲል ሁለተኛ ልጁን እፍሬም አለው።”  ከዚህ የእግዛብሔር ቃል እንደምናየው ምናሴ የዮሴፍ በኩር ልጅ ነው።

ዘፍ 48፡17-19”ዮሴፍ፣ አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ማድረጉን ሲያይ ተከፋ፤ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንስቶ በምናሴ ራስ ላይ ለማኖር የአባቱን እጅ ያዘ፤ ዮሴፍም፣ አባቴ ሆይ፣ እንዲህ አይደለም በኩሩ ይህኛው ስለሆነ፣ ቀኝ እጅህን እርሱ ራስ ላይ አድርግ አለው። አባቱ ግን፣ ዐውቃለሁ፤ ልጄ ዐውቃለሁ፤ እርሱም እኮ ሕዝብ ይሆናል፤ ታላቅም ይሆናል፤ ይሁን እንጂ ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል፤ ዘሮቹም ታላቅ ሕዝቦች ይሆናሉ ብሎ እምቢ አለው።” ይበልጥ ደግሞ ይህ ቃል የሚነገረን በኩሩ ምናሴ ቢሆንም የተባረከው ግን ኤፍሬም እንደሆነ ነው።         

ኤር 31፡9 “…እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፣ኤፍሬም በኩር ልጄ ነውና፣” እግዝአብሔር የተስፋው ዘር ሊተላለፍ የፈለገው በኤፍሬም በኩል ስለነበር ያእቆብ እንዲባርክ ያደረገው ኤፍሬምን ነበር፡ ስለዚህ ምንም እንኳ ኤፍሬም ሁለተኛ ልጅ ቢሆንም እግዛብሔር በኩሬ ብሎታል። እዚህ ላይ በኩር የሚለው ቃል የመጀመርያ ልጅ (መጀመርያ የተወለደ) ለማለት ሳይሆን ወራሽ፣ የበላይ የሚለውን ትርጉም ነው የሚሰጠን።  

መዝ 89፡20-27 “ባሬያዬን ዳዊት አገኘሁት፤ በተቀደሰው ዘይቴም ቀባሁት።…እኔም ደግሞ በኩሬ አደርገዋለሁ፤ ከምድርም ነገስታት በላይ ከፍ ይላል።”
አሁንም እዚህ ጋር የምናየው ዳዊት የመጨረሻው ልጅ (8ተኛ ልጅ ቢሆንም “1ሳሙ 16-10”) እግዛብሔር የተስፋው ዘር እንዲተላለፍ የፈቀደው (ወራሽ፤ የበላይ እንዲሆን) በዳዊት በኩል ስለነበር በኩሬ ሲል እናያለን።     

ቆሎ 1፡18”እርሱ አካሉ የሆነችው የቤተክርስትያን ራስ ነው፤ በሁሉ ነገር የበላይነት ይኖረው ዘንድ እርሱ የመጀመርያ፣ ከሙታንም መካከል በኩር ነው።”

ዘፅ 4፡22 “ …እግዝአብሔር እንዲህ ይላል፤ እስራኤል የበኩር ልጄ ነው፤”
እስራኤልን እዚህ ጋር በኩሬ ሲል መጀመርያ የተፈጠረች ሀገር ከሚል ሀሳብ ሳይሆን ከወራሽነት መንፈስ ነው በኩሬ ያላት

እዮ 18፡13 “ደዌ ቆዳውን ይበላል፤ የሞት በኩርም ቅልጥሙን ይበላል።”
ሞትን ያመጣው የመጀመርያው፡ በሽታ አይደለም ስለዚህ እዚህ ጋር በሽታን በኩር ሲለው ከመጀመርያ ጋር እያያያዘ አይደለም

ከላይ ባየነው ምክንያት መሠረት እንግዲህ በኩር የሚለውን ቃል በአማርኛ አሻሚ ትርጉም ስለአለው ምን ለማለት እንደፈለገ ከዐውዱ ሀሳብ ወይንም ከቻልን የግሪኩን ቃል ማየት ከትልቅ ስህተት ይጠብቀናል።  የግሪኩ ቃል  ግን በትክክል ምን ማለት እንደፈለገ ይነግረናል።   

እንዲያውም በዕብ 7፡1-3 ላይ “…አባትና እናት ወይም የተውልድ ሐረግ የለውም፤ ለዘመኑ መጀመርያ፣ ለሕይወቱም ፍፃሜ የለውም፤ ነገር ግን እንደእግዛብሔር ልጅ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል። ብሎ ለዘመኑ ጅማሮና ፍፃሜ እንደሌለው ይናገራል።


