Saturday, May 26, 2012

Trinity in Amharic Part 2


ኢየሱስ አምላክ ነውን? ኢየሱስ እኔ አምላክ ነኝ ብሎ ነበርን?




ጥያቄ፤ ኢየሱስ አምላክ ነውን? ኢየሱስ እኔ አምላክ ነኝ ብሎ ነበርን?

መልስ፤ በእርግጥ ኢየሱስእኔ አምላክ ነኝብሎ በቀጥታ ስለመናገሩ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈ የለም። ይሁን እንጂ ኢየሱስ አምላክ ስለመሆኑ ግን አላወጀም ማለት አይደለም። ለምሳሌ ያህል የኢየሱስ ቃል በዮሐንስ ፲፥፴ እነደተጻፈው እነዲህ ይላል፣እኔና አብ አንድ ነን።ላዩን ሲታይ ይህ አምላክ አንነደሆነ ማወጁን ላያመለክት ይችላል። ቢሆንም፣ ለኢየሱስ ንግግር የአይሁድ አቀባበል ማየት በቂ ነው፤አይሁድም፣የምንወግርህ፣ ተራ ሰው ሆነህ ሳለህ፣ ራስህን አምላክ በማድረግ፣ የስድብ ቃል ስለተናገርህ ነው እንጂ ከእነዚህ ስለ የትኛውም አይደለምብለው መለሱለት” (ዮሐንስ ፲፥፴፫) አይሁድ የኢየሱስን ንግግር የአምላክነቱን አዋጅ እንደሆነ ገባቸው። በእነዚህ ጥቅሶች ኢየሱስ አይሁድንእኔ አምላክ አይደሁምብሎ አልገሠጻቸውም። ይህ የሚያመለክተው ኢየሱስ አምላክነቱን በእርግጥ ማመኑን ነው፤እኔና አብ አንድ ነን” (ዮሐንስ ፲፥፴) ሌላው ምሳሌ ደግሞ በዮሐንስ ፰፥፶፰ የተጻፈውን ነው፤ኢየሱስም፣እውነት እላችኋለሁ፤ አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ፣ እኔ ነኝአላቸው።ለዚህም መልስ አይሁድ ኢየሱስን ሊወግሩት ድንጋይ አነሱ (ዮሐንስ ፰፥፶፱) አምላክ ነኝ ብሎ መናገሩ እነደስድብ ባይቆጥሩት ኖሮ፣ አይሁድ ኢየሱስን በድንጋይ ሊወግሩት ባልተነሱ ነበር።

ዮሐንስ ፩፥፩ እነደሚለው፣ “…ቃልም እግዚአብሔር ነበር።ዮሐንስ ፩፥፲፬ እንዲህ ይላል፣ቃልም ሥጋ ሆን።ይህ በግልጽ እነደሚያሳየው ኢየሱስ ሥጋ የለበሰ አምላክ ነው። የሐዋሪያት ሥራ ፳፥፳፰ እነደሚነግረን፣ “…በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።ማነው ቤተ ክርስቲያንን በደሙ የዋጃት? ኢየሱስ ክርሰቶስ። የሐዋሪያት ሥራ ፳፥፳፰ ላይ እነደተጻፈው፣ ቤተ ክርስቲያንን በገዛ ደሙ የዋጃት አምላክ ነው። ስለዚህም፣ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው!

የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ቶማስ ኢየስሱን አስመልክቶ እንዲህ ሲል ተናገረ፣ጌታዬ፤ አምላኬም!” (ዮሐንስ ፳፥፳፰) ለዚህ ንግግሩም ኢየሱስ ቶማስን ሲያርመው አይታይም። ቲቶ ፪፥፲፫ የጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት በርትተን እንድንጠብቅ ይመክረናል (በተጨማሪም ፪ኛ ጴጥሮስ ፩፥፩ ማየት ይቻላል) በዕብራውያን ፩፥፰፣ አብ ስለ ኢየሱስ እንዲህ ይላል፤ስለ ልጁ ግን እንዲህ ይላል፤አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤ ጽድቅም የመንግሥትህ በትር ይሆናል።

በራእይ እንደተጻፈው፣ መልአክ ሐዋሪያው ዮሐንስን እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልክ አዘዘው (ራእይ ፲፱፥፲) በወንጌል እነደሚነበበው፣ ኢየሱስ ብዙ ጊዜ አምልኮ ይቀበል ነበር (ማቴዎስ ፪፥፲፩፤ ፲፬፥፴፫፤ ፳፰፥፱፣ ፲፯፤ ሉቃስ ፳፬፥፶፪፤ ፲፱፥፲) ሰዎች ሲያመልኩትም አልገሠጻቸውም። ኢየሱስ አምላክ ባይሆን ኖሮ ግን፣ እኔን አታምልኩ ባለ ነበር፤ ልክ መልአኩ ሐዋሪያው ዮሐንስን እነዳዘዘው። ስለ ኢየሱስ አምላክነት የሚመሰክሩ ጥቅሶችና የወንጌል ገጸ ንባቦች ብዙ ናቸው።

ከሁሉም የላቀ ምክኒያት ግን አለን። ይኸውም ኢየሱስ አምላክ ባይሆን ኖሮ፣ በሞቱ የምድርን ሐጢአት ቅጣት መቀበል ባልቻለ ነበር (፩ኛ ዮሐንስ ፪፥፪) አምላክ ብቻ ነው ለዚህ መጨረሻ ለሌለው ቅጣት ለመቀበል (፪ኛ ቆሮንቶስ ፭፥ ፳፩) ለመሞትና ከሙታን በመነሳትም ሞትንና ሐጢአትን ማቸነፍ የሚችለው።

ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?




ጥያቄ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?

መልስ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው? “እግዚአብሔር አለእነደሚለው ጥያቄ ሳይሆን፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መኖር በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው የሚጠራጠሩት። ኢየሱስ ክርስቶስ ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት በእስራኤል ምድር የተመላለሰ ሰው እንደሆነ በአብዛኛው ተቀባይነት አለው። ክርክሩ የሚጀመረው የኢየሱስ ክርስቶስን እውነተኛ ማንነትን በተመለከተ ነው። ሁሉም አበይት ሃይማኖቶች ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢይ፣ ወይም ጥሩ መምህር፣ ወይም አምላካዊ ሰው እንደነበር ያስተምራሉ።

