Thursday, August 28, 2014

በጣም ጥሩ ፅሁፍ ስለ ኢየሱስ ምልጃ በኦርቶዶክስ መምህር part TWO



በጣም ጥሩ ፅሁፍ ስለ ኢየሱስ ምልጃ በኦርቶዶክስ መምህር part TWO
በሕይወት ያሉና የሌሉ ቅዱሳን በአማላጅነት ሥራ ተካፋይነት አላቸው?

የኔታ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅነት ከየት አስከ የት እንደ ሆነ አስረድተዉናል፡፡ የሚታከል ነገር ቢኖር በሕይወት ያሉና የሌሉ ቅዱሳን በአማላጅነት ሥራ ተካፋይነት ቢኖራቸው እንዲያስረዱን ፈቃድዎን እንጠይቃለንአላቸው፡፡
በአዳራሹ ውስጥ ያሉ ሁሉ በጥያቄው መስማማታቸውንና መልሱን ለማወቅ መጓጓታቸውን በምልክትም በቃልም አስረዱ፡፡ አለቃም መነጽራቸውን እያስተካከሉ ቆዩና እንደ ተለመደውመልካምአሉናበሉቃስ ወንጌል 1619-31 የተጻፈውን የራሱን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርት መላልሰን ብናነብ ይህን የተጠየቀውን ርእስ በሚመለከት በተለያየ አቅጣጫ ለሚነሡት ጥያቄዎች ሁሉ አጥጋቢ መልሶችን እናገኛለን፡፡ ባለጸጋው በሀብቱ እግዚአብሔርን ሊያከብርበት ይገባው የነበረውን ችላ በማለት እግዚአብሔር በሰጠው ሀብት ራሱን ብቻ አገለገለበት፤ ምድራዊ ሩጫውን ፈጸመ፤ ሞተ፡፡ ሞት ማለት ብዙዎቹ ይሆንልናል ብለው እንደ ተመኙት ወደ አለመኖር መለወጥ ሳይሆን ቀረና፥ የሥጋና የነፍስ መለያየት ሆነ፡፡ ስለዚህም ሥጋው ሲቀበር ነፍስ ወደሚገባት ሥፍራ ተወሰደች፡፡ በሲኦል የነበረችው የባለጸጋው ነፍስም ቀጥሎ የተመለከቱትን ነገሮች መረዳት ችላ ነበር፡፡
አንደኛ ከሥጋ ከተለየች በኋላ በተሰጣት ስፍራ ያጋጠማት ሥቃይ ይሰማት ነበር፡፡
ሁለተኛ በሲኦል ለመሠቃየት ያበቃት በሥጋ በነበረችበት ጊዜ ማድረግ ሳይገባት ያደረገችውና፥ ማድረግ ሲገባት ያላደረገችው ነገር መሆኑን በሚገባ ዐወቀች፡፡
ሦስተኛ ለሥራዋ ውጤት ተገቢ ሆኖ የሚከፈላት ዋጋ ገና እንደ ሆነና አሁን ያለችበት የፍርድ መጠባበቂያ ማረፊያ ሊለወጥ እንደማይችል ያወቀች ቢሆንም ቢሻሻልላት ኖሮ ተመኝታ ነበር፡፡ ከንቱ ፀፀት!
