Wednesday, December 12, 2012

አሁን ኢየሱስ ይማልዳል ወይስ ይፈርዳል??


አሁን ኢየሱስ ይማልዳል ወይስ ይፈርዳል??
ስለክርስቶስ ምልጃነት ስንናገር ሰዎች ኢየሱስን ከአብ እንዳሳነስነው ወይም ደግሞ አምላክነቱን ዝቅ እንዳደረግነው ያስባሉ ነገር ግን ኢየሱስ አሁን በሰማይ እንደሚማልድ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተፅፎ እናያለን:: እዚህ ላይ የሚያሳዝነው ነገር ቢኖር ይህንን የተፃፈ እውነታ ለመካድ ይህንን “ይማልዳል”የሚለውን ቃል “ይፈርዳል” በሚለው አንዳንድ የሃይማኖት ክፍሎች በአዲሱ ትርጉማቸው እየቀየሩት ነው::

ይህንን ስለክርስቶስ አሁን በሰማይ ማማለድነትን ለመረዳት መጀመርያ ስለእግዝአብሔር ወልድ በምድር ሲመላለስ እና አሁን ስላለው ማንነት መረዳት እጅግ ይጠቅማል:: ኢየሱስ እግዝአብሔር እንደሆነ መፅሐፍ ቅዱሰ በግልፅ ይነግረናል (ዮሐ 1:1; ሮሜ 9:5) ይህ እግዝአብሔር ወልድ በማርያም አድሮ ከማርያም ሥጋ ወስዶ የሰው ማንነት ሲኖረው የሰውን ተፈጥሮ በነበረው የአምላክ ማንነት ላይ ጨመረ ስለእዚህ ከማርያም ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ኢየሱስ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ነበር::

በፊሊ 2:6-8 ላይ ሲናገር “እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።

እዚህ ጋር ኢየሱስ ልክ እንደእግዝአብሔር አምላክ እንደነበረ ይናገራል ነገር ግን ሰው ለመሆን እራሱን ባዶ እንዳደረገ ደግሞ ይናገራል እዚህ ጋር ልብ ልንል የሚገባን አምላክነቱን መቸም ቢሆን ሊጠፋ ወይም ደግሞ ሊተወው የሚችለው ነገር አይደለም ምክንያቱም ቃሉ እንደሚል እሱ ትላንትም ዛሬም ለዘላለምም ያውነው የሚለወጥ አይደለም:: ስለእዚህ እዚህ ጋር ባዶ አደረገ ሲል ልክ አንደ ሰው ለመመላለስ እራሱን ወይም አምላክነቱን እንደገደበ (restrict) እንዳደረገ ነው የሚገባን በምድር ሲመላለስ ፍፁም አምላክ እንዲሁም ደግሞ ፍፁም ሰው ቢሆንም ነገሮችን ሁሉ ያደርግ የነበረው ልክ እንደ ፍፁም ሰው ነበር ለምሳሌ ተአምራትን ሁሉ ያደርግ የነበረው በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ነበር

ሉቃ 4:1 “ኢየሱስም መንፈስ ቅዱስ መልቶበት ከዮርዳኖስ ተመለሰ፥”
እንዲሁም ደግሞ ኢየሱስ እራሱ በመንፈስ ቅዱስ መቀባቱን ይናገራል::  ሉቃ 4:17-21
“የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ። የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ። መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብም የነበሩት ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር። እርሱም፦ ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ ተፈጸመ ይላቸው ጀመር።”

እንዲሁም ኢየሱስ እራሱ አጋንንትን ያወጣ የነበረው በመንፈስ ቅዱስ ሐይል እንደነበር ይናገራል:: (ማቴ 12:28)

ከእዛ በተረፈ ሐዋርያው ጴጥሮስ ሲናገር በሐዋርያት ሥራ 2:22 ኢየሱስ ተአምራትን ያደርግ የነበረው በእራሱ ሳይሆን በእግዝአብሔር (መንፈስቅዱስ) አማኝነት እንደነበር ይናገራል…”የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤”

እንዲሁም አሁንም ደግሞ ጴጥሮስ ሲናገር በሐዋርያት ሥራ 10:38 “እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤”    

