አንድ ወንድሜ እነዚህን ጥቅሶች ጠቅሶ በጌታችን “ፃድቃን” የተባሉት ቅዱስ ጳውሎስም “ሃጥያአት ያልሰሩ” ያላቸው እነማንን ነው?? ጴንጤዎች እስቲ መልሳችሁን አስነብቡን ብሎ ጠየቀ::
ሮሜ 5:14” ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና።”
ሉቃ 5:32 “ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው።”
ሉቃ 15:7 “እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።”
የእኔ መልስ ይኸው…
መጀመርያ ከወንድሜ አጠያየቅ እንደተረዳሁት ለእሱ ሃጥያአት ያልሰሩ ሰዎች አሉ:: እንዲሁም ደግሞ ፈሪሳውያን ፃድቃን ናቸው::
መፅሐፍ ቅዱስ ሲናገር ግን ሁሉም ሰው ሃጥያአት አንደሰራ ነው የሚናገረው
ሮሜ 3:11 “ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፤ አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፤ ሁሉ ተሳስተዋል፥”
እንግዲህ መፅሐፈ ቅዱስ እርስ በእርሱ ስለማይጋጭ ፃድቅ አንድም እንደሌለ ከተናገረ በቃ የለም ማለት ነው:: ታዲያ ይህ ነገር እላይ ከተጠቀሱት ጥቅሶች ጋር እንዴት ነው የሚስማማው የሚለውን መጠየቅ አግባብ ነው:: ሰለዚህ ከጥቅሶቹ ተነስተን አብረን አንየው…
ሮሜ 5:14 “ ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና።”
ይህንን ጥቅስ ለመረዳት መጀመርያ ከእዚህ ጥቅስ በፊት የተፃፈውን ማንበብ ይህን እንድንረዳ በጣም ይጠቅመናል
ቁጥር 13 “ሕግ እስከ መጣ ድረስ ኃጢአት በዓለም ነበረና ነገር ግን ሕግ በሌለበት ጊዜ ኃጢአት አይቈጠርም፤”
እንግዲህ ከእዚህ ጥቅስ እንደምንረዳው ሃጥያአት እንደሃጥያአት እንዲቆጠር ሕግ የሚባል ነገር መኖር አለበት:: ሕግ ደግሞ የተሰጠው በሙሴ ጊዜ ነው:: ስለዚህ ምንም እንኳ ቃሉ እንደሚለው ከሕግ በፊት በአለም ውስጥ ሃጥያአት ቢኖርም ሃጥያአት እንዲቆጠር ግን ሕግ የሚባል ነገር መኖር አለበት ቃሉ እንደሚለው:: ሕግ ከመሰጠቱ በፊትም ቢሆን ግን ሃጥያአት በአለም ውስጥ ነበር:: ሕግ ከሌለ ይህ ሐጥያአት ከየት መጣ?? አሁንም ከእዚሁ ምእራፍ ሳንወጣ መልሱን እናገኘዋለን
ቁጥር 12 “ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፤”
ከእዚህ በተጨማሪ ከሌላ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል እንደምንረዳው ለአዳም አንድ ትእዛዝ ተሰጥቶት ነበር ያንንም ትእዛዝ አዳም ተላለፈ:: በእዚህም ምክንያት ሃጥያአት ወደአለም ገባ:: ሰዎችም ከእዚህ የተነሳ ሞት ተፈረዳባቸው ::
ስለዚህ ሮሜ 5:14 ላይ
“ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤”
ሲል እስከ ሙሴ ድረስ የነበሩት ሰዎች የሚመሩበት ሕግ ባይሰጣቸውም ከእዚያ የተነሳ የሚበድሉት በደል ወይም ሃጥያአት ባይቆጠርባቸውም ከአዳም መተላለፍ የተነሳ በእነሱም ላይ ሞት ነግስዋል:: ስለዚህ ሃጥያአት ያልሰሩ ሲል ፃድቃን ናቸው እያለ ሳይሆን ሕግ በሌለበት የሚፈፅሙት ሃጥያአት እንደሃጥያአት አልተቆጠረባቸውም እያለ ነው:: መፅሐፍ እንደሚል ፍጡር ሁኖ ሃጥያአት ያልሰራ አንድም ሰው የለም ወይም በሌላ አነጋገር ጻድቅ አንድም ሰው የለም::
ወደሁለተኛው ጥቅስ ስንሄድ…

እዚህም ቦታ ኢየሱስ ጻድቃን አሉ እያለ ሳይሆን ከእዚያው ምዐራፍ ላይ እንደምነረዳው ራሳቸውን ፃድቃን ብለወ የሚጠሩ ፈሪሳውያን ስላሉ እነሱም ደግሞ ሃጥያአተኛ ከሚባሉት ጋር ሲበላ ሲጠጣ ሲያዩትና በእዚህ የተነሳ ሲከሱት የተናገራቸው ነው
እስቲ ታሪኩን አብረን እንየው…
ቁጥር 27-32 “ከዚህም በኋላ ወጥቶ ሌዊ የሚባል ቀራጭ በመቅረጫው ተቀምጦ ተመለከተና። ተከተለኝ አለው። ሁሉንም ተወ፤ ተነሥቶም ተከተለው። ሌዊም በቤቱ ታላቅ ግብዣ አደረገለት፤ ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጠው የነበሩ ከቀራጮችና ከሌሎች ሰዎች ብዙ ሕዝብ ነበሩ። ፈሪሳውያንና ጻፎቻቸውም በደቀ መዛሙርቱ ላይ። ስለ ምን ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር ትበላላችሁ ትጠጡማላችሁ? ብለው አንጐራጐሩ። ኢየሱስም መልሶ፦ ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤
ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው።”
እንግዲህ ከታሪኩ ሰንነሳ ፈሪሳውያን ራሳቸውን ጻድቅ ነን ብለወ የሚያስቡና መሲህ አያስፈልገንም የሚሉ ስለሆኑ እና ቀራጮችን ደግሞ ሃጥያአተኛች ናቸው ብለው ራሳቸውን ከእነሱ ስለሚያገሉ እየሱስ የተናገረው ነገር እንጂ ፈሪሳውያንን ፃድቅ ናቸው እያለ አይደለም
ይኼኛው ሶስተኛ ጥቅስ ተመሳሳይ መልስ ነው ያለው…
ሉቃ 15 7 እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።
ቁጥር 1-7 “ቀራጮችና ኃጢአተኞችም ሁሉ ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር። ፈሪሳውያንና ጻፎችም። ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል ከእነርሱም ጋር ይበላል ብለው እርስ በርሳቸው አንጐራጐሩ። ይህንም ምሳሌ ነገራቸው እንዲህ ሲል፦ መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው?
ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል፤ ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ። የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል። እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።”
ለማጠቃለል እነዚህ ሶስት ጥቅሶች ላይ “ሃጥያአት ያልሰሩ” “ፃድቃን” ሰዎች አሉ እያለ አይደለም ጠያቂው በእዚህ መረዳት እንደጠየቀ ገብቶኛል መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ አይልም

No comments:
Post a Comment