. . ለዊስባዶ ክርስትናበሚል መጽሐፉ የሚከተለውን እናገኛለን፤ብዙ ሰዎች ስለእርሱ (ኢየሱስ ክርስቶስ) የሚሉትን ሞኝ የሆነ አባባል ለማስቀረት እየጣርኩ ነው፤ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ታላቁ የግብረ ገብ መምህሬ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ፤ ነገር ግን አምላክነቱን አልቀበለውም።ይህ ነው እንግዲህ ማለት የሌለብን። ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውንና የሠራውን ሁሉ በአንድ ተራና የግብረ ገብ መምህር በሆነ ሰው በቻ ሊከናወን አይችልም። እንዲህ አይነቱ ሰው ወይም እብድ መሆን አለበት፣ አልያም የገሃነም ሰይጣን መሆን አለበት። መምረጥ አለብህ። ይህ ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ነበር፣ ነውም፣ ወይንም ደግሞ እብድ ወይም ከዛም የባሰ ነበር ማለት ነው። ሞኝ ነው ብለህ ልታልፈው፣ ልትተፋበትና ጋኔን ነው በለህ ልትገድለው ትችላለህ፤ ወይንም ደገሞ ጌታየና አምላኬ ብለህ እግሩ ሥር ልትደፋለት ትችላለህ። ነገር ግን ዝቅተኛ መንፈስ በሚያሳይ መልኩ ታላቅ ሰብአዊ መምህር እያላን ግን አንመጻደቅ። ይህ ከምርጫዎቹ ውስጥ የለም። የዚህ አይነት ምርጫ እንዲኖረንም ዕቅዱ አልነበረም።

ስለዚህ፣ ክርስቶስ ማን ነኝ ብሎ አወጀ? መጽሐፍ ቅዱስስ ስለማንነቱ ምን ይለናል? በመጀመሪያ የኢየሱስን ቃል በዮሐንስ ፲፥፴ የተጻፈውን እንመልከት፤እኔና አብ አንድ ነን።ላዩን ብቻ ሲታይ፣ የአምላክነት አዋጅ ላይመስለን ይችላል። ነገር ግን ለዚህ ቃሉ የአይሁድን መልስ ማየት ብቻ በቂ ነው፤የምንወግርህ፣ ተራ ሰው ሆነህ ሳለህ፣ ራስህን አምላክ በማድረግ፣ የስድብ ቃል ስለተናገርህ ነው እንጂ ከእነዚህ ስለየትኛውም አይደለም” (ዮሐንስ ፲፥፴፫) አይሁድ የክርስቶስ ንግግር የአምላክነቱን አዋጅ መሆኑ ገባቸው። በሚቀጥሉት ጥቅሶች ኢየሱስ አይሁድንአምላክ አይደለሁምብሎ ሲያርማቸው አይታይም። ይህም የሚያመለክተው ኢየሱስ በአውነት የአምላክ ልጅ እንደሆነ መናገሩን ነው፤እኔና አብ አንድ ነን” (ዮሐንስ ፲፥፴) ዮሐንስ ፰፥፶፰ ደግሞ ሌላው ምሳሌ ነው፤ኢየሱስም፣እውነት እላችኋለሁ፤ አብራሃም ከመወለዱ በፊት እኔ፣ እኔ ነኝአላቸው።ለዚህ መልሱም አይሁድ በድንጋይ ሊወግሩት ሞከሩ (ዮሐንስ ፰፥፶፱) ኢየሱስ ስለማንነቱእኔ ነኝብሎ መናገሩ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ይጠራበት የነበረውን ስም መጠቀሙን ያሳየናል (ዘፀአት ፫፥፲፬) ታድያ እነርሱ እንደስድብ በቆጠሩት የአምላክነቱን አዋጅ ካልሆነ በቀር በሌላ በምን ምክንያት አይሁድ ኢየሱስን በድንጋይ ሊወግሩት ተነሳሱ?

ዮሐንስ ፩፥፩ እንደሚለው “… ቃልም እግዚአብሔር ነበር።በማሰከተልም፣ ዮሐንስ ፩፥፲፬ቃልም ሥጋ ሆነይላል። ይህ በግልጽ እንደሚያመለክተው ክርስቶስ ሥጋ የለበሰ አምላክ ነው። የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ቶማስ፣ጌታየ፤ አምላኬም!” በማለት የኢየሱስን አምላክነት ተናገረ (ዮሐንስ ፳፥፳፰) ለዚህ ንግግሩም ኢየሱስ አልገሰጸውም። የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ጳውሎስ እንዲህ በማለት ኢየሱስን ይገልጸዋል፤ “…የታላቁን የአምላካችንንና የአዳኛችን የኢየሱስ ክርስቶስ…” (ቲቶ ፪፥፲፫) የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ጴጥሮስም ተመሳሳዩን ይናገራል፤ “…በአምላካችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ…” (፪ኛ ጴጥሮስ ፩፥፩) እግዚአብሔር አብም ስለ ኢየሱስ ሙሉ ማንነት እነዲህ ሲል ይመሰክራል፤ “…አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤ ጽድቅም የመንግሥትህ በትር ይሆናል” (ዕብራውያን ፩፥፰) የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ስለ ክርስቶስ አምላክነት እንዲህ ይላሉ፤ሕፃን ተወልዶልናልና፤ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣ የዘለዓለም አባት፣ የስላም ልዑል ይባላል” (ኢሳይያስ ፱፥፮)

ስለዚህ፣ ኢየሱስ እንደ አንድ ጥሩ መምህር ብቻ መቀበል ምርጫ ውስጥ የለም ሲል . . ለዊስ ይከራከራል። አምላክ ካለሆነ ዋሽቶአል ማለት ነውና ነብይም ሆነ ጥሩ መምህር ሊሆን አይችልም። አንዳድ ዘመናውያንሊቃውንትየኢየሱስን ቃል እርሱ እንዳልተናገረው ለማስመሰል፣ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ኢየሱስ የተጠቀሰው ሁሉ፣እውነተኛው የታሪክ ኢየሱስበቃሉ አልተናገረውም ይላሉ። እኛ ማን ነንና ኢየሱስ ስላለው ወይም ስላላለው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የምንከራከረው? እንዴት ሲሆን ነው አንድሊቅየዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት የተደረገውን ከኢየሱስ ጋር አብረው ከነበሩት በላይ ሊያውቅ የሚችለው?