ስለእዚህ በፍፁም ሰው ማንነቱ ነበር በምድር ይመላለስ የነበረው ምነም እንኳ እንዲሁም ፍፁም አምላክ የነበረ ቢሆንም

በእዚህ ፍፁም ሰው ማንነቱ ወደአባቱ ፀልይዋል ለእራሱም ሆነ ለደቀመዛሙርቱ ምልጃን አቅርብዋል

ማማለድ ወይም ምልጃ
ምልጃ ማለት ማሰታረቅ ስለሌላ አካል መለመን ማስማማት ማለት ነው፡ አንዳንድ ሰዎች የኢየሱስን አማላጅነት ላለመቀበል ሲጣጣሩና መጽሐፍ ቅዱስን ለማጋጨት ጥረት ሲያደርጉ ይታያሉ፡ አንዳንዶቹ ደግሞ በምድር ላይ እያለ አማልዷል ካረገ በኋላ ግን አያማልድም ይላሉ፡ እስቲ ስለእዚህ ስለኢየሱስ የማማለድ ተግባር የእግዚአብሔር ቃል ምን እንደሚል እንመልከት::

ኢየሱስ እንደ አምላክነቱ ጸሎትን የሚሰማ ተማላጅ አምላክ ቢሆንም እንደ ሰውነቱ በግብሩ (ሊቀ ካህንነቱ)
ደግሞ ሥለ እኛ በሰማያዊት መቅደስ ያለ ብቸኛ አማላጅ/አስታራቂ/መካከለኛ ነው፡  በአሁኑ ሰአት ያለውየኢየሱስ ምልጃ በምድር ላይ ከነበረበቱ ልዩ የሚሆነው ምልጃው በተፈጸመ ሥራው ስለ እኛ በአብ ዘንድ አንዴ የቀረበ ብቻ መሆኑ ነው(ዕብ. 9፡24፣28):: የክርስቶስ የማዳን/የማስታረቅ ሥራ በመስቀል ላይ ያለቀ ቢሆንም ስለታረቁት ወይም በእሱ የመስቀል ሥራ አምነው ልጅ ስለሆኑት ግድ (care)ማድረጉን አልተወም ለእዚህ ነው ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ 5:10 እንዲህ ያለው
ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤”

ክርስቶስ ያማለደው በሥጋው ወራት (በምድር ሳለ) ብቻ ነውን???

በስጋው ወራት የክርስቶስ ምልጃ
ኢየሱስ በምድር ላይ በሰነበተበት የ3አመት ተኩል ጊዚያት፣ በተለያየ ሁኔታ የምልጃ ሥራን ሰርቷል፡

ጌታ ኢየሱስ በምድር በነበረ ሰዓት ምልጃ ፈጽሟል ለምሳሌ በዮሐ 17 ጌታ ለደቀመዛሙርቱና ከቃላቸው የተነሳ ለሚያምኑ ሁሉ አንድ እንዲሆኑና በዓለምም እንዲጠብቃቸው ፀልዮል
እንደዚሁም ደግሞ በሉቃስ 22፡31-33 ጌታም «ስምዖን ስምዖን ሆይ እነሆ ሰይጣን እንደስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ እኔ ግን እምነትህ እንደይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ»፡
ይህም ብቻ ሳይሆን እዛው ሉቃስ 23፡34 «አባት ሆይ የሚያደረጉትን አያወቁምና ይቅር በላቸው» ሲል ለሚሰቅሉት ጸልዮል፡ አንግዲህ የዕብራዊያን ጸሐፊ ስለምልጃውና ስለጸሎቱ ሲናገር እንዲህ ይላል ዕብ 5፡7 «እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትና ምልጃን አቀረበ እግዚአብሔርንም ስለመፍራቱ ጸሎቱ ተሰማለት»ይላል፡፡

ነገር ግን አሁን በአባቱ ቀኝ በተቀመጠበት ጊዜ ይህ ቆሟል የሚሉ አንዳንድ ሰዎች አሉ፡


ከእርገት በኋላ የክርስቶስ ምልጃ
እንግዲህ ከላይ እንዳየነው ጌታ በምድር ላይ ጸሎትንና ምልጃን አቅርቧል፡ እንዲሁም የተሰጠውን ተልዕኮ በመፈፀም በምድር አገልግልዋል:: አሁን ደግሞ የዕብራዊያን ጸሐፊ እንደሚናገረው ኢየሱስ በሰማይ በሰው እጅ ባልተሰራችውና በእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው ይለናል (ዕብ 8፣1-2፡)