አራተኛ የእርስዋን ዐይነት ሥራ እየሠሩ በነበረበት ጊዜ ወደ ኋላ የተወቻቸው ወገኖችዋ ዕጣ ፈንታ የእርሷ ዐይነት እንደሚሆን ተረድታ ነበር፡፡ የሚቻል ቢሆንማ እነርሱ እንኳ ጐዳናቸውን እንዲለውጡ ከሞት የተነሣ ሐዋርያ ቢላክላቸው ተመኝታ ነበር፡፡
አምስተኛ ትታው የመጣችው ምድራዊ ነገር ትዝታ አልተረሳትም፡፡ ሆኖም እርስዋ ከተወችው በኋላ የተለወጠ ሁኔታ ቢኖር ኖሮ የምትረዳበት መንገድ አልነበረም፡፡ እነዚህን ነጥቦች እንደ ጨበጥን ወደ ቀረበው ጥያቄ ተመልሰን በአምስት ክፍል የተዘጋጁ መልሶችን እሰጣለሁ፡፡ አሉ አለቃ፥
1. በዐጸደ ነፍስ ያሉ ማለት ምድራዊ ሩጫቸውን ጨርሰው በአካለ ነፍስ ገነት የተወሰዱ ቅዱሳን እንደነርሱ ሩጫቸውን ጨርሰው በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ለገቡ ነፍሳት ይማልዳሉን? ወይም ያማልዳሉን? ቢባል አያማልዱም፤ አይማልዱም የሚል ነው መልሱ፡፡ በሲኦል ያሉ ነፍሳት ከፃዕር የተነሣ በገነት ወደሚገኙ ቅዱሳን ቢጮኹ እንኳ የሚሰጣቸው መልስ ልጄ ሆይ በሕይወትህ ሳለህ የተሰጠህን ዕድል አልተጠቀምህበትም፡፡ ዛሬማ በመከካከላችን ታላቅ ገደል አለ ይባላሉ (ሉቃ. 1625-26)፡፡
2. በዐፀደ ነፍስ ያሉ የቅዱሳን ነፍሳት በዐጸደ ሥጋ ላሉት ይማልዳሉን? ያማልዳሉን? የለም አያማልዱም፤ አይማልዱም፡፡ በሕይወተ ሥጋ ያሉ ሰዎች ዕድል ፈንታ፥ እነርሱ እንዳደረጉት ሁሉ ቅዱሳት መጻሕፍት የሚሰጡትን ምሪት መከተልና መዳን እንደ ሆነ ያውቃሉና (ሉቃ. 1627-29)፡፡
3. በሕይወተ ሥጋ ያሉ ቅዱሳን በዐጸደ ነፍስ ለሚገኙት ይማልዳሉን? ያማልዳሉን? ቢባል አሁንም መልሱ አይማልዱም አያማልዱም ነው፡፡ ሰው የሚድነው በሕይወተ ሥጋ በነበረበት ጊዜ መጻሕፍት በሚሰጡት ትምህርት ልቡ ሲነካና ንስሓ ሲገባ እንደ ሆነ አሳምረው ያውቃሉና (ገላ. 67-8) ወልድ ያለው ሕይወት አለው፥ ወልድ የሌለው የእግዚአብሔር ቁጣ ይኖርበታል እንጂ ሕይወትን የሚያይበት ሌላ እድል አልተሰጠውም (ዮሐ. 336)
ማስገንዘቢያ፡- በእግዚአብሔር አመነ፥ እምነቱም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት የተባለው አብርሃም ከቤተ እስራኤልም ከቤተ አሕዛብም በእምነት ለሚጸድቁ ሁሉ አባት ስለ ሆነ (ሮሜ 41-12) የቅዱሳን ነፍሳት ማረፊያ ሕፅነ አብርሃም፡- የአብርሃም ዕቅፍ (አጠገብ) በመባል ይታወቃል (ማቴ. 810-11 ሉቃ. 1328-29)፡፡ ይህ የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን ቅዱሳን ሁሉ አባት የሆነው አብርሃም ከተማፀነችውና ከወተወተችው ነፍስ ጥያቄዎች አንዱን እንኳ ለመፈጸም ችሎታ እንደሌለው ቢታወቅም፥ ወደ እግዚአብሔር ምልጃ እንኳ አላቀረበላትም፡፡ ወሰኑን ያውቀዋልና፡፡
4. በሕይወተ ሥጋ ያሉት እንደ እነርሱ በሕይወተ ሥጋ ላሉት ይማልዳሉን ምልጃቸውስ ተቀባይነት አለውን ቢባል አዎን፡፡ እንዴታ!