ስለ ኢየሱስ ማንነት ጥያቄ ለምንድነው እንደዚህ አንገብባቢ የሆነው? ኢየሱስ አምላክ ቢሆንም ባይሆንምስ ለምን ጉዳያችን እናደርገዋለን? ዋናው ምክንያት፣ ኢየሱስ አምላክ ካልሆነ፣ ሞቱ የዓለምን ኀጢአት ለማስተሰረይ አይችልም ማለት ነው (፩ኛ ዮሐንስ ፪፥፪) አምላክ ብቻ ነው እንደዚህ ያለ መጨረሻ የሌለው ቅጣት መቀበል የሚችለው (ሮሜ ፭፥፰፤ ፪ኛ ቆሮንቶስ ፭፥፳፩) ኢየሱስ አምላክ መሆን አለበት ዕዳችንን እንዲከፍልልን። ኢየሱስ ሰው መሆን ነበረበት መሞት እንዲችል። ድነት የሚገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው! የኢየሱስ አምላክነትም ነው የድነት መንገድ በኢየሱስ ብቻ እንዲሆን ያደረገው። ኢየሱስ አምላክ ስለሆነም ነው እንዲህ ብሎ ያወጀው፤መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካለሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” (ዮሐንስ ፲፬፥፮)
መጽሐፍ ቅዱስ እየሱስን የመላእክት አለቃ ሚካኤል ነው ይለዋል?

መላእክ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ማለት ነው?
ዕብ 1፡7,14”ስለመላእክትም ሲናገር፣ መላእክቱን ነፋሳት፣ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል ያደርጋል ይላል።”…”14 መላእክት ሁሉ መዳንን የሚወርሱትን ለማገልገል የሚላኩ አገልጋይ መናፍስት አይደሉምን?”
ከዚህ ቃል እንደምንረዳው መላእክት ሁሉ መንፈስ ናቸው እግዛብሔርንና መዳንን የሚወርሱትንም የሚያገለግሉ አገልጋይ ናቸው።
ስለእየሱስ ግን የእግዛብሔር ቃል ሲናገር ፊሊ 2፡6-7 “እርሱ ግን በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ፣ ከእግዛብሔር ጋር መተካከልን ሊለቀው እንደማይገባው አድርጎ አልቆጠረውም፤ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም አምሳል ተገኝቶ፣ ራሱን ባዶ አደረገ፡”  ከእዚህ ቃል እንደምንረዳው እየሱስ በባሕርዩ አምላክ እንጂ ባርያ(አገልጋይ)አይደለም ነገር ግን ሰውን በማዳን ስራው ራሱን ባዶ አደረገ፣ የባርያን መልክ ያዘ። መላእክት ግን በተፈጥሮአቸው(በባሕርያቸው)አገልጋይ(ባርያ) ናቸው። ይህ ቃል ብቻ እንኳን እየሱስ መላእክ(የመላእክት አለቃ) ሊሆን እንደማይችል ይነግረናል። ምክንያቱም ዕብ 1፡14 እንደሚነግረን መላእክት ሁሉ መዳንን የሚወርሱትን ለማገልገል የሚላኩ አገልጋይ መናፍስት ናቸው።

ይህ የዕብራውያን መልዕክት ሲቀጥል ዕብ 1፡4-5”ስለዚህ የወረሰው ስም ከመላእክት ስም እንደሚበልጥ ሁሉ፣ እርሱም ከመላእክት እጅግ የላቀ ሆኗል። እግዛብሔር፣ አንት ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤ ወይስ ደግሞ፣ እኔ አባት እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል ያለው ከመላእክት ከቶ ለማነው?”   እግዛብሔር ለአንድም መልአክ ልጅ ይሆነኛል አላለም።

ዕብ 1፡6 “ደግሞም እግዛብሔር በኩሩን ወደ ዓለም ሲያስገባ፣ የእግዛብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት(worship) ይላል።” ይህ የእግዛብሔር ትዕዛዝ ሁሉም መላእክት(ሚካኤልን እንደሚጨምር ግልፅ ነው)ለልጁ እንዲሰግዱ ያዛል። ከሌላ የእግዛብሔር ቃል እንደምናውቀው ስግደት የሚገባው ለእውነተኛ አምላክ ብቻ ነው።

ዕብ 2፡5 እና ዕብ 2፡8ን ደግሞ እንይ
ዕብ 2፡5 “ይህ የምንናገርለት መጪውን ዓለም ለመላእክት አላስገዛም፤”  ካለ በኋላ  ዕብ 2፡8 ላይ”ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት። እግዛብሔር ሁሉን ከበታቹ ሲያስገዛለት፣ ያላስገዛለት ምንም ነገር የለም…” ከዚህ የምንረዳው ለልጁ ሁሉን ነገር ሲያስገዛለት ለመለእክት ግን አላስገዛም። አሁንም ከዚህ የምንረዳው ልጁ የመላእክ ማንነት የለውምም አይደለምም።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሚካኤል የሚለው የመላእክት አለቃ ስም 6(ስድስት) ጊዜ ተጠቅሷል። አንድም ቦታ ታዲያ ከእየሱስ ጋር የሚያያይዘው ነገር የለም። እስቲ ሁሉንም አንድ በእንድ እንያቸው።

ዳን 10፡13, 10፡21, 12፡1, 1 ተሰ 4፡16, ይሁዳ 9, ራዕ 12፡7

እነዚህን አንድ ባንድ ብናይ አንድም ቦታ እየሱስ ሚካኤል እንደሆነ አይናገርም።

  1. ዳን 10፡13 “ነገር ግን የፋርስ መንግስት አለቃ ሃያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ የሆነው ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም በዚያ ከፋርስ ንጉስ ጋር ተውሁት።” 
እዚህ ጋር ሚካኤል እየሱስ እንደሆነ ይናገርልናል ብለው የሚያስቡት “ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ የሆነው ሚካኤል” የሚለውን ቃል ነው።
የተጠቀሰው ሚካኤል ከዚህ ሐሳብ በመነሳት በእርግጥ ዋነኛ አለቃ ነው። ነገርግን እሱ ብቻ አይደለም ዋነኛ አለቃ ምክንያቱም “ከዋነኞቹ አለቆች” ስለሚል ልክ እንደሱ ሌሎች ዋነኛ አለቆች አሉ ስማቸው የማይታወቅ። እንደመጠበቅያ ትምህርት ደግሞ ከእየሱስ ጋር የሚስተካከል ሌላ ፍጡር የለም። ምክንያቱም ይሆዋ እየሱስን(ሚካኤል) መጀመርያ ፈጠረ ከዛም ሚካኤል ሌሎቹን ሁሉ ፈጠረ። ስለዚህ ሚካኤል እሱ ራሱ ከፈጠራቸው ጋር አብሮ ዋነኛ አለቃ ተብሎ አይጠራም። እየሱስ ደግሞ ሌላ ቦታ ዋነኛ አለቃ ተብሎ የተጠራበት ቦታ አናገኝም። ስለዚህ ይህ ቦታ በፍፁም እየሱስ ሚካኤል እንደሆነ አይናገርም።