ለሰማያዊው መቅደስና አውነተኛ ድንኳን ምሳሌና ጥላ በነበረችው ውስጥ በምድር ሊቀ ካህን በዓመት አንድ ጊዜ መሰዋዕት እያቀረበ ህዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር ያሰታርቅ ነበር (ዕብ 9 በሙሉ) ፡ ነገር ግን ኢየሱስ የአዲስ ኪዳን ሊቀ ካህን ሆኖ በሰው እጅ ወደተሰራችው ሳይሆን ወደ እውነተኛይቱ ድንኳን በእግዚአብሔር ፊት አሁን ስለአኛ ይታይልን ዘንድ ወደ እርሷ ገባ ይላል(ዕብ 9፣24):: “አሁን” የሚለው ቃል ማስተዋል አለብን ምክኒያቱም አሁንም በእግዚአብሔር ፊት ስለአኛ የሚታይልን ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡ ሌላም ቦታ በሮሜ 8፣34 ላይ ኢየሱስ ካረገ በኋላ ስለምልጃው ሲናገር፡ «የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኮንንስ ማነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው»፡፡ አዚህ ላይ ደግመን ማሰተማል ያለብን ነገር… ፣የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው፣ የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ሐላፊ ግዜን ሲሆን ፣ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ፣ የሚለው ግን አሁንን ነው የሚያመለክተው፣ በዚህም ላይ ጨምሮ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ይላል::

እንግዲህ እግዚአብሔር ለኤርሚያስ አዲስና የተሻለ ኪዳን አንደሚገባ ተናገሯል ኤር 31፣31-34;
ዕብ 8፣6-13ኤርሚያስ 3፣16:: ስለዚህም እየሱስ የአዲስ ኪዳን ዋስ ሆኗል (ዕብ7፣22)፡: እንዲሁም በዕብራዊያን 7፣25 «ስለእነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህም ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል»፡ ይላል:: አሁንም ሊያማልድ እና ዘወትር የሚሉትን ቃላት የአሁኑን ጊዜ እንጂ ያለፈን ነገር የሚያመለክቱ አይደሉም:: የክርስቶስ ክህነት እንደ አሮን ሞት የሚከለክለውና የሚቋረጥአይደለም (ዕብ.717):፡ ሞት ያላስቀረው 
ሊቀ ካህናችን ስለ ሆነ: ስለ እኛ «...ሲያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል፡: ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ 
እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል(ዕብ 7:25) ይላል::

የኢየሱስ ክህነት/ምልጃ ዘላለማዊና የማይለወጥ ክህነት/ምልጃ ነው 

«… እርሱ (ኢየሱስ) ግን የማይለወጥ ክህነት አለው…(ዕብ 7:24)፡ 
«... የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለእኛየሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው (ሮሜ8:34) ይህ ጥቅስም የክርስቶስ ምልጃ/ክህነት በመሞቱ ምክኒያት ያልተቋረጠ መሆኑን 
በግልጽ ያሳያል:ይህ ክህነት በምድር ላይ እያለ ብቻ ሳይሆን ከትንሳኤው በኋላ በአባቱቀኝ ተቀምጦም ሳለ 
አብሮት ያለ የዘላለምሹመት እንደሆነ ያሳየናል፡ «አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመትለዘላለም ካህን ነህ”(ዕብ.5፡6)::

በዕብ 9፣24 አሁን ስለእኛ ይታያል እንዳለው ሁሉ በአብ ዘንድ ጠበቃችንም ኢየሱሰ ብቻ እንደሆነ ዮሐንስ
በመልዕክቱ«ልጆቼ ሆይ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህንን እጽፍላችኋለሁ፤ ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃአለን፤ እርሱም ጻድቅ የሆነ ክርስቶስ ነው”(1ዮሐ.21) የሚለው ጥቅስ የኢየሱስን የጥብቅና ማዕረግ በጉልህ ያሳያል: ይህም ጥብቅና ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ሰዓት ብቻ ሳይሆን አሁንም ድረስ 
ወደእግዚአብሔር ለመቅረብም ሆነ የኃጢአት ይቅርታን ለመቀበል ትምክህት ሊሆነን የሚችል ጠበቃ ኢየሱስ ብቻ እንደሆነ ያበስረናል፡ ጠበቃ አለን እንጂ ጠበቃ ነበረን አለማለቱን ልብ እንበል፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ብቻ መካከለኛ ነው:መንገድ ነው:በር ነው:: በ1ኛ ጢሞቲዮስ 2፣5 «አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛ ደግሞ አንድ አለ አርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው»፡ ስለዚህ መካከለኛው ኢየሱስ ብቻ ነው:: ጳውሎስም የኢየሱስን መካከለኛነት ሲያበራራ እንዲህ ይላል ኤፌ 2፣15-16«እርሱ ሰላማችን ነውና ሁለቱን ያዋሀደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ህግ ሽሮ በመካከል የለውን የጥል ግድግዳን በስጋው ያፈረሰ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው»፡፡ ኢየሱስም ሲናገር በዮሐ 14፣6 «እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም» ብልዋል:: የዕብራዊያን ጸሐፊ ደግሞ ይህንን ሲደግመው አናያለን
ዕብ 7፣25…ስለዚህም ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል»፣
ሮሜ 3፣24« …በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው በዛነት እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ» ብሏል ጌታም በዮሐ 10፣9« በሩ እኔ ነኝ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል ይገባል ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል»