  
9.የመዳን ስም

የዳንነው በማን ስም ነው? ሮሜ 10፡9-13 “እየሱስ ጌታ ነው ብለህ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዛብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን፣ ትድናለህ። የምትጸድቀው በልብህ አምነህ ነው፤ የምትድነውም በአፍህም መስክረህ ነውና። መጽሃፍ እንደሚለው፣ በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም። በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ልዩነት የለም፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፤ የሚለምኑትንም አብዝቶ ይባርካል፤ የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።”
1.ይህ ክፍል የሚነግረን ስለአንድ ጌታ ነው። ያም ጌታ እየሱስ ነው። ይህንንም አምነን እየሱስ ጌታ ነው ስንል እንድናለን። ጌታችን ነህ ብለን ስንጠራው የሕይወታችን ጌታ ስናደርገው እንድናለን። ይህ “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና” የሚለውን ሃሳብ ሐዋርያው ያመጣው ከኢዮኤል 2፡32 ነው።” የእግዛብሔርን(የይሆዋ)ስም የሚጣራ ሁሉ፣ እርሱ ይድናል።” በእርግጥ የመጠበቂያ ግንብ ትርጉም ሮሜ 10፡13ን “የይሆዋ ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና” ብሎ ጌታን (ይሆዋ) ብሎ ተርጉሞታል ምንም እንኳን የግሪኩ ቃል ከቁጥር 9-13 ያለውን ጌታ የሚለውን ቃል “kyros” ብሎ ቢጠቀምበትም ቁጥር 13 ያለውን “kyros” ብቻ ይሆዋ ብሎውታል። ግን በግልፅ መጽሐፍ ቅዱስ ስንት የድነት ስም እንዳለ ይነግረናል ሐዋ 4፡10-12”…ድነት በሌላ በማንም አይገኝም፤ እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ ከዚህ ስም በስተቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና።” ይላል
እነዚህን አሳቦች አንድ ላይ ስናመጣቸው ለመዳን የምንጠራው አንድ ስም ብቻ ነው ያለው። ያም ስም እየሱስ ነው። ስለዚህ የጌታን ስም የሚጠራ ይድናል ሲል፡ ከሰማይ በታች ላለነው ለእኛ የምንድንበት ስም አንድ ብቻ ነው። ያም ስም እየሱስ ነው። ኢዮ 2፡32 የመዳኛ ስም ይሆዋ(እግዛብሔር) ነው ይለናል አዲስ ኪዳን ላይ ደግሞ እየሱስ ብቻ ነው ይለናል። እንግዲህ እየሱስ እግዛብሔር ካልሆን ይህም ሃሳብ እርስ በእርሱ ሊጣረስ ነወ። መጽሃፍ ቅዱስ ደግሞ አይጣረስም ስለዚህ በብሉይ ኪዳን የመዳኛ ስም ተብሎ የተጠራው ይሆዋ(እግዛብሔር) እና በአዲስኪዳን የተጠራው የመዳኛ ብቸኛ ስም እየሱስ አንድ ናቸው። እየሱስ ይሆዋ ነው።
         
10.የእግዝአብሔር ስራ ብቻ የሆነውን ኀጢአትን ይቅር ብሎአል፤ የዘላለም ሕይወት ሰጥቶአል።

ሉቃ 7፡48-50 “ እየሱስም ሴቲቱን፣ ኀጢአትሽ ተሰርዮልሻል አላት። አብረውት በማዕድ ተቀምጠው የነበሩ እንግዶችም፣ ይህ ኀጢአትን እንኳ የሚያስተሰርይ እርሱ ማነው? ብለው በልባቸው አሰቡ?...”
ዮሐ 10፡28-30 እኔ የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለሁ … እኔና አብ አንድ ነን።”
ማር 2፡5-7” እየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፣ አንተ ልጅ፣ ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል አለው። በዚያ ተቀምጠው የነበሩ አንዳንድ ፀሐፍት ስለዚህ ነገር በልባቸው እያሰላሰሉ፣ ይህ ሰው እንዴት እንዲህ ይላል? በአምላክ ላይ የስድብ ቃል እየተናገረ እኮ ነው! ካንዱ ከእግዛብሔር በቀር ማን ኀጢአትን ሊያስተሰርይ ይችላል? ብለው አሰቡ።”  
የእግዛብሔር ቃል እንደሚነግረን ሐጢአትን ካለአምላክ በስተቀር ማንም ሊያስተሰርይ አይችልም። እየሱስ በስልጣኑ የሚያስተሰርይ ከሆነ እሱ አምላክ መሆን አለበት።
  