4.1 ያዕቆብ በመልእክቱ 514-20 አንዱ ለሌላው ይጸልይለት ይማልድለት፥ ከስሕተት ይመልሰው፤ እርስ በርስ ተናዘዙ አለ፡፡ መካሪውና ማላጁ፤ እንዲሁም ተመካሪውና ምልጃ አቅራቢው (መስተብቊዕ - አድራሹ) ሁለቱም ወገኖች በሕይወተ ሥጋ ያሉ ናቸው፡፡
4.2 ሐዋርያው ጳውሎስ በሥጋ ሕይወት በነበረበት ጊዜ እንደ እርሱ በሥጋ ሕይወት ለነበሩት ማለት፥ ለምእመናን፥ ለአብያተ ክርስቲያናትም ይጸልይ ነበር፡፡ መስተብቊዕ - ምልጃ ያቀርብ ነበር (ሮሜ 19-10 ኤፌ. 116 ፊል. 14 ቈላ. 13-9 2ጢሞ. 12-3 ፊልሞና 4-5)፡፡
4.3 ይኸው ሐዋርያ የሚጸልይላቸው ምእመናን፥ አብያተ ክርስቲያናት ስለ እርሱና ስለ አገልግሎቱ እንዲጸልዩ (መስተብቊዕ እንዲያደርሱ) ያሳስብ ነበር (ሮሜ 1530 2ቆሮ. 111 ኤፌ. 618-19 ፊል. 119 ቈላ. 43 1ተሰ. 525 2ተሰ. 31 ፊልሞና 22 ዕብ. 1318)፡፡
4.4 ጳውሎስ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ያሉትን ሁሉ ተግባራቸውን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንዲያከናውኑ፥ ይድኑም ዘንድ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲያስተውሉ ምልጃ ያቀርቡላቸው ዘንድ ክርስቲያኖችን አዟል (1ጢሞ. 21-4)፡፡ እርሱም ይህን ኀላፊነት እንደ ተወጣ ገልጿል (.. 2629)፡፡
ሐዋርያው ወደ ጌታ መንግሥት ከመጠራቱ በፊት የመጀመሪያው የጌታ ሰማዕት እስጢፋኖስ በድንጋይ ተወግሮ ሞቶ ነበር፤ ነፍሱን ጌታ ሲቀበላት፥ ሥጋውን ግን ምእመናን ቀብረዉት ነበር (.. 759-60 81-3)፡፡ ለዚህም ጳውሎስ ምስክር ነበር (.. 758-59 83)፡፡ እንዲሁም ይኸው ሐዋርያ ከተጠራ በኋላ የጴጥሮስ ወንድም ያዕቆብ ተሰይፎ (አንገቱን ተቈርጦ) ነበር (.. 121-2) በታሪክም እንደ ተገለጸው ጌታን በሥጋ የወለደችው ድንግል ማርያም፥ ጳውሎስ አብዛኛውን መልእክቶቹን ከመጻፉ በፊት በሞት ከዚህ ዓለም ተለይታ ነበር፡፡ የሐዲስ ኪዳን አማንያንን ጠቀስን እንጂ ጳውሎስ ከላይ የተጠቀሰውን ማሳሰቢያ በጻፈበት ጊዜ የቅዱሳን አባት አብርሃምና ሌሎቹ የብሉይ ኪዳን አማንያን፥ ከሐዲስ ኪዳን መግቢያም መጥምቁ ዮሐንስን ጨምሮ በዐጸደ ነፍስ መኖራቸውን አንዘነጋም፡፡ ሆኖም እነዚህ ቅዱሳን ነፍሳት ይማልዱለት ዘንድ አልጠየቀም፤ በሕይወተ ሥጋ ያሉትን ብቻ ጸልዩልኝ አለ እንጂ፡፡ በሕይወተ ሥጋ ላሉት ራሱ ሲጸልይና ሌሎችም ክርስቲያኖች እንዲጸልዩ ሲያሳስብ ለሞቱት ወገኖቹ ግን አልጸለየም፡፡ ሌሎችንም ይጸልዩ ዘንድ አላዘዘም፡፡
ክርስቲያን በሕይወተ ሥጋ ላሉት ቢጸልይ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የመዳን ዕድል በፊታቸው ስላለ ይህን ዕድል ይጠቀሙበት ዘንድ ጌታ እንዲረዳቸው መጸለይ አስፈላጊነት ይኖረዋል፡፡ በዐጸደ ነፍስ ያሉት ግን ቃሉን ሰምተው የመዳን ዕድል ያመለጣቸው በመሆኑ ስለ እነርሱ ለምን መጸለይ ያስፈልጋል? የቅዱሳንም ነፍሳት ቢሆን እንደ ኀጥኣን ነፍሳት ሁሉ ከፀሓይ በታች በሚደረገው