  1. ዳን 10፡21 “አስቀድሜ ግን በእውነት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ ከእነዚህ አለቆች ጋር ለመዋጋት ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ የለም።”
እዚህ ጋር ያለውን ከዳን12፡1 ጋር ስናስተያየው ሚካኤል የእስራኤል ጠባቂ(አለቃ) (prince) ነው። ቁጥር 13 ላይ እንደሚነግረን ከዋነኞቹም አለቆች አንዱ ነው። እየሱስ ደግሞ የጌቶች ጌታ፤ የነገስታት ንጉስ ነው የተባለው። አሁንም ሚካኤል እየሱስ እንደሆነ ትንሽም ፍንጭ አይሰጠንም።

  1. ዳን 12፡1 “…ስለሕዝብህ የሚቆመው ታላቁ ሚካኤል ይነሳል።…” ይህም ከላይ ካየነው ሃሳብ ጋር አንድ ነው። ሚካኤል ለዳንኤል ሕዝብ (በስደት ለነበረው እስራኤል) ይቆማል ወይም ጠባቂ መላዕክ ነው።


  1. 1 ተሰ 4፡16 “ጌታ ራሱ በታላቅ ትእዛዝ፤ በመላእክት አለቃ ድምፅና በእግዛብሔር የመለከት ድምፅ ከሰማይ ይወርዳልና።…” ይህን ይበልጥ ለመተንተን እንዲረዳን እንግሊዘኛውን እንይ 1 Th 4:16 16 For the Lord himself will come down from heaven, with a loud command, with the voice of the archangel and with the trumpet call of God, and the dead in Christ will rise first.” አሰተውለን ስናይ  with
የሚል ቃል እናያለን ትርጉምም ከ…ጋር ማለት ነው። እየሱስ ሁለተኛ ሲመጣ ማር8፡38 እንደሚነግረን ቅዱሳን መላእክቱ ጋር ነው። እንዲሁም ማቴ25፡31 ላይ የሰው ልጅ መላእክቱ ሁሉ ጋር ሲመጣ ይለናል። እሱ ሲመጣ ከ…ጋር ነው። እሱ ሲመጣ የመላእክት አለቃ በድምጽ እያጀበው ነው። እሱ ብቻ ሳይሆን የእግዛብሔር መለከት ድምፅም ያጅበዋል። በመላእክት አለቃ ድምፅ ሲል ራሱ እየሱስ ነው ካልን በእግዛብሔር መለከት ድምፅ ሲል ራሱ እግዛብሔር ነው ማለት እንችላለን። ምክንያቱም ከመላእክት አለቃ የሚወጣ አንድ ድምፅ አለ እንዲሁም ከእግዛብሔር በመለከት አማካኝነት የሚወጣ ሌላ ድምፅ አለ። ስለዚህ በተለያየ ድምፅ ታጅቦ ይመጣል ነው የሚለን እንጂ እሱ ራሱ ድምፅ ያሰማል አይለንም። ደግሞ ሲመጣ ስሙ ሚካኤል አይደለም ራዕ 19፡11-12 እንደሚነግረን ስሙ “ታማኝና እውነተኛ” ፤ “ከእርሱ በቀር ማንም የማያውቀው ስም” ፤ “የነገስታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ” ።

  1. ይሁዳ 9 “የመላእክት አለቃ የሆነው ሚካኤል እንኳ ስለሙሴ ስጋ ከዲያቢሎሰ ጋር በተከራከረ ጊዜ፣ ጌታ ይገስጽህ አለው እንጂ የስድብ ቃል በመናገር ሊከስው አልደፈረም።” ይህንን የመላእክት አለቃ የሆነው ሚካኤል ጌታ ይገስጽህ ሲል ፤ የጠራው ጌታ ማነው? የይሁዳን አውዱን (context) ስናነበው ቀጥር 4 ላይ “…እርሱ ብቻ ልዑል ገዣችንና ጌታችን የሆነውን እየሱስ ክርስቶስን የሚክዱ ናቸው።” ይላል። ስለዚህ አው ዱን ይዘን ስናነበው ጌታ ብሎ ይሁዳ በመልዕክቱ የጠቀሰው እየሱስን ነው ስለዚህ ጌታ ይገስጽህ ሲል እየሱስ ይገስጽህ እያለው ነው። ስለዚህ አስተውለን ስናየው በጣም በግልጽ የሚያሳየን ሚካኤልና እየሱስ የተለያዩ እንደሆኑ ነው። መጽሓፍ ሌላም ቦታ እየሱስ ጌታ ነው ይላል።

  1. ራዕ 12፡7 “…በሰማይም ጦርነት ሆነ፤ ሚካኤልና መላዕክቱ ከዘንዶው ጋር ተዋጉ …” ሚካኤል በስሩ መላእክት ስላሉ እንዳለቃነቱ እየሱስነው ይላሉ። በምሳሌ ለማስረዳት መቶአለቃ በስሩ ወታደሮች አሉ ግን ጄኔራሉን ሊሆን አይችልም ምክንየቱም ጄኔራሉ በስሩ ከተራወታደር ጀምሮ ብዙ መቶአለቆች ስላሉ። ጄኔራሉም የጦር ሐይሎች ጠቅላይ አዛዥ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም የጦር ሐይሎች ጠቅላይ አዛዥ በስሩ ብዙ ጄኔራሎች ስላሉ። የመላእክት አለቃ የሆነው ሚካኤል በስሩ መላእክት ስላሉ እየሱስ ነው ማለት አንችልም ምክንያቱም እንደሱ ሌሎችም ዋነኛ አለቆች ስላሉ። ባይፃፍልንም ዋነኛ አለቃ ከሆኑ በስራቸው መላእክት እንዳሉ ግልጽ ነው።

ለማጠቃለል ሚካኤል ተብሎ የተጠቀሰውን ቦታ ሁሉ አየነው ሥድስቱም ቦታ ግን ጥቂትም ቢሆን ከእየሱስ ጋር የሚያያይዘው ነገር የለም። ለነገሩ በ1917 የተፃፈው STUDIES IN THE SCRIPTURES, VOLUME 7, THE FINISHED MYSTRY በሚለው ክፍል ገፅ 188 ላይ ሚካኤል የሮም ጳጳስ ነው ብለው ነበር። በ1879 ዋች ታወር ፅሁፍ ላይ ቻርለስ ቲ ራስል ዕብ 1፡6 የእግዛብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት ስለሚል ይህም መላእክት ሁሉ ስለሚል ሚካኤልን ይጨምራል ስለዚህ ሚካኤል ደግሞ የእግዛብሔር ልጅ አይደለም ብሎ ነበር። 

***የሚመካ በጌታ ይመካ***

2 CORINTHIANS 10:17
PHILIPPIANS 3:3
“But he that boasts, let him boast in Jehovah.”—New World Translation
“For we are those…who are rendering sacred service…and have our boasting in Christ Jesus.…” —New World Translation