11. ከእግዝአብሔር ጋር እኩል አምላክ

ፊሊ 2፡6 “እርሱ በባሕርዩ (Eng=nature) (Greek=morphe) አምላክ ሆኖ (Eng=being) (Greek=huparcho) ሳለ፣ ከእግዝአብሔር ጋር መተካከልን ሊለቀው እንደሚገባ አድርጎ አልቆጠረውም፤”

ሆኖ (Eng=being) (Greek=huparcho) ማለት የአሁኑ ጊዜ (Present tense) ስለሆነ ቀጣይ ድርጊትን ማለትም ያምላክነት ባህርይ (ተፈጥሮ) ቀጣይነት ያሳያል።
በባሕርዩ (Eng=nature) (Greek=morphe) ማለት የአንድ ነገር ወይም የተጠቀሰው ነገር ዋና (original) ማንነት የያዘ ማለት ነው። በዚህ ሁኔታም “በባሕርዩም አምላክ” ሲል የአምላክነት እውነተኛ (original) ማንነት የያዘ፣ መለኮታው ባሕርይ(ተፈጥሮ) (divine nature) ያለው ማለት ነው።

ይህ ባሀርይ (Eng=nature) (Greek=morphe) ወይም መልክ የሚለው ቃል ወረድ ብሎ ቁጥር 7 ላይ አንደገና እናየዋለን።  

ፊሊ 2፡7 “ነገር ግን የባርያን መልክ ((Eng=nature) (Greek=morphe) ይዞ፣ በሰው አምሳል ተገኝቶ. ራሱን ባዶ አደረገ፤” እዚህ ጋር የባርያን መልክ ሲይዝ እውነተኛ(original) ሰው ነው የሆነው።


ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ  ለይሆዋ የተሰጡ መለዮዎች(ባህሪዎች)በአዲስ ኪዳን ለእየሱስ እንዴት እንደተሰጠ አብረን እንይ።

ኢሳ 44፡6-8 “…ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አለን? ፈጽሞ! ወይም ሌላ ዐለት አለ? የለም! ማንንም አላውቅም።” 
2ሳሙ 22፡32 “ከእግዛብሄር በቀር አምላክ ማን አለና፡ ካምላካችን በቀር ዐለት ማን ነው?”
1ቆሮ 10፡3-4”…ይከተላቸው ከነበረው መንፈሳዊ ዐለት ጠጥተዋልና፡ ያ፡ ዐለት ክርስቶስ ነበር።”

ኢሳ 8፡13-14”ልተቀድሱት የሚገባው የሰራዊት ጌታ እግዛብሄርን(The LORD Almighty) ብቻ ነው፡ ልትፈሩት የሚገባው እርሱን ነው፡ ልትንቀጠቀጥሉት የሚገባው እርሱ ነው፡ እርሱም መቅደስ ይሆናል፡ ለሁለቱ የእስራኤል ቤት ግን የሚያደናቅፍ ድንጋይ የሚያሰናክልም ዐለት ይሆንባቸዋል”
የሚናገረው ስለማነው?  ስለሰራዊት(ሁሉን ቻይ) ጌታ እግዛብሄር (The LORD Almighty)
ሐዋርያው ጴጥሮሰ በመጀመርየው መልዕክቱ 2፡6-8 እንዲህ ይላል
1 ጴጥ 2፡6-8 “ ምክንያቱም በመጽሐፍ እንዲህ ተብሎ ተፅፎአልና፡ እነሆ፡ የተመረጠና ክቡር  የማዕዘን ድንጋይ ፡ በጽዮን አኖራለሁ፡ በእርሱ የሚያምን፡ ከቶ አያፍርም። እንግዲህ ለእናንተ ለምታምኑት ይህ ድንጋይ ክቡር ነው፡ ለማያምኑት ግን፡ ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ። ደግሞም ሰዎችን የሚያሰናክል የሚጥላቸው ዐለት ሆነ፡ የሚሰናከሉት ቃሉን ባለመታዘዛቸው ነው፡ የተመደቡት ለዚህ ነውና።”
 ሐዋርያው ጴጥሮስ በኢሳያስ ለይሆዋ የተነገረውን ለእየሱስ ሲያውለው እናያለን። ሐዋርያው ጴጥሮስ ይህን ሲል እየሱስ ራሱ የሰራዊት ጌታ እግዛብሄር(The LORD Almighty) መሆኑን አምኖ ነው። አለበለዚያ የይሆዋን የተነገረውን ለእየሱስ መስጠት አይችልም። ለነገሩ እየሱስን በ2ጴጥ 1፡1”…በአምላካችንና በአዳኛችን በእየሱስ ጽድቅ በኩል…” እያለ እየሱስን አምላካችንና አዳኛችን ብሎታል።