ከላይ ያሉትን ሃሳቦች በአጭሩ ለማጠቃለል ኢየሱሰ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ የሰው ማነነትን ጨምርዋል ስለእዚህ ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው ነበር በእዚህ የሰው ማነነቱ የተላከበትን ዓላማ በማገልገል ፈፅምዋል አሁን ደግሞ እንዲሁ በእዚህ የሰው ማንነቱ ነገር ግን በከበረ የሰው ማንነቱ ቃሉ እንደሚል በሊቀ ካህነነቱ በሰማይ ያገለግላል ግልጋሎቱም ማማለድ ነው ምልጃው ደግሞ አንዴ በምድር በሰራው ስራ ስለእኛ ለመታየት በአብ ፊት መታየት ነው ለእዚህ ነው ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ 5:10 እንዲህ ያለው  ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤”

ስለዚህ እኛም በምስጋናም በልመናም ሆነ በምልጃ ወደእግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል ስንቀርብ ኢየሱስ ክርስቶስ በአምላክነቱ ከአባቱ ጋር ጸሎታችንን የሚሰማናየሚቀበል ሲሆን በሥጋው ወይም ደግሞ በሰው ማንነቱ ደግሞ ከእኛ ጋር ሆኖ ጸሎታችን ተሰሚነት እንዲኖረው በአባቱ ፊት ስለ እኛ ብቁ ሆኖ የሚታይ አማላጅ ነው እንጂ እሱ በቃላት ስለእኛ መፀለዩ አይደለም ምክንያቱም እሱ እራሱ እንዲህ ብልዋልና-- ዮሐ 16:26 “በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም፤”

ስለእዚህ ኢየሱስ አሁን በሰማይ ይማልዳል እንጂ አይፈርድም በመጨረሻ ግን ኢየሱስ በሰው ማንነቱ ሊፈርድ ይመጣል

ኢየሱስ እንደፈራጅ
በመጨረሻም የሚፈርደውም በአምላክ ማንነቱ ሳይሆን በሰው ማንነቱ ነው:: የሚፈርደው ደግሞ እንደ መፅሐፍ ቅዱስ እግዝአብሔር ወልድ እንጂ እግዝአብሔር አብ አይደለም
·        ዮሐ 5:22 “ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም።”
·        የሐዋ ሥራ 10:42 “ለሕዝብም እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በእግዚአብሔር የተወሰነ እርሱ እንደ ሆነ እንመሰክር ዘንድ አዘዘን።”
·        የሐዋ ሥራ 17:31 “ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።
·        2 ጢሞ 4:1 “በእግዚአብሔር ፊት በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ባለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት፥ በመገለጡና በመንግሥቱም እመክርሃለሁ”

ንደነዚህ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በመጨረሻው ጊዜ የሚፈርደው እየሱስ ነው እዚህ ጋር ለምንድነው እየሱስ ብቻ  የሚፈርደው ብሎ መጠየቅ ነው ጥሩ ነው የእግዝአብሔር ቃል እንዲህ ይለናል
·        ዮሐ 5:27 “የሰው ልጅም ስለ ሆነ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው”
·        ዮሐ 5:22 “ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም።”

ከላይ እንዳየነው እየሱስ ፈራጅ ነው ግን አሁን ነው ፈራጅ ነው ወይስ በመጨረሻ ጊዜ ብሎ መጠየቅ ከስህተት ይጠብቀናል
·        የሐዋ ሥራ 17:31 “ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።
·        ማቴ 25:31-33, “የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።”
·        2 ተሰ 1:5-10 ”ስለ እርሱ ደግሞ መከራ ለምትቀበሉለት ለእግዚአብሔር መንግሥት የምትበቁ ሆናችሁ ትቈጠሩ ዘንድ፥ ይህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ ምልክት ነው። ጌታ ኢየሱስ ከሥልጣኑ መላእክት ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና። እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤  በዚያም ቀን በቅዱሳኑ ሊከብር፥ ምስክርነታችንንም አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ ሊገረም ሲመጣ፥ ከጌታ ፊት ከኃይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።”