2ቆሮ 10፡17 ላይ በመጠበቂያ ግንብ በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም የሚመካ በይሆዋ ይመካ ብለዋል። ነገር ግን በፊሊ 3፡3 ጳውሎስ የምመካው በእየሱስ ነው የሚለው ቦታ ላይ በትክክል ተርጉመውታል። ታዲያ ይሆዋ እና እየሱስ አንድ ይሆኑ?
መንፈስ ቅዱስ


እየሱስ ከመሰቀሉ በፊት ከደቀመዛሙርቱ ጋር ሲነጋገር እንዲህ ብሎአቸው ነበር….
ዮሐ 14፡16 ” እኔ አብን እለምናለሁ፤ እርሱም ከእናንተ ጋር ለዘላለም የሚኖር ሌላ( በእንግሊዘኛ another (በግሪክ allos) አጽናኝ ይሰጣችኋል፤”

አንድ ሰው እየረዳህ ከነበረና ያ የሚረዳህ መሄድ ስላለበት ሌላ የሚረዳህ ካንተ ጋር እንዲሆን እልክልሃለሁ ቢልህና እነደሱ አይነት የሚረዳህ ባይመጣ ምን ይሰማሃል? እየሱስ ሌላ ረዳት እልካለሁ ሲል እዚህ ቦታ ላይ የሚለው ልክ እንደሱ የሆነ ማለቱ ነው። ሌላ የሚለው የግሪክ ቃል allos ማለት ልክ እነእንደራስ ማለት ነው( another of the same kind) ነገር ግን ማለት የተፈለገው ከሱ የተለየ ሌላ( another of a different kind) ቢሆን ኖሮ የግሪኩ ቃል ይሆን የነበረው፡(heteros) ነበር።

ለምሳሌ ይህን ጥቅስ እንይ ገላ1፡6 ”በክርስቶስ ጸጋ የጠራችሁን እርሱን ትታችሁ፣ ወደተለየ(በግሪክ heteros) ( በእንግሊዘኛ another) ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ መዞራችሁ ደንቆኛል፤ እንደእውነቱ ከሆነ ሌላ (በግሪክ allos) (በእንግሊዘኛ another) ንጌል የለም። የሚያደነጋግሯችሁና የክርስቶስን ወንጌል ለማጣመም  
ጥረት የሚያደርጉ አንዳንድ ሰዎች አሉ።

ከቃሉ እንደምንረዳው የገላትያ ሰዎች ከትክክለኛው ወንጌል ጋር የማይመሳሰል ወደሌላ ሃሰተኛ ወንጌል ሄደዋል። ስለዚህ ሐዋርያው ጳውሎስ የተጠቀመበት ቃል የተለየ ወይም ሌላ ለሚለው ሃሳብ heteros ነው እንጂ allos አይደለም። እንግዲህ ዮሐ 14፡16 ላይ ያለው ሌላ allos ተመሳሳይ ማንነት (ሰብዕና) ያለው ሌላ ማለት ነው። እንደሱ አይነት ሰብዕና የሌለው ቢሆን ኖሮ ሌላ ለሚለው የመጠቀመበት የግሪክ ቃል heteros  ይሆን ነበር የተጠቀመው።

ሰለዚህ ስለሚመጣው ረዳት ሌላ ቦታ ላይ ሲናገር ዮሐ 16፡13 “ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል። እርሱ ከራሱ አይናገርም…” ይላል። ከራሱ ስለማይናገር ሰብዕና የለውም ማለት ይቻላል? ዮሐ 12፡49 ላይ እየሱስ ስለራሱ ሲናገር “እኔ ከራሴ አልተናገርኩም…” ይላል ታዲያ እየሱስ ሰብዕና የለውም ማለት እንችላለን? ዮሐ 16፡13 ላይ ደግሞ “የሚሰማውን ብቻ ይናገራል” ሲልስ ይህ የእውነት መንፈስ ከሌላ ሰብዕና ካለው ነገር እሱ የተለየ ሆኖ ይሰማል ማለት አይደለም? ሰምቶ የሚናገር ደግሞ በራሱ ሰብዕና ያለው ነው። ይህ የእውነት መንፈስ የእግዛብሔር ሃይል(active force) ብቻ ቢሆን ኖሮ የአብ የሆነው ሁሉ በእሱም ውስጥ ስለሚያልፍና እሱም የዛ ቅጥያ ስለሆን ከእየሱስ የሚወስደው ነገር አይኖርም ነበር ግን እዛ ቦታ እንዲህ ይላል ዮሐ 16፡14 ”የእኔ ከሆነው ወስዶ እንድታውቁ በማድረግ ያከብረኛል። የአብ የሆነው ሁሉ የእኔ ነው፤ እንግዲህ፣ የእኔ ከሆነው ወስዶ እንድታውቁ ያደርጋል ያልኋችሁ ለዚሁ ነው።”

ሮሜ 8፡22-34” እስካሁን ድረስ ፍጥረት ሁሉ በምጥ ጊዜ እንዳለው ሥቃይ በመቃተት ላይ እንደሚገኝ እናውቃለን። እርሱ ብቻ ሳይሆን፣ የመጀመርያውን የመንፈስ ፍሬ ያገኘን እኛ ራሳችን የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነታችንን በናፍቆት እየተጠባበቅን በውስጣችን እንቃትታለን። በዚህ ተስፋ ድነናል፤… እንዲሁም ደግሞ( In like manner) መንፈስ በድካማችን ያግዘናል፤ እንዴት መፀለይ እንደሚገባን አናውቅም፤ መንፈስ ግን በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ለእኛ ይማልድልናል።…ታዲያ የሚፈርድ ማነው? የሞተው፣ እንዲሁም ከሞት የተነሳው፣ በእግዛብሔር ቀኝ የተቀመጠው ክርስቶስ እየሱስ፣ ስለእኛ ይማልዳል።”                

እዚህ ቦታ ላይ የሚቃትተው ወይም የሚማልደው ማነው?
ቁጥር 22 ላይ “ፍጥረት ሁሉ”
                           ቁጥር 23 ላይ “እኛ”
                           ቁጥር 34 ላይ “እየሱስ”
                           ቁጥር 26 ላይ “መንፈስ ቅዱስ”
መንፈስ ቁዱስ ኀይል ብቻ ከሆነ እንዴት ነው እነደፍጥረት፣ እንደእኛ፣ ወደ እግዛብሔር የሚቃትተው? ይህ ከአብ የተለየ ሰብዕና እንዳለው አያሳየንም?