ኢሳ 45፡18-23”…ጉልበት ሁሉ በእኔ ፊት ይንበረከካል፡ አንደበትም ሁሉ በእኔ ይምላል።”
ፊል 2፡10-11”…ጉልበት ሁሉ ለእየሱስ ስም ይንበረከክ ዘንድ፡ ምላስም ሁሉ ለእግዛብሄር አብ ክብር፡ እየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።”

ዘካ 12፡10”…ወደ ወጉኝ ወደ እኔ ይመለከታሉ…” እግዛብሔር ነው እየተናገረ ያለው።
ዮሐ 19፡31-37”…የእየሱስን ጎን በጦር ወጋው…”
ራዕ 1፡7 እነሆ፡ በደመና ይመጣል፡ የወጉት እንኳ ሳይቀሩ፡ ዐይን ሁሉ ያየዋል…”

ዘዳ 10፡17”አምላካችሁ እግዛብሄር የአማልክት አምላክ፡ የጌቶች ጌታ ታላቅ አምላክ…”
መዝ 136፡1-3”እግዛብሄርን አመስግኑ …የጌቶችን ጌታ አመስግኑ…”
ራዕ 17፡14”…በጉ ድል ይነሣቸዋል፡ ምክንያቱም እርሱ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ነው፡…”        
1ጢሞ 6፡15”ያም መገለጥ፡የተባረከውና ብቻውን ገዥ የሆነው የነገሥታት ንጉስ፡ የጌቶች ጌታ እግዛብሄር በራሱ ጊዜ የሚያሳየው ነው፡”
ራዕ 19፡11-16 “…እርሱም በጽድቅ ይፈርዳል፡…ስሙም የእግዛብሄር ቃል ነው።… በልብሱና በጭኑ ላይ እንዲህ የሚል ስም ተጽፎአል፡ የነገስታት ንጉስና የጌቶች ጌታ።”

ዘካ 14፡5”…ከዚያም አምላኬ እግዛብሔር ይመጣል፡ ቅዱሳኑም ሁሉ አብረውት ይመጣሉ።”
1 ተሰ 3፡13”ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር በሚመጣበት ገዜ በእምላካችንና በእባታችን ፊት ነቀፋ የሌለባችሁና ቅዱሳን ሆናችሁ እንድትገኙ ልባችሁን ያጽና።”

ዘጽ 15፡2 “እግዛብሔር ብርታቴና ዝማርዬ ነው፡ ድነቴም ሆነልኝ” እርሱ አምላኬ ነወ፡ አመሰግነዋለሁ።”
መዝ 3፡8 “ማዳን የእግዛብሔር ነው፡ በረከትህ በህዝብህ ላይ ይሁን።”
መዝ 62፡1 “ነፍሴ ዕረፍት የምታገኘው በእግዛብሔር ብቻ ነው፡ ድነቴም የሚመጣልኝ ከእርሱ ዘንድ ነው።”
መዝ 118፡14,21 “እግዛብሔር ብርታቴና ዝማርዬ ነው፡ አዳኝ ሆነልኝ።…ሰምተህ መልሰህልኛልና አዳኝም ሆነህልኛልና አመሰግንሃለሁ።”
ዕብ 2፡10 “ ሁሉ ነገር ለእርሱና በእርሱ የሚኖር እግዛብሔር ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ለማምጣት፡ የድነታቸውን መሥራች በመከራ ፍፁም ሊያደርገው የተገባ ነበር።”
ዕብ 5፡9 “በዚህም ፍፁም ሆኖ ከተገኘ በኋላ፡ እርሱን ለሚታዘዙ ሁሉ የዘላለም ድነት ምክንያት ሆነላቸው፡”
ራዕ 7፡10 “…ማዳን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው፡ የአምላካችንና የበጉ ነወ።”

