Friday, July 6, 2012

ሃይማኖት ምንድን ነው????


ሃይማኖት ምንድር ነው? የአማርኛው መዝገበ ቃላት ሁለት ትርጉም ይሰጠዋል::

አንደኛው ትርጉም እምነት ሲሁን በእንግሊዘኛው The Faith
ሁለተኛው ተርጉም ደግሞ የአንድ ሐይማኖት ድርጅትን ነው እንግሊዘኛው Religion.

ይህ በደንብ ከገባን ሌላው በጣም ቀላል ነው::

ጳውሎስ በመልዕክቱ የተናገረው ስለየትኛው ሃይማኖት ትርጉም ነው? (The Faith or Religion)

የአማርኛችን የሃይማኖት ትርጉም አሻሚ ስለሆነ ስለየትኛው እንደተናገረ ለማየት እንግሊዘኛውን ማየት ይበልጥ መረዳት ይጠቅመናል

’’
እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ ……..ጠብቁ ’’ ይሁዳ 20፡፡

Jude 20 “But you, dear friends, by building yourselves up in your most holy FAITH, by praying in the Holy Spirit,”
ልብ በሉ ሃይማኖት ለሚለው የተጠቀመው FAITH የሚለውን ቃል እንጂ Religion አይደለም

’’
ገንዘብ መውደድ የክፋት ሁሉ ስር ነውና አንዳንዶች የህን ሲመኙ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ስቃይ ራሳቸውን ወጉ ’’ 1ጢሞ 610

1 Timothy 6:10 “For the love of money is the root of all evils. Some people in reaching for it have strayed from THE FAITH and stabbed themselves with many pains.”
ልብ በሉ ሃይማኖት ለሚለው የተጠቀመው THE FAITH የሚለውን ቃል እንጂ Religion አይደለም

ስለ ዘመናችንም ሲናገር ’’በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንት ትምህርት እያዳመጡ ሃይማኖት ይክዳሉ’’ 1ጢሞ 42 

1 Timothy 4:1-2 “1 Now the Spirit explicitly says that in the later times some will desert THE FAITH and occupy themselves with deceiving spirits and demonic teachings, influenced by the hypocrisy of liars whose consciences are seared.”
ልብ በሉ ሃይማኖት ለሚለው የተጠቀመው THE FAITH የሚለውን ቃል እንጂ Religion አይደለም

’’
በሃይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ በብርቱ ውቀሳቸው’’ ቲቶ 114 ፡፡

Titus 1:13 “Such testimony is true. For this reason rebuke them sharply that they may be healthy in THE FAITH”
ልብ በሉ ሃይማኖት ለሚለው የተጠቀመው THE FAITH የሚለውን ቃል እንጂ Religion አይደለም

’’
የሃይማኖት ሐዋርያና ሊቀ ካህናት’’ተብሎ መጠራቱን ሊያስታውሱ ይገባል ፡፡ዕብ 1212
Hebrews 12:2 “keeping our eyes fixed on Jesus, the pioneer and perfecter of our FAITH.”
ልብ በሉ ሃይማኖት ለሚለው የተጠቀመው THE FAITH የሚለውን ቃል እንጂ Religion አይደለም

ስለዚህ ቃሉን በደንበ ከተረዳነው መፅሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ሃይማኖት ሲል FAITH እንጂ የሃይማኖት ድርጅትን (Religion) አይደለም የአማርኛ ቋንቋ በደንብ የዳበረ ቢሆን ኖሮ ይበልጥ ነገሩን ያቀለው ነበር

No comments:

Post a Comment