1 ቆሮ 12፡11 “ እነዚህ ሁሉ የዚያው የአንዱ መንፈስ ስጦታዎች ሲሆኑ፣ ለእያንዳንዱ ሰው እርሱ ራሱ እንደ ፈቀደ ይሰጣዋል።” 
መንፈስ ቅዱስ እንደወደደ ስጦታዎችን ለመስጠት ፈቃድ (will) ካለው፡ ይህ የሚያሳየው የራሱ ሰብዕና እንዳለው ነው።

ራዕ 22፡17 “መንፈስና ሙሽራይቱ፣ “ና” ይላሉ፤ የሚሰማም፣ “ና” ይበል፤…”
ሐዋርያው ዮሐንስ በራዕይ አይቶ መንፈስና ሙሽራይቱ ና ይላሉ ይለናል። እዚህ ጋር ዮሐንስ ያየው ነገር አለ ያየው አብን አይደለም ያየው መንፈስ ቅዱስን ነው። ለማየት ደግሞ የሚታይ ነገር ማየት አለበት። ባጠቃላይ የዮሐንስን ራዕይ ስናጠና ሐዋርያው ዮሐንስ በራዕይ(vision) አብን አይቷል እየሱስን አይቷል መንፈስ ቅዱስን አይቷል ።

ሐዋ 5፡1-11 “ ሐናንያ የተባለ ሰው፣ ከሚስቱ ከሰጲራ ጋር መሬት ሸጠ፤ ሚስቱም በሚገባ እያወቀች ከሽያጩ የተወሰነ ገንዘብ በማስቀረት የተረፈውን አምጥቶ በሐዋርያት እግር ስር አስቀመጠ። ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለ፤ ሐናንያ ሆይ፤ መንፈስ ቅዱስ ትዋሽና ከመሬቱ ሽያጭ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን ልብህን ለምን ሞላው? ሳትሸጠው በፊት የአንተው አልነበረምን? ከሸጥከውስ በኋላ ቢሆን ገንዘቡ በእጅህ አልነበረምን? ለመሆኑ ይህን ነገር እንዴት በልብህ አሰብህ? የዋሸኸው እኮ እግዛብሔርን እንጂ ሰውን አይደለም።…”  ልብ ብለን ስናይ ጴጥሮስ መጀመርያ ዋሸህ ያለው መንፈስ ቅዱስን ነበር ከዛም እግዛብሔርን ዋሸህ አለው። ይህ መንፍስ ቅዱስ ራሱ እግዛብሔር እንደሆነና መንፍስ ቅዱስ ማንነት እንዳለው ሰውም ሊዋሸው እንደሚችል ነው። አንዳንዶች እንደሚሉት መንፈስ ቅዱስ ኀይል ብቻ ቢሆን ኖሮ እንዴት ሰው ኀይልን ይዋሻል?

ሐዋ 8፡29 “መንፈስም ፊሊጶስን፣ “ሂድ ወደዚህ ሠረገላ ቅረብ” አለው።” መንፈስ በንግግር ያዛል። ይናገራል””

ሐዋ 13፡2 “እነዚህም ጌታን እያመለኩና እየጾሙ ሳሉ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ በርናባስንና ሳውልን እኔ ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ መንፈስ ቅዱስ እዚህ ቦታ ላይ እየተናገረ ነው የምናየው ራሱንም “እኔ” ብሎ እየጠራ ነው። አንድ ኀይል ራሱን እኔ ብሎ አይጠራም።

ራሱ እግዛብሔር ስለሆንም የዘላለም መንፈስ ተብሎአል። ዕብ 9፡14”በዘላለም መንፈስ አማካይነት…” 


እግዛብሔርን መንፈስ ቅዱስ እንዴት ለተመሳሳይ ነገር እየተለዋወጡ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተጠቀሱ እንይ

ዘፅ 17፡2 እና ዕብ 3፡7-9

ዘፅ 17፡2 “ስለዚህ፣ የምንጠጣው ውሃ ስጠን በማለት ሙሴን ተጣሉት። ሙሴን፣ እኔን ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዛብሔርንስ ለምን ትፈታተኑታላችሁ? አለ?” ቃሉ እንደሚነግረን ሰዎቹ እግዛብሔርን እየተፈታተኑት ነው። ይህን ቃል በዕብራውያን ላይ 3፡7-9 ስናየው ሰዎቹ የተፈታተኑት መንፈስ ቅዱስን ነው። “ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚል፣ ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣ በምድረ በዳ በፈተና ቀን በዐመፅ እንዳደረጋችሁት፣ ልባችሁን አታደንድኑ። አባቶቻችሁ በዚያ ተፈታተኑኝ፤ መረመሩኝ፤ ያደረግሁትን ሁሉ ለአርባ አመት አዩ።” በግልፅ እንደምናየው እዚህ ቦታ ላይ ተናጋሪው መንፈስ ቅዱስ ነው። በምድረ በዳ ተፈታተናችሁኝ እያለ ነው። 

ኤርሚያስና 31፡33 እና  ዕብራውያን 10፡15

ኤር 31፡33 “ነገር ግን ከዚያ ጊዜ በኋላ፣ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል እግዛብሔር፤ ሕጌን በልቦናቸው አኖራለሁ፣፤ በልባቸውም እጽፍዋለሁ። እኔ አምላክ እሆናቸዋለሁ። እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”

ያ ተስፋ የተገባው አዲሱ ኪዳን እውን ሆኗል። ይህንንም ኪዳን ተስፋ የገባው እግዛብሔር(ያህዌ) ነው። ዕብ 10፡15 ደግሞ እናንብብ…
ዕብ 10፡15 “መንፈስ ቅዱስም ስለዚህ ነገር ይመሰክርልናል፡ በመጀመርያ እንዲህ ይላል፤ ከዚያም በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው፤ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልባቸው አኖራለሁ፤ በአእምሮአቸውም እጽፈዋለሁ።”

ኢሳያስ 6፡8-10 እና ሐዋ 28፡25-27

ኢሳያስ 6፡8-10
የጌታንም ድምፅ። ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ። እኔም። እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ አልሁ።
እርሱም፦ ሂድ፥ ይህን ሕዝብ። መስማትን ትሰማላችሁ አታስተውሉምም ማየትንም ታያላችሁ አትመለከቱምም በላቸው።
በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳይፈወሱ፥ የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፥ ጆሮአቸውንም አደንቍር፥ ዓይናቸውንም ጨፍን አለኝ።

ይህ በሐዋርያው ጳውሎስ በአዲስ ኪዳን ሲነገር ተናጋሪው መንፈስ ቅዱስ ነው። ሐዋ 28፡25-27”… መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ በኢሳያስ አማካኝነት ለአባቶቻችሁ በትክክል እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፤ ወደዚህ ሕዝብ ሂድ፤ እንዲህም በላቸው፤ መስማትን ትሰማላችሁ፤ ነግር ግን አታስተውሉም፤ ማየትን ታያላችሁ፤ ነግር ግን አትመለከቱም። የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኗልና፤ ጆሮአቸውም ተደፍኖአል፤…”