ከነዚህ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንደምናየው እየሱስ በመጨረሻው ጊዜ ለፍርድ ይመጣል ታዲያ አሁን ምን እያደረገ ነው መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይለናል አሁን በሰው ማንነቱ ይማልዳል!! (ዕሁፉ ከወንድሞች አና በእራሴ የተቀነባበረ)

4 comments:

  1. የኢየሱስን አማላጅነት የማይቀበሉ ሰዎች መነሻ ችግሮቸው ኢየሱስ ፍፁም ሰው ፍፁም አማላክ ሳይዋሃድ ሳይለያይ እንደሚኖር ሲያምኑ ነው። የኢየሱስ ፍፁም ሰውነት ከተወለደ ጀምሮ ዛሬም በሰማይ መኖሩን ቢያውቁ ማማለዱን አይጠራጠሩም።

    ReplyDelete
  2. እስክትሞት ያማልዳል ብለህ ቆይ፣ ክዚያ በኋላ ደግሞ ምንም መስራት አትችልም። ስለዚህ አማላጅ ነው! እንዳልክ ተዘናግተህ ምንም ሳትሰራ የፍርድ ቀን እንዲመጣ ትጠብቃለህ ማለት ነው። ልቡን ከፍቶ ቃሉን ላዳመጠ “የመዳን ቀን ዛሬ ናት!”። አላውቃችሁም ያለውስ ማንን ነው? የተዘናጉትን (ይማልዳል እንጂ ፍርዱስ ገና ነው ያሉትን) አይደለምን? ነፍሱን ለማዳን የሚወድ ቢኖር በኖኅ ዘመን አሁን አንተ የምተለውን ሲሉ የነበሩ ተቀቅለውም ያለቁ እንደነበሩ ሊያስብ አይገባምን? አንተስ በእነዚህ ነፍሳት መጥፋት የምትጠቀመው አለን?
    ቁም ነገሩ ወዲህ ነው፦ ስህተቱ አላማዋን መዳን ላደረገች ነፍስ ጭንቅ ነው። ምክንያቱም የተሄደው አንድም የራሱ የፈራጁን ክብር ለማሳነስ ስለሆነ፣ አንድም አዘናጊ ስለሆነ ነው፦ ምክንያቱም ሊያማልድ ሳይሆን ሊፈርድ ይመጣልና ይህን አውቆ ተዘጋጅቶ መጠበቁ ይበጃል እንጂ ጊዜው ሲደርስ መከራከር እርባና እንደሌለው ተጽፏል።
    እንግዲህ ከሄኖክ ጀምሮ እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ ስለ ፍርድ ተነገረ። እንግዲህ ቀደም ብሎ “ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ “እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።” የይሁዳ መልዕክት ቁጥር 14። ሙሉ ምዕራፉን ማንበብ እጅግ ጠቃሚ ነው። ይህን ለመቀበል መጽሐፈ ሔኖክን መቀበል ግድ እንዳይል ልብ ይሏል። አንዱ መንፈስቅዱስ የተለያየ ነገር አልተናገረም። ሰዎች፣ ግን ስለ ጊዜያዊው ጥቅም አንድም በተጻራሪው መንፈስ ይህን እንደሚያደርጉ ማሰብ እራስንም ማዳን የባለቤቱ ነው። በመልካሙ ዘር ላይ ከርዳድ መጨመርና ማዘናጋትም የርሱ ስራ ነው።

    ReplyDelete
    Replies
    1. አዎ እስክሞት ድረስ ያማልዳል እላለሁ ቃሉ ስለሚል...

      «ልጆቼ ሆይ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህንን እጽፍላችኋለሁ፤ ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃአለን፤ እርሱም ጻድቅ የሆነ ክርስቶስ ነው”(1ዮሐ.21)

      1ኛ ጢሞቲዮስ 2፣5 «አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛ ደግሞ አንድ አለ አርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው»

      «... የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለእኛየሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው (ሮሜ8:34)

      ዕብራዊያን 7፣25 «ስለእነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህም ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል»፡

      ዕብ 9፣24 "ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ።"

      ከሰው ሎጂክ ወጥተን ቃሉ ላይ ብቻ ካተኮርን ለመረዳት በጣም ቀላል ነው ኢየሱስ አማላጃችን እንደሆነ

      ከሞትን በሁዋላ ግን የሚጠብቀን ፍርድ ብቻ ነው አንድ ሺ ጊዜ ተዝካር ቢደረግልን ከፍርድ አናመልጥም

      Delete
  3. betam des blognal malakewen awekeyalehu betly demo keser melse yesetwe lij yenem tyakewoch neberu keza gn keser yalew demo yaregagetal malet nw letyakeye bezih lek mekse.magegn alemeselegnm neber

    ReplyDelete