Thursday, June 28, 2012

ልሳን (Tongues)



ልሳን (Tongues)

ልሳንን መጀመርያ ላይ የምናገኘው በሐዋርያት 2 ላይ ነው ::
ከእዚያ የምንረዳውም ነገር ሰዎች በልሳን ለመናገር በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ (መሞላት) እንዳለባቸው ነው (ሐዋ 19):: ልሳን ስጦታ ነው::

ይህንን ካወቅን በሁዋላ ሌላው ማየት ያለብን ስንት አይነት ልሳን እንዳለ ነው:: ይህንንም ደግሞ ከመፅሐፍ ቅዱስ ስንረዳ ሁለት አይነት እንዳለ ነው የምንረዳው

(1ቆሮንቶስ 12 10 ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር to another different kinds of tongues)

  1.  የግል ወይም ከሰው ወደእግዝአብሔር
  2.  ለጉባኤ ወይም ለሕዝብ ከእግዝአብሔር ወደ ሰው



የግል ወይም ከሰው ወደእዝአብሔር

ይህንን ልምምድ ብዙ ቦታ ላይ እናየዋለን
·        1 ቆሮንቶስ 14 2 በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል፤
·        ቆሮንቶስ 14 14 15 በልሳን ብጸልይ መንፈሴ ይጸልያል አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው።  እንግዲህ ምንድር ነው? በመንፈስ እጸልያለሁ በአእምሮም ደግሞ እጸልያለሁ፤ በመንፈስ እዘምራለሁ በአእምሮም ደግሞ እዘምራለሁ።
·        ይሁዳ 20 እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥

እነዚህ ከላይ የምናያቸው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሚናገሩት “ስለግል ልሳን” ወይም “ከሰው ወደእግዝአብሔር ስለሚፀለየው” ልሳን ነው::

 ለጉባኤ ወይም ለሕዝብ ከእግዝአብሔር ወደ ሰው

ይህንንም ልምምድ በተለያየ የመፅሐፍ ክፍሎች እናየዋለን
·        የሐዋርያት ሥራ 2:4-8 በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ   ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ   ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ፥ እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ።   ተገርመውም ተደንቀውም እንዲህ አሉ። እነሆ፥ እነዚህ የሚናገሩት ሁሉ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን?   እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋችንን እንዴት እንሰማለን?”

·        1 ቆሮንቶስ 14:26-27 “እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ምንድር ነው? በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለእያንዳንዱ መዝሙር አለው፥ ትምህርት አለው፥ መግለጥ አለው፥ በልሳን መናገር አለው፥ መተርጐም አለው፤ ሁሉ ለማነጽ ይሁን።  በልሳን የሚናገር ቢኖር ሁለት ወይም ቢበዛ ሦስት ሆነው በተራቸው ይናገሩ አንዱም ይተርጉም፤”

ይህ ደግሞ ከእግዝአብሔር ወደ ሰው ለማህበር ወይም ለጉባኤ የሚነገር ልሳን ነው:: ይህ ልሳን ደግሞ ሁለት አይነት ነው
1. ትርጉም የማይስፈልገው የሰው ቋንቋ የሆነ ማለት ተናጋሪው የማያውቀው ነገር ግን ሰሚዎቹ የሚያውቁት ቋንቋ ልክ በሐዋርያት 2 እንዳለው ልምምድ
2. ማንም የማያውቀው ግን ሰዎች እንዲሰሙት እግዝአብሔር ያንን የሚተረጉም ስጦታ በተሰጠው ሰው የሚተረጎም

1 ቆሮንቶስ 12:10 “…ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤”

ስለዚህ ስለልሳን ስንነጋገር ስለየትኛው አይነት ልሳን እየተነጋገርን ከሆነ የምንወያየው ነገሩ ለመረዳት በጣም ይቀለናል::

ከእዛ በተረፈ አሁን በአብዛኛው በጴንጤው ማህበረሰብ የሚታየው ልምምድ የመጀመርያው ወይም ከሰው ወደ እግዝአብሔር የሆነው ነው:: ሁለተኛውም አይነት ልምምድም አለ ግን አንዳንዴ ነው::

ይህኛው ልምምድ በ1ቆሮ12:10 እንደተነገረው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እንጂ በሥራ የሚገኝ አይደለም::

ሌላው በልሳን የሚፀልይ ሰው የሚናገረው ልሳን ይገባዋል ወይ ተብሎ ቢጠየቅ:: መልሱ በልሳን የሚፀልይ ሰው ምን ብሎ እንደሚፀልይ አይገባውም:: ግን እንደተሰጠው ከውስጥ የሚወጣውን በአፉ እየተናገረ ይፀልያል::

ይህ እንዴት ይሆናል ተብሎ ሊጠየቅ ይችላል ለዚህ መልሥ ለማግኘት እነዚህን የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ማየት ይጠቅማል::

1ቆሮ 14 2 በልሳን የሚናገርስ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርም፤ የሚያስተውለው የለምና፥ በመንፈስ ግን ምሥጢርን ይናገራል፤

1ቆሮ 14 14 በልሳን ብጸልይ መንፈሴ ይጸልያል አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው። If I pray in a tongue, my spirit prays, but my mind is unproductive

ሮሜ 8 26 እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤

እንግዲህ ሰው ሲድን የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ ይሆናል:: ይህ የዳነ ሰው ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ አለበት ስጠታን ሃይልን ለመቀበል::

ብዙ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አሉ::

1ቆሮ 12:7-11 “ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም 
ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና፥
ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል፥ 
ለአንዱም በዚያው መንፈስ እምነት፥
ለአንዱም በአንዱ መንፈስ የመፈወስ ስጦታ፥
ለአንዱም ተአምራትን ማድረግ፥ 
ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥
ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥
ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥
ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤   
ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል።”

ከእነዚህ መሐል ደግሞ ልሳን አንዱ ነው:: ሰው በልሳን ወደእግዝአብሔር ሲፀልይ ምን እንደሚፀልይ አያውቀውም መንፈስ ቅዱስ ግን ይረዳዋል (ሮሜ 8 26)  ቃላቶችን ይሰጠዋል:: 

No comments:

Post a Comment