በብሉይ ኪዳን የተናገረው እግዛብሔር ነው በአዲስ ኪዳን ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ተብሎአል። ይህ የሚያሳየን እግዛብሔርና መንፍስ ቅዱስ አንድ እንደሆኑ ነው። መንፍስ ቅዱስ ደግሞ ራሱ እንደሚናገር ነው።

መንፍስ ቅዱስ ዘላለማዊ ነው?
ዕብ 9፡14 “በዘላለም መንፈስ አማካኝነት ራሱን ነውር አልባ መሥዋዕት አድርጎ…”

መንፈስ ቅዱስ ሁሉን ያውቃል?
1 ቆሮ 2፡10-11” እግዛብሔር ግን ይህን በመንፈሱ አማካኝነት ለእኛ ገልጦልናል። መንፈስ የእግዛብሔርን ጥልቅ ነገር እንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራል።በውስጡ ካለው ከራሱ መንፈስ በስተቀር ከሰው መካከል የአንድን ሰው ሓሳብ የሚያውቅ ማን አለ? እንደዚሁም ከእግዛብሔር መንፈስ በስተቀር፣ የእግዛብሔርን ሐሳብ የሚያውቅ ማንም የለም።”              

       
መንፈስ ቅዱስ ይናገራል?
ሐዋ 13፡2 “እነዚህም ጌታን እያመለኩና እየጾሙ ሳሉ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ በርናባስንና ሳውልን እኔ ለጠራኋቸው ሥራ ለዩሉኝ አለ።”
ዕብ 3፡7 ““ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚል፣ ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣ በምድረ በዳ በፈተና ቀን በዐመፅ እንዳደረጋችሁት፣ ልባችሁን አታደንድኑ።”
1ጢሞ 4፡1 “ በ`ኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች እምነትን ክደው አታላይ መናፍስትንና የአጋንንትን ትምህርት እንደሚከተሉ መንፈስ በግልጥ ይናገራል።”  

መንፈስ ቅዱስ ይከልክላል?
ሐዋ 16፡6 “ጳውሎስና ባልደረቦቹ ቃሉን በእስያ እንዳይሰብኩ መንፈስ ቅዱስ ስለካለከላቸው…”

መንፈስ ቅዱስ ያስተምረናል ያሳስበናል?
ዮሐ 14፡26 “አብ በስሜ የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ግን ሁሉን ነገር ያስተምራችሁአል፤ እኔ የነገርኋችሁንም ሁሉ ያሳስባችኋል።”   

መንፈስ ቅዱስ በራሱ ማንነት አለው?
ዮሐ 14፡16-17 ”እኔ አብን እለምናለሁ፤ እርሱም ከእናንተ ጋር ለዘላለም የሚኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም የእውነት መንፈስ ነው፤ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም። እናንተ ግን አብሮአችሁ ስለሚኖር በውስጣችሁ ስለሚሆን ታውቁታላችሁ።”

መንፈስ ቅዱስ ይሰደባል?
ዕብ  10፡29 “ …የጸጋንም መንፈስ ያክፋፋ…”

መንፈስ ቅዱስ ስለክርስቶስ ይመሰክራል?
ዮሐ 15፡26 “እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ፣ ከእብ የሚወጣው አጽናኙ የእውነት መንፍስ በመጣ ጊዜ፤ እርሱ ስለኔ ይመሰክራል።”

መንፈስ ቅዱስ ስሜት አለው፤ ያዝናል?
ኤፌ 4፡30 “ለቤዛ ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዛብሔር መንፈስ አታሳዝኑ።”
ኢሳ 63፡10 “ እነርሱ ግን አመጹ፤ ቅዱሱ መንፈሱንም አሳዘኑ፤ ስለዚህ ተመልሶ ጠላት ሆነባቸው፤ እርሱ ራሱ ተዋጋቸው።”
ሚኪያስ 2፡7 “…የእግዝአብሔር መንፈስ የማይታገስ ነውን? ...”

መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ አለው?
1 ቆሮ 12፡11 “እነዚህ ሁሉ የዚያው የአንዱ መንፈስ ስጦታዎች ሲሆኑ፤ ለእያንዳንዱ ሰው እርሱ ራሱ እንደፈቀደ ይሰጠዋል።”

መንፈስ ቅዱስ ፍቅር አለው?
ሮሜ 15፡30 “…የተጋድሎዬ አጋር እንድትሆኑ በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስና በመንፈስ ፍቅር እለምናችኋለሁ።”

መንፈስ ቅዱስ ሐሳብ አለው?
ሮሜ 8፡27 “ልባችንንም የሚመረምረው እርሱ (እግዝአብሔር) የመንፈስን ሐሳብ ያውቃል፤ ምክንያቱም መንፈስ እንደእግዝአብሔር ፈቃድ ለቅዱሳን ይማልዳልና።” 

መንፈስ ቅዱስ ነገሮች መልካም እንደሆኑ ያስባል?
ሓዋ 15፡28 “ ከእነዚህ አስፈላጊ ነገሮች በስተቀር ሌላ ተጨማሪ ሸክም እንዳንጭንባችሁ፣ ለመንፈስ ቅዱስም ለእኛም መልካም መስሎ ታይቶናል።” 
  
ለማጠቃለል የመንፈስ ቅዱስ አምላክነትና ማንነት (personality)

ማንነቱ (ሰብዕናው) 1) በስራው 2) በባህርዩ 3)በስሜቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሷል።

አምላክነቱ ደግሞ…..
1. በመለዮው  
1.1) ሁሉን በማወቁ ፦1 ቆሮ 2፡10-11” እግዛብሔር ግን ይህን በመንፈሱ አማካኝነት ለእኛ ገልጦልናል። መንፈስ የእግዛብሔርን ጥልቅ ነገር እንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራል።በውስጡ ካለው ከራሱ መንፈስ በስተቀር ከሰው መካከል የአንድን ሰው ሓሳብ የሚያውቅ ማን አለ? እንደዚሁም ከእግዛብሔር መንፈስ በስተቀር፣ የእግዛብሔርን ሐሳብ የሚያውቅ ማንም የለም።”              
     1.2) በአንዴ በሁሉም ቦታ በመገኘቱ ፦ መዝ 139፡7-10 “ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ፣ ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ፣ ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ አለህ። መኝታዬንም በሲዖል ባደርግ በዚያ ትገኛለህ። በንጋት ክንፍ ተነሥቼ ብበር እስከ ባሕሩ ዳርቻ መጨረሻ ብሄድ በዚያም ቢሆን እጅህ ትመራኛለች። ቀኝ እጅህም አጥብቃ ትይዘኛለች።”
     1.3) የዘላለም መሆኑ ፦ ዕብ 9፡14” “በዘላለም መንፈስ አማካኝነት ራሱን ነውር አልባ መሥዋዕት አድርጎ…”