ዘፅ 33፡14-15 “እግዛብሔር “ሀልዎቴ(My presence)ከአንተ ጋር ይሄዳል ዕረፍትም እሰጥሃለሁ” ብሎ መለሰ። ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለው። “ሀልዎትህ ከእኛ ጋር ካልሄደ ከዚህ አትስደደን። አንተ ከእኛ ጋር ካልሄድክ…”
ማቴ 11፡28-30”እናንት ሸክማችሁ የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፡ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ ። …ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፡…”

ዘዳ 30፡20 “……ምክንያቱም እግዛብሔር ሕይወትህ ነው፡ ለአባቶችህ፡ ለአብርሃም፡ ለይስሓቅና ለያዕቆብ …”
ቆላ 3፡3-4 ”ሞታችኋልና፡ ሕይወታችሁም ከክርስቶስ ጋር በእግዛብሔር ዘንድ ተሰውሮአልና፡ ሕይወታችሁም የሆነው ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ …”     

ኤር 17፡10 “እኔ እግዛብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፡ እንደ ሥራው ፍሬ ለመስጠት፡ ልብን እመረምራለሁ፡ የአእምሮን ሐሳብ እፈትናለሁ።”
ራዕ 2፡18-23 “…የእግዛብሔር ልጅ እንዲህ ይላል…ከዚያም አብያተ ክርስትያናት ሁሉ እኔ ልብንና ሐሳብን የምመረምር መሆኔን ይረዳሉ፡ ለእያንዳንዳችሁም እንደስራችሁ እከፍላችኋለሁ።”
1ነገ 8፡39 “…አንተ ብቻ የሰውን ልብ የምታውቅ ስለሆንህ ልቡን ለምታውቀው ለእያንዳንዱ ሰው እንደሥራው ሁሉ ክፈለው፡…”  
  
ነህ 9፡6 “አንተ ብቻ እግዛብሔር ነህ። ሰማያትን፡ ከሰማያት በላይ ያሉትን ሰማያትና የከዋክብታቸውን ሰራዊት ሁሉ፡ ምድርንና በላይዋ ያለውን ሁሉ፡ ባሕሮችንና በውስጣቸው ያሉትን ሁሉ ፈጥረሃል። ለሁሉም ሕይወትን ትሰጣለህ፡ የስማይ ሰራዊትም ይሰግዱልሃል።”
ቆላ 1፡16-17” ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል ፡በስማይና በምድር ያሉ፡ የሚታዩና የማይታዩ፡ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኃይላት፡ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለስልጣናት፡ ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፡ እርሱ ከሁሉ በፊት ነው፡ ሁሉም ነገር በአንድ ላይ ተያይዞ የፀናው በእርሱ ንው።”

መዝ 24፡7-10 “ እናንት ደጆች፡ ቀና በሉ፡ እናንት የዘላለም በሮች፡ የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ! ይህ የክብር ንጉሥ ማነው? እግዛብሔር ነው ብርቱና ኃያል፡ እግዛብሔር ነው በውጊያ ኃያል። እናንተ ደጆች፡ ቀና በሉ፡ እናንተ የዘላለም በሮች፡ የክብር ንጉስ እንዲገባ ብድግ በሉ!ይህ የክብር ንጉስ ማን ነው? የሰራዊት አምላክ፡ እርሱ የክብር ንጉሥ ነው።”
1 ቆሮ 2፡8 “ከዚህ ዓለም ገዦች አንዳቸውም ይህን ጥበብ አልተረዱትም፡ ቢረዱትማ ኖሮ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት ነበር።”
ያዕ 2፡1 “ ወንድሞች ሆይ፡ ክቡር በሆነው በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስ የምታምኑ እንደመሆናችሁ አድልዎ አታድርጉ።”        

መዝ 102፡24-27 “እኔም እንዲህ አልሁ፡ “አምላኬ ሆይ፡ በዘመኔ እኩሌታ እትውሰደኝ ዘመናትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራሉ። አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትክ” ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ፡ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፡ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ እንደ መጎናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፡ እነርሱም ወዲያ ይጣላሉ። አንተ ግን ያው አንተ ነህ፡ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።” መዝሙረኛው ዳዊት ለእግዛብሔር የተቀኘው ነው።

ዕብ1፡8.10-12”ስለ ለጁ ግን እንዲህ ይላል…ደግሞም እንዲህ ይላል፡ “ጌታ ሆይ አንተ በመጀመርያ የምድርን መሠረት አኖርህ፡  ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ፡ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፡ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፡ እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ፡ እንደ ልብስም ይለወጣሉ። አንተ ግን ያው አንተ ነህ፡ ዘመንህ ፍፃሜ የለውም።” ይህ ደግሞ እግዛብሔር ሰለልጁ የተናገረው ነው።      
 
