Saturday, February 22, 2014

"ለሰይጣን አሳልፌ የሰጠሗቸው" ሲል ምን ማለቱ ነው?

1.ጢሞ.1:20 "ከእነዚያም እንዳይሳደቡ ይማሩ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፌ የሰጠሗቸው ሄሜኔዎስና እስክንድሮስ ናቸው::" ይላል:: ለመሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ለሰይጣን አሳልፌ የሰጠሗቸው" ሲል ምን ማለቱ ነው? በተጨማሪም 1.ቆሮ.5:5 ላይ "እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው::" ማለትስ ምን ማለት ነው?

መጀመርያ 1.ጢሞ.1:20ላይ ስማቸው የተጠራው ሄሜኔዎስና እስክንድሮስ ምንድ ነው ያደረጉት? ምንድነው የተሳደቡትስ? ብሎ መጠየቅ ጥሩ ነው:: 2 ጢሞ 2:17-18 ብናይ እንዲህ ይላል 
ከእነርሱም ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ ናቸው፤ እነዚህም። ትንሣኤ ከአሁን በፊት ሆኖአል እያሉ፥ ስለ እውነት ስተው፥ የአንዳንዶችን እምነት ይገለብጣሉ።

ስለዚህ የአነዚህ ሰዎች ስድብ የተባለው የክህደት ትምህርት በቤተ ክርስትያን ውስጥ ስለተናገሩ ነው:: ስለዚህ እነዚህን ከወንድሞች ህብረት እንዲወጡ ነው ሐዋርያው እያዘዘ ያለው:: ምክንያቱም ሰህተትን እያስተማሩ (እየተሳደቡ blasphemy) ስለሆነ:: ይህ ማለት እንግዲህ አብረው አግዝአብሔርን አያመልኩም: ከበተክርስትያን አባልነት ተባረዋል: ከወንድሞች ጋር ሕብረት የላቸውም ማለት ነው:: ይህ ደግሞ ለሰይጣን ጥቃት ያጋልጣቸዋል:: ይህም ደግሞ በስጋቸው ላይና በሕይወታቸው ላይ መከራን ያበዛል::

እንዲሁም 1.ቆሮ.5:5 ይህን ነገር (እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው:) ሐዋርያው ሲናገር እናያለን:: ከላይ ጀመረን ስናነብ ይህን ፍርድ የሰጠበት ሰው ያረገውን ጥፋት እናያለን

በአጭር ቃል በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው፥ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና። እናንተም ታብያችኋል፤ ይልቅስ እንድታዝኑ አይገባችሁምን? ይህን ሥራ የሠራው ከመካከላችሁ ይወገድ። እኔ ምንም እንኳ በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፥ ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን እንደዚህ በሠራው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ፤ እናንተና መንፈሴም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር ተሰብስበን፥ መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው። 


እንግዲህ ይህም ሰው ትልቅ በአሕዛብ እንኳ የማይገኝ ዝሙት የሰራ ሰው እንዳለ ተናግሮ: ይህንንም ሰውከመካከላችሁ ይወገድእያለ ነው:: ደግሞ በመከራ ውስጥ አልፎ እንዲማርመንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው።ይላል:: ይበልጥ ሲያብራራው ደግሞ ቁጥር 11 ላይ እንዲህ ይላል

አሁን ግን ወንድሞች ከሚባሉት አንዱ ሴሰኛ ወይም ገንዘብን የሚመኝ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካር ወይም ነጣቂ ቢሆን ከእርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ፤ እንደነዚህ ካለው ጋር መብል እንኳን አትብሉ።


ስለዚህ "ስጋውን ለሰይጣን አሳልፌ ሰጥቸዋለሁ" ሲል ከማህበራችቸሁ አውጡት: አትተባበሩት: መብል እንኳ አብራችሁ አትብሉ: እያለ ነው:: ሲቀጥልም ስለእንደዚህ አይነት ፍርድም ሲናገር በቁጥር 12-13 እንዲህ ይላል

በውጭ ባሉ ሰዎች ላይ መፍረድ ምን አግዶኝ? በውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱምን? በውጭ ባሉቱ ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት።


ይህ ፍርድ የሚሰጠው በውስጥ ላሉ የቤተክርስትያን አባሎች እንጂ ለማያምኑ ሰዎች አይደለም:: በመቀጠልም እንደዚህ አይነት ፍርድ እስከመጨረሻው የሚፈረድም አይደለም:: 2 ቆሮ 2:6-11 እንደምናየውም ያጠፋውን ሰው አስተምሮ ለመመለስ ነው...

እኔስ ባሳዝናችሁ፥ እንግዲያስ በእኔ ምክንያት ከሚያዝን በቀር ደስ የሚያሰኘኝ ማን ነው? ደስ ሊያሰኙኝ ከሚገባቸውም በመምጣቴ ኀዘን እንዳይሆንብኝ ይህንኑ ጻፍሁላችሁ፥ ደስታዬ የሁላችሁ ደስታ ነው ብዬ በሁላችሁ ታምኜአለሁና። በብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት በብዙም እንባ ጽፌላችሁ ነበርና፤ ይህም እናንተን አብዝቼ የምወድበትን ፍቅር እንድታውቁ እንጂ እንዳሳዝናችሁ አይደለም። ነገር ግን ማንም አሳዝኖ ቢሆን፥ እንዳልከብድባችሁ፥ በክፍል ሁላችሁን እንጂ እኔን ያሳዘነ አይደለም። እንደዚህ ላለ ሰው ይህ ከእናንተ የምትበዙት የቀጣችሁት ቅጣት ይበቃዋልና እንደዚህ ያለው ከልክ በሚበዛ ኀዘን እንዳይዋጥ፥ ይልቅ ተመልሳችሁ ይቅር ማለትና ማጽናናት ይገባችኋል። ስለዚህ ከእርሱ ጋር ፍቅርን እንድታጸኑ እለምናችኋለሁ፤ ስለዚህ ደግሞ ጽፌ ነበርና፤ በሁሉ የምትታዘዙ እንደ ሆናችሁ የእናንተን መፈተን አውቅ ዘንድ አሳቤ ነበር። እናንተ ግን ይቅር የምትሉትን እኔ ደግሞ ይቅር እለዋለሁ፤ እኔም ይቅር ካልሁ፥ ይቅር ያልሁትን ስለ እናንተ በክርስቶስ ፊት ይቅር ብዬአለሁ፥ በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና።


በገላ 6:1 ላይ እንደምናነበውወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።እንደዚህ ያለውን ጥፋተኛ ሰው ለማጥፋት ሳይሆን ከስህተቱ እንዲማር እንዲቃና በንስሃ እንዲመለስ ነው ዋናው አላማ መሆነ ያለበት::

ለማጠቃለልይማሩ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፌ የሰጠሗቸውወይምለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥማለት መጀመርያ የቤተክርስታያን አባል ለሆኑ ሰዎች ሲሆን: ቀጥሎም ደግሞ ከሕብረት ውስጥ አንዲወጡና በመከራና ስቃይ ውስጥ አልፈው በንሰሃ እንዲመለሱ ሲሆን: ይህም ቀጣት ደግሞ ለተወሰነ ጊዜ እንጂ ለሁልጊዜ እንዳልሆነ ነው ከእግዝአብሔር ቃል የምንማረው::

No comments:

Post a Comment