Thursday, August 28, 2014

በጣም ጥሩ ፅሁፍ ስለ ኢየሱስ ምልጃ በኦርቶዶክስ መምህር part one



በጣም ጥሩ ፅሁፍ ስለ ኢየሱስ ምልጃ በኦርቶዶክስ መምህር part one

አለቃ ነቅዐ ጥበብ
የጥያቄና መልስ ጊዜ
ሥርዐተ አምልኮው እንደ ተፈጸመ፥ ለጥያቄዎች መልስ የሚሰጥበት ጊዜ መሆኑን ዲያቆን ምስግና እንዳስታወቀ፥ አለቃ ነቅዐ ጥበብ የተመደበላቸውን ስፍራ ያዙ፡፡ የዛሬው ጥያቄና መልስ በምን ርእስ ላይ እንደሚያተኵር አለቃ ሲጠይቁ፥ ከሳምንታት በፊት ስለ ምልጃ ከተማርን በኋላ ቀሪውን በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን ተብሎ እንደ ነበረ ዲያቆን ምስግና አስታወሳቸው፡፡ አለቃም መነጽራቸውን ካስተካከሉና መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ካመቻቹ በኋላመልካምአሉ፡፡መልካም ባለፈው ጊዜ በሐዲስ ኪዳን ተገቢ ሊቀ ካህናት፥ ነቢይ፥ ንጉሥ፥ መካከለኛ ሆኖ የተሾመው፤ ሰውም እግዚአብሔርም የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንደ ሆነ የሚናገሩትን ጥቅሶች ከመጽሐፍ ቅዱስ እያወጣን ተመልክተን ነበር፡፡ በጥቅሶቹም አስረጅነት በመሐላ የተሾመው፥ ክህነቱ የማይሻረው ዘላለማዊው ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ የመሥዋዕት ማቅረቡን ሥራ ጨርሶ በአብ ቀኝ ተቀምጦ ባለበት ጊዜም እያማለደን መሆኑን የሚያስጨብጥ ግንዛቤ አግኝተን እንደ ነበረ ይታወሳልበማለት ጀመሩ (ጮራ . 4 እና 5)፡፡
ለሚቀጥለው ሐሳብ መግቢያ የሚሆነውን ሲያብራሩም እንዲህ አሉ፤የእስራኤል ልጆች ለእግዚአብሔር የተለየ ሕዝብ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የቃል ኪዳን ማኅተም ይሆን ዘንድ የእንስሳ ደም ተረጭቶባቸው ነበር (ዘፀ. 246-8)፡፡ ደም ሕዝቡ የእግዚአብሔር፥ እግዚአብሔርም የሕዝቡ ለመሆናቸው ጽኑዕ የትስስርና የውርርስ ቃል ኪዳን ማረጋገጫ ነው፡፡ ሆኖም ሕዝቡ በተለያዩ መንገዶች ቢበድሉ በመቅሠፍት እንዳይቀጡና የእግዚአብሔር ሕዝብነታቸውን ዐድሰው እንዲኖሩ የመሥዋዕት ሕግ ተደነገገላቸው፡፡ እስራኤላዊው የእግዚአብሔርን ሕግ ቢተላለፍ የኀጢአት ደመወዝ ሞት ነውና ሞት የሚያስፈርድበትን ኀጢአቱን የሚሸከምለትንና በምትኩ ይሞትለት ዘንድ የሚሠዋለትን እንስሳ ወደ መገናኛው ድንኳን መውሰድ ነበረበት፡፡ ሊቀ ካህናቱ ቢበድል (ዘሌ. 41-12) ማኅበሩ ቢበድል (ዘሌ. 413-21) የማኅበሩ መሪ ቢበድል (ዘሌ. 422-26) የማኅበሩ አባል ቢበድል (ዘሌ. 427-35) እንደ ታዘዘው መፈጸም ነበረባቸው፡፡