ኢሳ 6፡1-5,8-10  ንጉስ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዛብሔርን ከፍ ባለና በከበረ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፡…ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ የሰራዊት ጌታ እግዛብሔር፡ ምድር ሁሉ በክብሩ ተሞልታለች ይሉ ነበር።…እኔም፣ ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፡ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፡ ዐይኖቼም ንጉሡን፣ የሰራዊት ጌታ እግዛብሔርን አይተዋልና ጠፍቻለሁ፣ ወዮልኝ! አልሁ።…ከዚያም የጌታ ድምጽ፣ ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል? ሲል ሰማሁት።…መስማትን ትሰማላችሁ፡ ነገር ግን አታስተውሉም፡ ማየትንም ታያላችሁ፡ ነገር ግን ልብ አትሉም ብለህ ንገራቸው። የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፡ ጆሮአቸውን ድፈን ዐይኖቻቸውን ክደን፡ ይህ ካልሆነማ በዐይናቸው አይተው፣ በጆሮአቸው ሰምትው፣በልባቸውም አስተውለው በመመለስ ይፈወሳሉ።”  ኢሳያስ እዚህ ቦታ ላይ የእግዛብሔርን ክብር ነበር ያየው።
          

ዮሐ 12፡37-41” እየሱስ እነዚህን ታምራዊ ምልክቶች ሁሉ በፊታቸው ቢያደርግም እንኳ፣ አሁንም አላመኑበትም፡ ይኸውም ነቢዩ ኢሳያስ፣ ጌታ ሆይ፣ ምስክርነታችንን ማን አመነ? የጌታ ክንድስ ለማን ተገለጠ? ያለው ቃል እንዲፈጸም ነው። ስለዚህ ማመን አልቻሉም፡ ይህም ኢሳያስ በሌላ ቦታ እንዲህ ሲል እንደተናገረው ነው፣ ዐይናቸውን አሳውሮአል፣ ልባቸውንም አደንድኖአል፣ ስለዚህ በዐይናቸው አያዩም፣ በልባቸውም አያስተውሉም፣ እንዳልፈውሳቸውም አይመለሱምኢሳያስ ይህን ያለው የእየሱስን ክብር ስላየ ነው፣ ስለ እርሱም ተናገረ።”      

ኢሳ 43፡10 “…እናንተ ምስክሮቼ፣ የመረጥሁትም ባርያዬ ናችሁ ይላል እግዛብሔር።”
ሐዋ 1፡8 “ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፣ …እስከ ምድር ዳርቻ ሁሉ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።” 

እዮብ 9፡8”እርሱ ብቻውን ሰማያትን ዘርግቷል፡ በባሕርም ማዕበል ላይ ይራመዳል።”
ኢሳ 44፡24”ከማሕፀንህ የሠራህ፣ የተቤዤህም፣ እግዛብሄር እንዲህ ይላል፡ ሁሉን ነገር የፈጠርኩ፣ ብቻዬን ሰማያትን የዘረጋሁ፣ ምድርን ያንጣለልሁ፡ እኔ እግዛብሄር ነኝ።”
ነህ 9፡6 “አንተ ብቻ እግዛብሔር ነህ። ሰማያትን፡ ከሰማያት በላይ ያሉትን ሰማያትና የከዋክብታቸውን ሰራዊት ሁሉ፡ ምድርንና በላይዋ ያለውን ሁሉ፡ ባሕሮችንና በውስጣቸው ያሉትን ሁሉ ፈጥረሃል። ለሁሉም ሕይወትን ትሰጣለህ፡ የስማይ ሰራዊትም ይሰግዱልሃል።”
ሐዋ 14፡15”…እናንተም ደግሞ ከዚህ ከንቱ ነገር ርቃችሁ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ፈጠረው ወደ ሕያው እግዛብሔር እንድትመለሱ ወንጌልን እንሰብክላችኋለን።” 

