Thursday, August 28, 2014

በጣም ጥሩ ፅሁፍ ስለ ኢየሱስ ምልጃ በኦርቶዶክስ መምህር part THREE



በጣም ጥሩ ፅሁፍ ስለ ኢየሱስ ምልጃ በኦርቶዶክስ መምህር part THREE

ክርስቲያን ያማልዱት ዘንድ ወደ መላእክት እንዲጸልይ ታዝዋል?

እሺ፥ ወደ ጥያቄው እንመለስ፥ ክርስቲያን ያማልዱት ዘንድ ወደ መላእክት እንዲጸልይ አልታዘዘም፡፡ በተቃራኒው ያለውን ለመረዳት ግን አራት መግለጫዎች ከእግዚአብሔር ቃል ትመለከቱ ዘንድ አሳስባለሁ፡፡
አንደኛ፡- መናፍስትንና የሙታንን ነፍሳት አትጥሩ ሲባል፡- የሙታን ነፍሳት የተባሉት አንድ ጊዜ እንደ እኛ ከአዳምና ከሔዋን ዘር በሥጋና በደም ተወልደው በዚህ ምድር ለዐጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ከታዩ በኋላ ሥጋዎቻቸው በዚህ ምድር ሲቀሩ፥ ነፍሶቻቸው በሲኦልና በገነት ያሉትን ማለቱ እንደ ሆነ ይገባናል፡፡ መናፍስት የተባሉትም አገልጋዮቹን መናፍስት አድርጎ ፈጠራቸው ተብሎ እንደ ተነገረው እግዚአብሔር በትእዛዝ የፈጠራቸውና ከአለመኖር ወደ መኖር ያመጣቸው መላእክት ናቸው (ዕብ. 114)፡፡ እነዚህንም እንዳንጠራቸው (በጸሎት) ተከልክለናል፡፡ ከላይ የሰጣኋችሁን ጥቅሶች እቤታችሁ ስትገቡ መላልሳችሁ አንብቧቸው፡፡
ሁለተኛ፡- ኢዮብን ለማጽናናት በአጠገቡ ከተገኙት አንዱ ኤልፋዝ - መልስ ታገኝ እንደ ሆነ እስኪ ከቅዱሳን ወደ አንዱ ተጣራ በማለት ተናገረው፡፡ እስኪ መልስ ታገኝ እንደ ሆነ ሲል አታገኝም ለማለት ነው፡፡ ምናልባት በሕይወተ ሥጋ ያሉ ሰዎችን መጪ ዕድል ለመጠየቅ በዐጸደ ነፍስ ያሉትንና መናፍስት የሆኑትን መላእክት ብንጠራ፡- የእግዚአብሔር ሕዝብ በቀጥታ ከእስትንፋሱ ይልቅ የቀረበውን አምላኩን (ኤር. 2323) ለምን አይጠራም? በማለት ይመልሱልናል፡፡ ደጋግመን እንደ ገለጽነው መናፍስትንና የሞቱ ሰዎችን ነፍሳት መጥራት ማለት እግዚአብሔር በሚጸየፈውና በከለከለው በሟርት፥ በጥንቆላ፥ በአስማተኛነት ሥራ ላይ መሰማራት ማለት ነው (ኢሳ. 819)፡፡
ሦስተኛ፡- ከኢዮብ አጽናኞች አራተኛው ኤሊሁ ግን ለሰው አማላጅ ሆኖ ሊቆም ስላለው ከአእላፋት ሁሉ ምርጥ ስለሆነው፥ ቤዛ በመክፈልና ሰው የሚከሰስበትን ኀጢአት በማስወገድ ቤዛውን ከፍያለሁና ኀጢአተኛውን ይቅር በለው በማለት ወደ እግዚአብሔር ለመማለድ መካከለኛ ሆኖ ስለሚገለጠው ስለ አንዱ ልዩ መልአክ ተስፋ ለኢዮብ ነገረው፡፡ በመልአከ እግዚአብሔር አምሳያ በብሉይ ኪዳን የተገለጸው መልአክም ለቃልነቱ ከዊን (ቃል ለመሆኑ) እና ለተወላዲነቱ ተስማሚ ሆኖ በተሰጠው በመልእከተኛነት ስም የተገለጸው ወልደ እግዚአብሔር ቃል በሥጋዌ ስሙም ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ በቤዛነቱ ኀጢአትን ከእግዚአብሔርና ከሰው መካከል በማስወገድ ኹለቱን እርስ በርስም ያስታረቀና ሰላምን ያስገኘ ብቸኛ መካከለኛ ነው (ኢዮ. 3323-28 ኢሳ. 5310-12 ሚል. 31 ሉቃ. 2334 ኤፌ. 213-17)፡፡ ነው፡፡ ሁሉ በእርሱ የተደመደመበት ፍጻሜ ነው (ቈላ. 119-22 21-3 9-15)

No comments:

Post a Comment