ቅዱስ
ቁርባን ወይም የጌታ ራት የከበረ በስርዐት የሚፈፀም ህይወትን የምንካፈልበት መንፈሳዊ ስርዓት ነው፡፡ በጌታ ራት ጊዜ የሚበላውን በመብላት የሚጠጣውን በመጠጣት የዘላለም ሕይወት ይገኛል
ብለን አናምንም ምክንያቱም መፅሐፍ ቅዱሳዊ ስላልሆነ መፅሐፍ ሲናገር ድነት የሚገኘው “ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።”
ኤፌ 2 8-9 ይላል እንጂ በመብላትና በመጠጣት በስራ ይገኛል አይልም
ኢየሱስ
ክርስቶስ እንዲህ ብሎ ነበር…
ሉቃ 22:19-20 “እንጀራንም አንሥቶ አመሰገነ ቆርሶም ሰጣቸውና። ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ። እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ፦ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው።”
ሐዋርያው
ጳውሎስ ሲናገር…
1 ቆሮ 11:23-26 “ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ የሰጠሁትን እኔ ከጌታ ተቀብያለሁና፤ ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት በዚያች ሌሊት እንጀራን አንሥቶ አመሰገነ፥ ቆርሶም። እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ። እንደዚሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን ደግሞ አንሥቶ። ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው፤ በጠጣችሁት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ። ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ፥ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና።”
እንጀራውን በተመለከተ ለምን ብሉ እንዳላቸው ኢየሱስ ሲናገር… “ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ።” ሐዋርያውም ሲናገር ኢየሱስ ለምን ብሉ ብሎ እንጀራ እንደሰጣቸው… ““ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ የሰጠሁትን እኔ ከጌታ ተቀብያለሁና፤ ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበት በዚያች ሌሊት እንጀራን አንሥቶ አመሰገነ፥ ቆርሶም። እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ።
ሁለቱም ጋር የሚለው “ለመታሰቢያ” አድርጉት ነው:: ደሙ በተመለከተ ደግሞ ኢየሱስ ሲናገር…”እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ፦ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው።” ሐዋርያው ሲናገር ደግሞ… “እንደዚሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን ደግሞ አንሥቶ። ይህ ጽዋ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው፤ በጠጣችሁት ጊዜ ሁሉ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ። ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ፥ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና።”
ሁለቱም በተግባር ሲናገሩ ያሉት ይህንን ሥርዐት በመፈፀማችን የምናደርገው ነገር መታሰቢያ ነው ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን መናገራቸን ነው እንጂ ይህን በመብላታችንና በመጠጣታችን የዘላለም ሕይወት እንደምናገኝ አልተናገሩም
ብዙ
ጊዜ ሰዎች የጌታን ስጋና ደም በመብላታችንና በመጠጣታችን ዘላለም ሕይወት እናገኛለን ብለው መከራከርያ የሚያነሱት በዮሐንስ 6 ላይ
ያለውን ነው:: እሱን እንመልከተው…
ስጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው እኔም በመጨረሻቀ ቀነ አስነሳዋለሁ (ዮሐ 6:56)
ይህም ሃሳብ እጅግ ሰፊ ቢሆንም አጠቃላይ ሃሳቡን ልናገር ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ሲል ምሳሊያዊ አነጋገር ነው ወይስ መብላትን እና መጠጣትን ለማሳየት ነው??? ለእኔ የበላ እና የጠጣ ሲል ምሳልያዊ አነጋገር እንጂ የዘላለም ሕይወት ከመብላት ጋር እና ከመጠጣት ጋር የተያያዘ ነው ብዬ አላምንም ምክንያቴን ላስረዳ….
ይህን የዮሐንስ 6 ከሰዎቹ ጋር ያለውን ውይይት ሲጀመር እንዲህ ይላል
ቁጥር 28-29 “እንግዲህ። የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ? አሉት። ኢየሱስ መልሶ፦ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው አላቸው።”
ቁጥር 28-29 “እንግዲህ። የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ? አሉት። ኢየሱስ መልሶ፦ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው እንድታምኑ ነው አላቸው።”
ከእዛ ሰዎቹ እንድናምንህ ምን እናርግ ብለው ጠየቁት እሱም ስለአባቶቻቸው ከሰማይ እግዝአብሔር እንጀራ ሰጥትዋቸው እንደበሉ እና ያንን የሰጣቸው ሙሴ እንዳልሆነ ከነገራቸው በሁዋላ እውነተኛው እንጀራ ከሰማይ የሚወርድ ለአለምም ሕይወት እንደሚሰጥ ከተናገረ በሁዋላ እነሱም የሚናገረው ስለሚበላ እንጀራ መስልዋቸው ይህንን እንጀራ ስጠን ሲሉት እሱ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው…
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም። ነገር ግን አይታችሁኝ እንዳላመናችሁ አልኋችሁ። … ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።… ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና።ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።… ብሎ ሰዎቺ ሲያንጎራግሩ ሰምቶ ሲቀጥል እንዲህ አለ … ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው። ነገር ግን ከእናንተ የማያምኑ አሉ።
እንግዲህ ይህን ውይይት ከሰዎቹ ጋር ሲጀምር ስለእምነት ነው የተናገረው ሲጨርስም የጨረሰው በእምነት ነው:: ኢየሱስ እየተናገረው ያለው የዘላለም ሕይወት የሚገኘው በሚበላ ሥጋ እና በሚጠጣ ደም ሳይሆን እሱ ስለኛ ስለሚቆስለው ሥጋው ስለሚፈሰው ደሙ ባጠቃላይ ስለመስቀል ሥራው እና ስለሞቱና ትንሣኤው:: በእዛም በእምነት ስለሚገኘው ፀጋ ነው:: ከእዚህም የተነሣ ስለምናገኘው የዘላለም ሕይወት ነው::
ለመጨመር ያህል…
"ከደቀ መዛሙርቱም ብዙዎች በሰሙ ጊዜ። ይህ የሚያስጨንቅ ንግግር ነው፤ ማን ሊሰማው ይችላል? አሉ።
ኢየሱስ ግን ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ እንዳንጐራጐሩ በልቡ አውቆ አላቸው። ይህ ያሰናክላችኋልን? እንግዲህ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደ ነበረበት ሲወጣ ብታዩ እንዴት ይሆናል?
ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።" እየሰሙ እንዳያደምጡ እያዩ እንዳያስተውሉ በምሳሌ ይናገር የነበረው ጌታ በዚህ ስፍራ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ስፍራዎች ብዙ ምሳሌዎችን እየተናገረ የእግዚአብሄርን መንግስት የማወቅ ምስጢር ለተሰጣቸው ለደቀመዛሙርቱ ግን ይተረጉምላቸው ነበር፡፡
የጌታን ንግግር በመደዴው የሚወስዱ ሁሉ ይሰናከሉበት ነበርና እዚህ ስፍራም ጌታ በተናገረው ብዙዎች ተሰናክለዋል፡፡ ጌታ እየተናገረ የነበረው የለበሰውን ስጋ እና ደሙን እንደሆነ በማሰብ ብዙዎች ወደኋላ ተመልሰዋል፡፡ ከዚህም የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም። ሲል ዮሐንስ ይዘግብልናል፡፡
ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።" እየሰሙ እንዳያደምጡ እያዩ እንዳያስተውሉ በምሳሌ ይናገር የነበረው ጌታ በዚህ ስፍራ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ስፍራዎች ብዙ ምሳሌዎችን እየተናገረ የእግዚአብሄርን መንግስት የማወቅ ምስጢር ለተሰጣቸው ለደቀመዛሙርቱ ግን ይተረጉምላቸው ነበር፡፡
የጌታን ንግግር በመደዴው የሚወስዱ ሁሉ ይሰናከሉበት ነበርና እዚህ ስፍራም ጌታ በተናገረው ብዙዎች ተሰናክለዋል፡፡ ጌታ እየተናገረ የነበረው የለበሰውን ስጋ እና ደሙን እንደሆነ በማሰብ ብዙዎች ወደኋላ ተመልሰዋል፡፡ ከዚህም የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም። ሲል ዮሐንስ ይዘግብልናል፡፡
እንግዲህ ጌታ ስጋ ምንም አይጠቅምም ብሎ ተናግሯል፡፡ ይህ ማለት እያወራ ያለው የለበሰውን ስጋ ስለመብላት ሳይሆን በመስቀል ላይ ስለሃጢአታችን ስለሚሰቀለው ስጋ ስለሚፈስሰውም ደም ነው፡፡ ያንንም ስጋና ደም የምንበላውና የምንጠጣው በእምነት ከእርሱ ጋር ስንዋሃድ በመንፈስ እንጂ ምትሃታዊ በሆነ መንገስ ከህብስትነት ወደክርስቶስ ስጋነት ከወይንነት ደግሞ ወደደምነት ስለሚቀየር አንዳች ነገር አይደለም፡፡
ህይወትን የሚሰጠው መንፈስ እንጂ ምትሃታዊ ለውጥ አይደለም፡፡ እግዚአብሄር መንፈስ የሆነ በመንፈስም የምንገናኘው አምላክ እንጂ ምትሃት አይደለም፡፡
የአዲስ ኪዳን ነገር በሙሉ የእምነት እንጂ የቁስ ስላልሆነ ከቁስና ከሚታይ ስርዓትም ስለወጣን ይህንን በምንካፈልበት ጊዜ ቂጣውን የጌታ ስጋ ጽዋውንም የጌታ ደምን እያሰብን እንወስዳለን፡፡ ምትሃታዊ ለውጥን ግን መጽሀፍ ቅዱስ ሳይሆን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ያስተማረችው ትምህርት ነው፡፡
ስጋ ምንም አይጠቅምም፤ መንፈስ ግን ህይወትን ይሰጣል…..ስጋየን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ህይወት አለው. . . . ህይወትን የሚሰጠው መንፈስ ነው . . . . እኔ የምነግራችሁ ቃል ህይወትም ነው፤ መንፈስም ነው. . . . . ቃሉን በእምነት ስንቀበል በእምነት የሆነውን የመንፈስን ህይወት እንካፈላለን እንጂ ስጋ ምንም አይጠቅምም፡፡ ይህንን ያላቸው ይህ ስጋውን እንበላ ዘንድ እንዴት ይሰጠናል ሲሉ ለነበሩ አላማኞች ሳይሆን ለቅርብ ደቀመዛሙርቶቹ ነበር፤ እነዚያ እንዳሰቡት ስጋ ለምንም አይጠቅምም፤ ይልቁኑ መንፈስ ህይወትን ይሰጣል አላቸው፤ መንፈሱ ደግሞ በቃሉ ውስጥ ስለሚሰራ ይህ የምነግራችሁ ቃል ህይወትም ነው መንፈስም ነው አላቸው፡፡
No comments:
Post a Comment