ዮሐ 1፡3” ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፣ ከተፈጠረው ሁሉ ያለ እርሱ የተፈጠረ ምንም የለም።”
ቆላ 1፡16-17” ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል ፡በስማይና በምድር ያሉ፡ የሚታዩና የማይታዩ፡ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኃይላት፡ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለስልጣናት፡ ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፡ እርሱ ከሁሉ በፊት ነው፡ ሁሉም ነገር በአንድ ላይ ተያይዞ የፀናው በእርሱ ነው።”
ዕብ 1፡2-3,10-12”በዚህ መጨረሻ ዘመን ግን ሁሉን ወራሽ ባደረገውና ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ለእኛ ተናገረን። እርሱ የእግዛብሄር ክብር ነጸብራቅና የባህርዩ ትክክለኛ ምሳሌ ሆኖ፣ በኃያል ቃሉ ሁሉን ደግፎ ይዞአል፣…ደግሞም እንዲህ ይላል፡ “ጌታ ሆይ አንተ በመጀመርያ የምድርን መሠረት አኖርህ፡  ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ፡ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፡ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፡ እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ፡ እንደ ልብስም ይለወጣሉ። አንተ ግን ያው አንተ ነህ፡ ዘመንህ ፍፃሜ የለውም።”  
         
ከእየሱስ አንደበት ደግሞ…

1. ዮሐ 8፡58 “ እየሱስም እውነት እውነት እላችኋለሁ፡ አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ፡ እኔ ነኝ፡ አላቸው።” እዚህ ጋር እኔ ነበርኩ አይደለም ያለው እኔ እኔ ነኝ ነው (ego eimiበግሪክ)(I AM)ያለው ይህ “እኔ ነኝ” የይሆዋ መገለጫ ነው። ዘፃ 3፡14” እግዛብሄር ሙሴን እኔ ያለሁና የምኖር ነኝ፡ ስለዚህም ያለና የሚኖር ልኮኛል ብለህ ንገራቸው አለው።”God said to Moses, "I AM WHO I AM. This is what you are to say to the Israelites: `I AM has sent me to you.' "
እዚህ ቦታ ላይ ይሰሙት የነበሩት አይሁድ ምን ማለቱ እንደሆነ ገብቶአቸው ሊወግሩት ድንጋይ አነሱ።
ከብሉይ ኪዳን እንደምንረዳው ድንጋይ የሚያስወግሩ ምክንያቶች
1.መንፈስን የሚጠሩ(ጠንቋዮች) ሌዋ 20፡27
2.እግዛብሔርን መሳደብ ሌዋ 24፡10-23
3.ሐሰተኛ ነቢያት ዘዳ 13፡5-10
4.በጣም አሰቸጋሪ ልጅ ዘዳ 21፡18-21
5.ዝሙት ወይም አስገድዶ መድፈር ዘዳ 22፡21-24፣ ሌዋ 20-10 ናቸው።

ይህ “እኔ ነኝ” የሚለው ቃል ምን ያህል ሃይለኛ እንደሆነ በዮሐ 18፡5-6 እናያለን ” እነርሱም የናዝሬቱን እየሱስን አሉት። እየሱስም እርሱ እኔ ነኝ አላቸው። አሳልፎ የሰጠውም ይሁዳ ከእነሱ ጋር ቆሞ ነበር እየሱስም እርሱ እኔ ነኝ ባለ ጊዜ ወደ ኋለ አፈግፍገው መሬት ላይ ወደቁ። “  

ሥላሤን የሚቃወሙ ክፍሎች እዚህ ጋር የነበረውን “እኔ ነኝ” (greek=ego eimi) (English= I AM) በነሱ መፅሐፍ “ነበርኩ” (English= I have been) ብለው ተርጉመውታል::
ምክንያታቸውም
1.1.ከአብርሐም በፈት እንደነበረ ለመናገር ስለፈለገ መተርጎም ያለበት በዚህ መንገድ ነው ይላሉ። ግን የዚህ ወንጌል ፀሐፊ ሐዋርያው ዮሐንስ ሊነግረን የፈለገው ልክ እንደነሱ ሐሳብ ቢሆን ኖሮ ይጠቀምበት የነበረው የግሪክ ቃል (greek = emen) (English = I have been) ይሆን ነበር::

1.2. ከላይ እንደተጠቀሰው ምክንያትም እየሱስ ለማለት የፈለገው ነበርኩ (English= I have been) ቢሆን ኖሮ ይሰሙት የነበረው ሰዎች ሊወግሩት ድንጋይ አያነሱም ነበር።

1.3. ይህን ቃል “እኔ ነኝ” (greek=ego eimi) (English= I AM) በአዲስ ኪዳን ውስጥ በተለያየ ቦታ ሲተረጉሙት “እኔ ነኝ” እያሉ ሲሆን ግን እዚህ ቦታ ብቻ ግን በተለየ ሁኔታ “ነበርኩ”(English= I have been) ብለው ተረጉመውታል። ለምን የለየ ትርጉም ለመጠቀም ተፈለገ?