ደም ሳይፈስ ስርየት የለምና (ዕብ. 922) ኀጢአተኛ የሆነ ሁሉ በዚህ መንገድ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብበትን ስርየት እየተቀበለ ኅብረቱን ያድስ ነበር፡፡ በኦሪት ዘሌዋውያን ምዕራፍ 4 ውስጥ የየክፍሉ መጨረሻዎች ማለት ቍጥር 20263135 መሥዋዕት በቀረበበት ኀጢአት በደለኛው እንደማይጠየቅ ያረጋግጣሉ፡፡ በብሉይ ኪዳን ለስርየት ማግኛ የፈሰሰው ደም በምሳሌነቱ ያመለክት የነበረው ዘላለማዊውን ስርየት ሊሰጠን አንድ ጊዜ የፈሰሰልንን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ደም ነው፡፡ ስለዚህ በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ለተሠራው ኀጢአት ሁሉ በእግዚአብሔር የተዘጋጀው አማናዊ ማስተስረያና መታረቂያ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ብቻ እንደሆነ ግልጽ ነው (1ዮሐ. 11-10 ኤፌ. 17 ራእ. 15-7 13-14)፡፡
ወንጌላዊ ዮሐንስ የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኀጢአት ሁሉ ያነጻናል ሲል፡-
. የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም የማያነጻው ኀጢአት አለመኖሩን፤
. ማንኛውም ኀጢአት የሚነጻበት ሌላ መንገድ በእግዚአብሔር እንዳልተዘጋጀ አረጋግጦ ይመሰክርልናል፡፡ እንዲሁም እግዚአብሔር የልጁን ደም ለኀጢአት ማስተስረያ አድርጎ በዘመን ፍጻሜ ሲያቆመው
- በፊት የነበረውን ኀጢአትና
- አሁን በዚህ ዘመን የተሠራውን ኀጢአት
በማስተሰረይ ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው (ሮሜ 325-26) አሉና አለቃ አየር ሳቡ፡፡ መነጽራቸውንም እያስተካከሉ አድማጮች እየተከተሏቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ግራ ቀኙን ማተሩ፡፡
ከዚያምመልካምአሉና ቀጠሉየልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኀጢአት ሁሉ ያነጻናል የሚለውንና ለኀጢአት ስርየት የሚፈሰው ደሜ ይህ ነው (ማቴ. 2628) የሚለውን የምሥራች በእምነት የተቀበለ ክርስቲያን ደምህ ባይፈስልኝ ኖሮ ሞት የተገባኝ ኀጢአተኛ ነበርሁ፤ ለኔ የፈሰሰው ደምህ ኀጢአቴን ለመደምሰስ ኀይልና ብቃት እንዳለው አምናለሁ በሚል ልብ ሲታመንበት ታጥቧል፥ ነጽቷል (1ቆሮ. 611)፡፡ ሁል ጊዜ ጥያቄ የሚያስነሣው ጉዳይ ግን ከዚያ በኋላስ ክርስቲያን ኀጢአት ቢሠራ በምን መንገድ ስርየት ያገኛል? የሚለው ነው፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ጊዜ አንጽቶ ወደ ሥራ ላሰማራቸው ደቀ መዛሙርት እግራቸውን ሁል ጊዜ መታጠብ እንደሚያስፈልጋቸው አስተማራቸው፡፡ አይሁዳዊ ወጣ ብሎ ወደ ቤቱ በተመለሰ ቍጥር መላ አካሉን መታጠብ ባያስፈልገውም፥ ከቤቱ በራፍ ካስቀመጣቸው ማድጋዎች ውሃ በመቅዳት በአቧራና በከባቢ ነገሮች በመነካካት በቀላሉ የሚያድፉትን እግሮቹን በመታጠብ እንደሚያነጻ ሁሉ (ዮሐ. 26) አንድ ጊዜ ጌታ ያነጻው ክርስቲያን ከዓለም ጋር በመነካካት የሚያድፈውን እግረ ልቡናውን ሁል ጊዜ እየታጠበ መንጻት እንዳለበት እግርን በመታጠብ ምሳሌ አስተማራቸው (ዮሐ. 1310)፡፡