ነገር የመካፈልን ዕድልና ችሎታን ያጡ፥ ሊያስተውሉ ይቅርና ከሞት በኋላ ልጆቻቸው ከብረው ወይም ደኽይተው እንደ ነበሩ እንኳ አያውቁም፡፡ ቀድሞ በምድር የነበሩበትን ሁኔታ ከማስታወስና አሁን ራሳቸው ያሉበትን ሁኔታ ከመረዳት በቀር ከሞቱ በኋላ የቤተ ሰባቸው ሁኔታ ተለውጦ እንደ ሆነ፥ ወይም በዚያው ሁኔታ እየቀጠለ እንደ ሆነ አያዩም፥ አያውቁም (ኢዮ. 1420-22 መክ. 94-6 ኢሳ. 6316)” አሉና አለቃ በረጅሙ ተነፈሱ፤ ሆኖም የድካም ምልክት አልታየባቸውም፡፡
5. “በእግዚአብሔር በኩል ሆኖ ሰዎችን መማለድም አለ፡፡አሉ አለቃ በመቀጠልምከዚህ በላይ 4.1 - 4.4 የዘረዘርናቸው ምልጃዎች በሕይወተ ሥጋ ያሉ ሰዎች እንደነርሱ በሕይወተ ሥጋ ባሉ ሰዎች በኩል ሆነው እግዚአብሔርን ሲማልዱ ነው፡፡ በዚህኛው በአሁኑ ክፍል ግን በሕይወተ ሥጋ ያሉ ሰዎች በእግዚአብሔር በኩል ሆነው በሕይወተ ሥጋ ያሉ ሰዎችን ሲማልዱ፥ ሲለምኑ ይታያሉ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈጸመው ያማስታረቅ አገልግሎት ምክንያትና በኩል እግዚአብሔር ሰዎችን ታርቋል፡፡ ሰውን ከእግዚአብሔር ያጣላው ኀጢአት መደምሰሱን በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ዕርቅና ሰላም መውረዱን ጌታ ከትንሣኤው በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ አብሥሯል (ሉቃ. 2436-47 ዮሐ. 2019-26 ኤፌ. 211-18 ቈላ. 120-22)፡፡
በጌታ የተበሠረውን የዕርቅና የሰላም ዐዋጅ የሰሙት ሐዋርያት ለተተኪዎች አስተላለፉት፡፡ ተያይዞም እኛ ዘንድ ደርሷል፡፡ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን (ማቴ. 2818-20 ማር. 168-19 20 ሉቃ. 11-4 24-46 53 .. 11-8 ዕብ. 23-4)፡፡
ቤተ ክርስቲያንም 2 ሺሕ ዓመታት ያህል ክርስቶስ በታላቅ ኀይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷል፡፡ ከእንግዲህስ ሰላምና ደስታ ሆኗል፤ (ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን አግዐዞ ለአዳም፤ አሰሮ ለሰይጣን እም ይእዜሰ ኮነ ፍሥሓ ወሰላም) በማለት እያወጀች አለች፡፡ ጌታ የሰጣቸውን የዕርቅ ዐዋጅ የያዙ አገልጋዮች ከሐዋርያት ጀምሮ በያለበት ይሰብካሉ፡፡ በእግዚአብሔር በኩልም ሆነው ሰዎችን እየማለዱ፥ እየለመኑ ይገኛሉ፡፡ እግዚአብሔርም የዕርቁን ዐዋጅ ይዘው ከወጡ አስታራቂዎች ጋር ሆኖ (በእነርሱ በኩል) እኔ ይቅር ብያለሁ ታረቁኝ እያለ (በመማለድ) በመለመን ላይ ይገኛል (2ቆሮ. 518-21)፡፡
ማስገንዘቢያ፡-
1. ኀጢአት የማያውቀውን ልጄን ስለ እናንተ ኀጢአት ያደረግሁት እናንተ በእርሱ የኔ ጽድቅ እንድትሆኑ ነውኮ! በእኔ በኩል ይቅር ብያለሁ፥ የዕርቁን ዐዋጅ ስሙና ታረቁኝ እያለ እግዚአብሔር በወንጌላውያን በኩል እየማለደ ሳለ፤ አይ ልጅህ በፈጸመው ሥራ አልታረቅም፤ ሌላ አስታራቂ እፈልጋለሁ ለሚል ሰው ኧረ ምን መፍትሔ ይገኛል?
2. ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ይሉ ዘንድ የዕርቁን ዐዋጅ የሚያሰሙት በሕይወተ ሥጋ ላሉት ኃጥኣን ነው እንጂ በዐጸደ ነፍስ ላሉ ኃጥኣን አይደለም፡፡
3. በሕይወተ ሥጋ ላሉት ኃጥኣንም የዕርቁን ዐዋጅ የሚሰብኩት ያው እንደነርሱ በሕይወተ ሥጋ ያሉ ቅዱሳን ናቸው፡፡
4. አንዳንድ ሰዎች ለክርክር የሚያመጡትን ሐሳብ እዚሁ እንመልከተው፤ ሐዋርያት 12 ነገደ እስራኤል ላይ ትፈርዳላችሁ ተብለዋልና እንዴት ማማለድ አይችሉም? ይላሉ፡፡ ይህ የአስተዳዳሪነት ሹመት ሊሰጣቸው የታቀደው በዳግም ምጽአቱ እንደ ሆነ የሚገልጸውንና ተያይዞ የሚነበበውን ካለማስተዋል የሚነሣ ጥያቄ ነው (ማቴ. 1928 ሉቃ. 2230) ለማስረጃና ለማገናዘቢያም፡-
- የመንግሥትን ሥልጣን ተቀብሎ ለመምጣት የሄደው መኰንን የሰጣቸውን መክሊት ምን ያህል እንዳራቡት አገልጋዮቹን የተቈጣጠራቸው የሾማቸውና የፈረደባቸው ሥልጣነ መንግሥትን ተቀብሎ በተመለሰ ጊዜ ነበር( ማቴ. 2514-33 ሉቃ. 1912-27)፡፡
- ጳውሎስ የተዘጋጀለትን አክሊል የሚረከበው በዚያን ቀን እንደ ሆነ ይናገራል (2ጢሞ. 46-8)፡፡
- እያንዳንዱ ክርስቲያን እንደ ሥራው ሽልማት የሚቀበልበት ቀን የጌታ ዳግም ምጽአት ነው (.. 1730-31 1ቆሮ. 312-13)፡፡
- ዛሬ ክርስቲያኖች የሚረዱት ነገር ቢኖር ከማንቀላፋታቸው በፊትም ሆነ በኋላ ሕይወታቸው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ መሰወሩን ብቻ ነው፡፡
- የተሰወረውም ሕይወታቸው በጌታ ዳግም ምጽአት ከጌታ ጋር ይገለጣል (2ተሰ. 15-10 1ዮሐ. 31-2)፡፡ በቅዳሴ ሠለስቱ ምእትምእንክርዳድ የሌለበት ስንዴ (ነጩ፥ ጥቍሩበአንድነት) በአንዲት መዝገብ ውስጥ ይጨመራል፡፡ ለሁሉ እንደየሥራው እስከሚከፈልበት ጊዜ ድረስ የጻድቃን ነፍሳት በዚያች ይኖራሉ፥ በዚያም ይጠበቃሉስለሚል ዛሬ ዋጋ እንደ ተከፈለ የሚሰበከው ትምህርት ዘግይቶ የበቀለ ዐረም እንደ ሆነ ይታወቃል፡፡ ስለዚህም ጻድቁ ሰማዕቱ እንደ ሞተ አክሊልና ሹመት ተሰጠው ማለት ዘበት ነው፡፡
- በሕይወተ ሥጋ ባሉበት ጊዜ የመጀመሪያውን ርምጃ የሚለውጡና አክሊላቸውን የሚያጡ ይኖራሉ፡፡ ሥራቸውም የሚገመገመው በእግዚአብሔር ዐይን እንጂ በሰው ዐይን አይደለም (1ቆሮ. 924-27 2ቆሮ. 51068 ራእ. 25 311)፡፡
- ሁሉን በሚመረምር በእርሱ ዐይን ሥራዎች ተመርምረው ፍርድ በሚሰጥበት ጊዜ ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘ ወደ እሳት ባሕር ይጣላሉ (ራእ. 2015)፡፡ ጻድቃን ያን ጊዜ በአባታቸው መንግሥት እንደየሥራቸው ይሸለማሉ፥ ይሾማሉ ማለት ነው፡፡ ካሉ በኋላ አለቃ ደምፀ በዝምታ ውስጥ ሆነው ጉባኤውን ሲመለከቱ ዲያቆን በፈቃዱ ቆመና፥መላእክት ያማልዱን ዘንድ ወደ እነርሱ እንድንጸልይ ታዟልንሲል ጠየቀ፡፡
- አለቃም መነጽራቸውን ካሰማመሩና ካስተካከሉ በኋላመልካምአሉና ፊታቸው በፈገግታ ተሞልቶየተዘነጋውን ጉዳይ ዲያቆን በፈቃዱ በማስታወስህ እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ ወደዚህ ጉባኤ መምጣት ከጀመርክ ጊዜው ዐጭር ቢሆንም (ጮራ . 7) ታስተውል ዘንድ ዐይነ ልቦናህን መንፈስ እንዳበራልህ ለመረዳት ችያለሁ፥ ጌታ ይመስገን፡፡

No comments:

Post a Comment