2.ዮሐ 10፥28-33”እኔ የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለሁ፡ ከቶ አይጠፉም፡ ከእጄም ሊነጥቃቸው የሚችል ማንም የለም። እነርሱን የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፡ ካባቴም እጅ ማንም ሊነጥቃቸው አይችልም፡ እኔና አብ አንድ ነን:፡ አይሁድ ሊወግሩት እንደ ገና ድንጋይ አነሡ።”  

3. ራዕ 5፡6-7 እና ራዕ 11፡15

ራዕ 5፡6-7 “…ከዚያም በዙፋኑና በአራቱ ሕያውያን ፍጡራን፣ በሽማግሌዎችም  መካከል የታረደ የሚመስል በግ ቆሞ አየሁ፤ … እርሱም መጥቶ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ቀኝ እጅ መጽሃፉን ወሰደ።” በጉ(እየሱስ) በዙፋኑ መካከል ነው ያለው አብ ደግሞ በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጠ ነው የሚነግረን።
ራዕ 11፡15 ደግሞ “ የዓለም መንግሥት የጌታችንና የእርሱ ክርስቶስ መንግስት ሆነች፤ እርሱም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሳል።” መንግስቱ የጌታችንና(አብ) የእርሱ ክርስቶስ(ወልድ) ሆነች ብሎ ብዙ ቁጥር ይናገርና መልሶ እርሱም ብሎ ነጠላ ያደርገዋል። እንግዲህ ሁለቱም አንድ ካልሆኑ ሀሳቡ እርስ በርሱ ይጋጫል።

ራእ 22፡1” …ከእግዛብሔርና ከበጉ ዙፋን …” እዚህ ጋር እናስተውል ከእግዛብሔርና ከበጉ ዙፋኖች አላለም ያለው ዙፋን ነው(ነጠላ ቁጥር)። ስለዚህ ዙፋኑ ሁለቱም አንድ ስለሆኑ በነጠላ ነው የተጠራው። 

በአጠቃላይ ከእግዛብሔር ቃል እንደምንረዳው እየሱስ ፍፁም አምላክ ፍጹም ሰው ነው።

ቆላ 2፡9”የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል በእርሱ ይኖራል።” ይላል። ሐዋርያው ጳውሎስ በእንግሊዘኛው “fullness of deity” በአማርኛ “የመለኮት ሙላት” በግሪኩ “theotetes” ማለት የመለኮት ማንነት(ተፈጥሮ)(ባህርይ)(divine nature)በእርሱ ውስጥ በሙላት ይኖራል እያለን ነው። የእግዛብሔር ጥቂት ማንነት ብቻ አይደለም በእሱ ውስጥ ያለው የእግዛብሔር ማንነት ሁሉ በሙላት በሱ ውስጥ አለ እያለን ነው። ይህ ሙሉ የሆነ የመለኮት ማንነት ተፈጥሮ ነው እየሱስን ፍጹም አምላክ ያሰኘው። ደግሞ ይኖራል ነው የሚለው(present tense)ያሁንን ጊዜ ነው።   

ፍፁም አምላክ
ፍፁም ሰው
ሰግደውለታል፤ አምልከውታል።(ማቴ 2፡2,11፤ 14፡33፤ 28፡9)
ወደሱ ተፀልዮአል (ሐዋ 7፡59፤ 1ቆሮ 1፡2)
አምላክ(God) ተብሎ ተጠርቷል (ዮሐ20፡28፡ ዕብ1፡8)
የእግዛብሔር ልጅ ተብሎ ተጠርቷል (ማር 1፡1)
ሐጢአት የለበትም ( 1ጴጥ 2፡22፤ ዕብ 4፡15)
ሁሉንም ያውቃል (ዮሐ 21፡17)
የዘላለም ሕይወት ይሰጣል (ዮሐ 20፡28)
የመለኮት ሙላት ሁሉ በእሱ ውስጥ ይኖራል (ቆላ 2፡9)
አባቱን አምልኮአል (ዮሐ 17)
ወደ አባቱ ፀልዮአል (ዮሐ 17፡1)
ሰው ተብሎ ተጠርቷል (ማር 15፡39 ፤ ዮሐ 19፡5)
የሰው ልጅ ተብሎ ተጠርቷል (ዮሐ 19፡35-37)
ተፈትኖአል (ማቴ 4፡1)
በጥበብ አድጓል (ሉቃ 2፡52)
ሞቷል (ሮሜ 5፡8)
ስጋና አጥንት ነበረው (ሉቃ 24፡39)

No comments:

Post a Comment