የቈሸሸ እግረ ልቡናን ለማን ይሰጧል? በምንስ ይነጿል
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስካላጠብሁህ ከኔ ጋር ኅብረት አይኖርህም” (ዮሐ. 138) ሲል ምስጢሩ የተሸፈነ አይደለም፡፡ የትሕትናውን ሥራ ሁላቸው እንዲሠሩ ቢያዛቸውም (ዮሐ. 1312-17) እኔ ካላጠብሁህ ከእኔ ጋር ኅብረት አይኖርህም በማለቱ የቈሸሸውን እግረ ልቡና ማጠብና ማንጻት የሚችለው ራሱ እንደሆነ ማመልከቱ ነበር፡፡ በአባባሉ ኀጢአትን የማንጻት ኀይልም ሥልጣንም ያለው ራሱ መሆኑን በማያወላውል ሁኔታ አስረድቷል (መዝ. (32)5 ኢሳ. 118 4325-26 ማር. 25-12)፡፡ የቈሸሸ እግረ ልቡና የሚነጻው ያው አንድ ጊዜ በፈሰሰው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ብቻ ነው፡፡ ውድ አባቱ ጌታ እግዚአብሔር አብከእንግዲህ ኀጢአትን በሰው ላይ እስከማልቈጥር ድረስ የተቀበልኸውን መከራ፥ ሥቃይና ሞት የፈሰሰውንም ደምህን ለኀጢአት ዕዳ ክፍያ በቂ ነው ብያለሁ፥ ይህም በትንሣኤህ ተረጋግጧል፤ሲል ያወጀበትን ሕጋዊ ሰነድ በማሳየት፥ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተናዛዡን ኀጢአተኛ ተቀብሎ በማማለድ ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቀዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም በዚህ ረገድ የሚያስጨብጠን ምስጢር ጥልቅ ቢሆንም በእምነት ለሚቀበሉት ሁሉ ሽፍን አይደለም፡፡ እስኪ እንደሚከተለው ዘርዘር አድርገን እንከልሰውአሉና አለቃ መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ገልበጥ ገልበጥ፥ የእልባት ምልክቶችን ሰካ - ሰካ እያደረጉ፥ ለሰከንዶች ጸጥ አሉ፡፡ እንደገናምመልካምበማለት ጀመሩ፡፡
. ኀጢአታችንንም ለማስተሰረይ፤ እኛንም ለማማለድና ለማስታረቅ ለሐዲስ ኪዳን ተገቢ ሊቀ ካህናት ሆኖ የተሾመው የኢየሱስ ክርስቶስ ክህነት የማይሻርና ዘለዓለማዊ ነው፡፡ (ወውእቱሰ ይነብር ለዓለም እስመ ኢይሰዓር ክህነቱ፤ ዕብ. 722-24) የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ክህነት እንደነቀያፋ ክህነት ጊዜያዊ የምታደርገውና ሌላ ሊቀ ካህናት የምትሾም አንተ ነህ እንጂ እግዚአብሔርስ ለዘላለም ሾሞታል (መዝ. (110)4 ዕብ. 728)፡፡
. ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሊቀ ካህናትነቱ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ካቀረበ በኋላ ኀጢአትን ለዘላለም በማስተስረይ ለሚያምኑት ሁሉ የዘላለም መዳን ሆነ (ዕብ. 55-10 925-26)፡፡ (ኮነ ዐሳዬ ሕይወትወመድኅነ ዘለዓለም)፡፡
. ዛሬ ዐዲስ አማኞችም ሆኑ የቈሸሸ እግረ ልቡናቸውን በማሳጠብ ኅብረታቸውን የሚያድሱ ክርስቲያኖች ወደ እግዚአብሔር ሊቀርቡ የሚገባው እነርሱንና እግዚአብሔርን በአንድ አካል (በራሱ አካል) ያገናኝ ዘንድ መካከለኛና ሊቀ ካህናት በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ነው (ወይክል አድኅኖቶሙ ለዝሉፉ ለእለ ይቀርቡ ኀበ እግዚአብሔር እንተ መንገሌሁ፡፡ ዕብ. 725)፡፡ ጌታችንም በኔ በኩል ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ አይመጣም (ወአልቦ ዘይመፅእ ኀበ አብ ዘእንበለ እንተ ኀቤየ ዮሐ. 146) ብሏል፡፡ በሌላ በኩል ለመግባት ብትሞክር፥ በሌብነት ተይዘህ እጥፍ ፍርድህን ትቀበላለህ እንጂ አይሳካልህም (ዮሐ. 101-7)፡፡
. ሞትን ድል አድርጎ በአብ ቀኝ የተቀመጠው ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬ ወደ እርሱ የሚቀርቡትን ሁሉ እየተቀበለ በማይሻረው ዘላለማዊ ክህነቱ ያማልዳቸዋል፥ ያስታርቃቸዋል፡፡ (እስመ ለግሙራ ሕያው ውእቱ፥ ወይተነብል ሎሙ፡፡) ዛሬ አያማልድም የምትል ካለህ ከሓዲነትህን ታሳውቃለህ እንጅ መጽሐፍ ቅዱስስ ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል ይልብሃል ዕብ. 725)፡፡
. በየጊዜው መሥዋዕት የማይቀርብ ከሆነ ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ መሥዋዕት ዛሬ እንዴት ስርየትን ይሰጣል፥ ያማልዳል፥ ያስታርቃል ቢባል ተገቢ ጥያቄ ነው፡፡
.1. ጌታችን ራሱን አንዴና ለመጨረሻው መሥዋዕትና ቊርባን አድርጎ ባቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር አብ ከእንግዲህ ኀጢአትን ለዘላለም አላስብም እስኪል ድረስ አርክቶታል፡፡ አልቦ እንከ መሥዋዕት በእንተ ኀጢአት (ዕብ. 924-28 1014-18)፡፡
.2. ጌታችን ዛሬ ስለ እኛ የሚማልደውና የሚያስታርቀን በየጊዜው መሥዋዕትን በማቅረብ ሳይሆን፥ አሁን በላዩ ተጭኖ የማይታየውን፤ አንድ ጊዜ ግን ተሸክሞት የተሠዋበትን ኀጢአት ለዘላለም ማስወገዱን በሚያረጋግጥና ድልን ለሚያበሥር መገለጥ እየታየልን እንደ ሆነ ቃሉ ያበሥረናል (ዕብ. 928)፡፡ ለምን እንዲታይልን አስፈለገ? የኀጢአት ዕዳችን የተከፈለበትን ሕጋዊ ሰነድ ለማሳየት ነዋ፡፡ አባባ! ስለ ሰው ልጆች ኀጢአት ሁሉ የከፈልሁትን ዋጋ ምንነትና መጠኑን የሚያስረዱትን በምስማር የተቦደሱትን እጆቼንና እግሮቼን፥ በጦር የተነደለውን ጐኔን፥ በጅራፍ የተተለተለውን ጀርባዬን ተመልከት! አባት ሆይ! በእሾህ የተወጋውን ራሴንና ግምባሬን፥ በፈጠርሁት እጅ የተጸፋውን ጕንጬን እየው እስኪ! የእርሱን ኀጢአት ለማስወገድ ይህን ሁሉ መቀበሌን አምኖ ይህ ኀጢአተኛ በእኔ በኩል፥ ወደ እኔ መጥቷልና በእኔ ያመነ ሁሉ ይቀበለው ዘንድ ለተገባው የኀጢአት ስርየትና የዘላለም ሕይወት ባለመብት አድርገው እንደ ማለት ነው፡፡
.3 ስለ ሰው ኀጢአት ከጲላጦስ አደባባይ ጀምሮ አስከ ቀራንዮ ኰረብታ የፈሰሰው የልጁ ደም ድምፅ ከጆሮው ትዝታው ከልቡ ሳይጠፋ ምን ጊዜም በእግዚአብሔር ዘንድ የተከበረ ስፍራውን እንደ ያዘ ይኖራል፡፡ ይኖራልና ዐዲስ አማንያንና እግረ ልቡናቸው የቆሸሸባቸው ክርስቲያኖች ይነጹ ዘንድ ሰው ሠራሽ መሥዋዕት ሳያስፈልጋቸው በእምነት በዚሁ ቅዱስ ደም ይረጫሉ፤ ይነጻሉም፡፡ የዕብራውያን መልእክት ፀሓፊ በምድር ገና እየኖሩ ሳሉ በሰማያት ወደ ተጻፈ የበኵራት ማኅበር የተጨመሩትን - ወደ ሐዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ፥ ከአቤል ደም ይልቅ የተሻለ ወደሚናገር ወደ መረጨት ደም ደርሳችኋል ይላል (ዕብ. 1218-24)፡፡
የአቤል ደም የጮኸው፥ ቃኤልን ለመክሰስ ነበረ (ዘፍ. 410)፡፡ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ግን የሚያሰማው ድምፅና የሚፈጥረው ትዝታ ኀጢአትን ለማስተሰረይና ስለ ሰዎች ለመማለድ ነው፡፡ በቅዳሴ ሐዋርያት በመሲሕነት የላክኸው የልጅህ ደም እነሆ ስለ እኔ ይጮኻል (ወናሁ ደመ መሲሕከ ይኬልሕ በእንቲአየ) ሲል ቀዳሹ በመማፀን ያቀረበው ልመና ከዚህ ጋር የሚስማማ ነው፡፡
. ወንጌላዊ ዮሐንስ ምዕመናን ኀጢአትን እንዳይሠሩ ከመከረ በኋላ ኀጢአትን ሠርተው ቢገኙ ግን፡- የኀጢአታችን ማስተስረያ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ዘንድ ጠበቃ ሆኖ እንዳለልን ያስረዳናል (1ዮሐ. 21-2)፡፡ ጠበቃችን ተከራካሪና ተሟጋች ወይም አማላጅ ብቻም አይደለም፤ የኀጢአታችን ማስተስረያ ነው እንጂ (ሮሜ 325)፡፡ በእርሱ በኩል ለሚቀርብ ተናዛዥ ይህማ እኔ የተወጋሁለት፤ የደማሁለት፥ የቈሰልሁለት፥ በመስቀል ጐዳና ሞትን የተቀበልሁለት መሆኑን ያመነ ኀጢአተኛ ነው፡፡ ስርየት በተሰጠበት ኀጢአት ሊጠየቅ አይገባውም በማለት የኀጢአት ማስተስረያ የሆነበትን ማስረጃ በማሳየት ይለፍ ያሰኛል ማለት ነው፡፡ ከኀጢአተኛ ምእመን የሚጠበቀው መናዘዝ ነው፡፡ እንደ ተናዘዘ የኀጢአቱ ማስተስረያ ሆኖ ከአብ ዘንድ በሚገኘው ጠበቃው አማካይነት የስርየት ማረጋገጫና የይለፍ ፈቃድ ይሰጠዋል (1ዮሐ. 17-10)፡፡ እግዚአብሔር አሁንም ለዘላለም ይመስገን፡፡
እንግዲህ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይኖረን ዘንድ ተገቢም አስፈላጊም ሆኖ የተገኘበት ምስጢር ከዚህ የተነሣ ነው (ዕብ. 726-28)፡፡ ሁሉ በራሱ ፍጻሜ የሚያገኝበት ምስጢር በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ አለ፡፡ እንደ ሙሴ ነቢይና መካከለኛ፥ እንደ አሮን በመልከ ጼዴቅ የሹመት ሥርዐት ሊቀ ካህናት እንደሚሠዋ እንስሳ በደሙ ኀጢአትን የሚያስወግድ መሥዋዕት፥ እንደ መገናኛው ድንኳን በሥጋው ሰውንና እግዚአብሔርን ያገናኘ መቅደስ (ዮሐ. 219-22) … ነው፡፡ ሁሉ በእርሱ የተደመደመበት ፍጻሜ ነው (ቈላ. 119-22 21-3 9-15) አሉ::

No comments:

Post a Comment