2. በሥራው
     2.1) በፍጥረት ጊዜ ተሳትፎው ፦ ዘፍ 1:2 “ምድርም ቅርጽ የለሽና ባዶ ነበረች። የምድርንም ጥልቅ ስፍራ ሁሉ ጨለማ ውጦት ነበር። የእግዝአብሔርም (ኤሎሂም) መንፈስ በውሆች ላይ ይረብብ ነበር።
እዮ 33 “የእግዝአብሔር መንፈስ ፈጥሮኛል፤ሁሉን የሚችለው አምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጥቶኛል።”s_è¾L
     2.2) በታምራት ተሳትፎው ፦ ማቴ 12፡28 “ነገር ግን እኔ አጋንንትን የማስወጣው በእግዛብሔር መንፈስ ከሆነ፣…”  
  ሮሜ 15፡19 “ይህም የሆነው በመንፈስ ቅዱስ ኀይል፣ በምልክቶችና በታምራት ነበር።…” 
2.3) ሰውን በመቤዤት ተሳትፎው ፦ ዕብ 9፡14 “በዘላለም መንፈስ አማካኝነት ራሱን ነውር አልባ መስዋዕት አድርጎ ለእግዛብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም ሕያው…”
2.4) በሰው ዳግም ልደት ተሳትፎው ፦ ዮሐ 3፡5 “…ማንም ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዛብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም..”
    ቲቶ 3፡4-6 “…ያዳነንም ዳግም ልደት በሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታደስ ነው” 

1.መንፈስ ቅዱስ የእግዛብሔር ሐይል በሰውኛ የተገለጠበት ነው እንጂ ሰብዕና ያለው አይደለም።በመጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ በተደጋጋሚ የምናየው የአጻጻፍ ዘይቤ ነው። ለምሳሌ ጥበብ ልጆች እነዳሏት ተጽፎአል። ሉቃ 7፡35 “እንግዲህ የጥበብ ትክክለኛነት በልጆቿ ሁሉ ዘንድ ተረጋገጠ”። እንዲሁም ሐጢአትና ሞትም እንደንጉስ ተጠርተዋል። ሮሜ 5፡14,21 “…ኀጢአት ባልሠሩት ላይ ሞት ነገሠ።…21 ይህም የሆነው ኀጢአት በሞት እንደነገሠ ሁሉ…” (Reasoning from the Scriptures, Spirit, p380, Jehovah's Witness publication)

      መልስ፡ 1) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነገሮችን በሰውኛ የመግለፅ አፃፃፍ የተለመደ ነው። ከብዙ በጥቂቱ ለምሳሌ ተራሮች ሲያጨበጭቡ ከዋክብት ሲዘምሩ የምናየው አለ። ነገር ግን ባለን ልምምድና ሰውኛ ዕውቀት እነዚህ ሰብዕና(personality) ያላቸው አይደሉም። መንፈስ ቅዱስ ግን አይደለም። ተራራ ሰብዕና እንዴሌለው በልምዳችን እንደምናውቀወ ሁሉ መንፈስ ቅዱስን በልምዳችን ሰብዕና የለውም ማለት አንችልም።
             2) በሰውኛ የተጠቀሱት ግን በልምዳችን የምናውቃቸው ነገሮች እንደ ተራራ ከዋክብት ጥበብ ወዘተ በዚያው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰብዕና እንዴሌላቸው ነገሮች (it) ተብለው ተጠቅሰው እናገኛቸዋለን። አንድም ቦታ ግን መንፈስ ቅዱስ በዚህ መንገድ ተጠቅሶ አናገኘውም።
 3) መንፈስ ቅዱስ በተጠቀሰበት ቦታ ሁሉ እሱ (HE) (ተባዕእ masculine) ተብሎ ነው የተጠቀሰው። ተራራና ከዋክብት ግን በዚህ መንገድ አልተጠሩም።
 4) ባብዛኛው ቦታ ላይ ከዋክብትና ተራሮች ወዘተ በሰውኛ ዘይቤ ሳይሆን በነገር(things) ነው የተጠሩት። በሰውኛ የተጠሩበት ጊዜ እጅግ በጣም ውስን ወይም አንዴ ብቻ ነው።
 5) መንፈስ ቅዱስ ግን ሁሌም በሰውኛ ነው የተጠራው።
 6) መንፈስ ቅዱስ ሰብዕና የለውም የሚሉ ትክክል ከሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ሁሌም በሰውኛ ስለሚጠራው ሰብዕና ያለውንና የሌለውን ነገር የመለያ መንገድ የለንም ማለት ነው።
 7) መንፈስ ቅዱስ ሰብዕና የለውም ለሚሉ እስኪ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የት ቦታ ነው መንፈስ ቅዱስ እንደ ነገር(thing) የተጠራው?

 8) በሰውኛ ስለተጠቀሱ ነገሮችን ስናይ ጥበብ አንድ ቦታ ብቻ ነው በሰውኛ የተጠቀሰችው፤ ኀጥያት 5 ጊዜ፤ ሞት 6 ጊዜ፤ መንፈስ ቅዱስ ግን በሰውኛ የተጠቀሰው ከመቶ ጊዜ በላይ ሊሆን ይችላል።

2.በሥላሴ የማያምኑ በሉቃ 1፡35 ላይ መንፈስ ቅዱስ የእግዛብሔር ሐይል ተብሎ ተጠርቷል ይላሉ።

      መልስ፡ 1) መጀመርያ እስቲ ጥቅሱን እናንብበው ሉቃ 1፡35 “…መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑሉ ኀይል ይጸልልሻል፤…” ጥቅሱ መንፈስ ቅዱስ የእግዛብሔር ሐይል ነው አይልም። የምናየው ሁሉት የተያያዙ ዐረፍተ ነገሮችን ነው። በሥላሴ የማያምኑ ለማያያዝ የፈለጉት መንፈስ ቅዱስና ሐይል የሚለውን ነው። እስቲ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሌላ ይኽን የሚመስል እንዲረዳን እንይ ። ሮሜ 1፡16 “ በወንጌል አላፍርም፤ ምክንያቱም ለሚያምን ሁሉ ለድነት የሚሆን የእግዛብሔር ሐይል ነው።” እዚህ ላይ እንደምናየው፡ ወንጌልና የእግዛብሔር ሐይል የተለያዩ ነገሮች ናቸው። የእግዛብሔር ሐይል ያረገው ቃሉን ለሚያምን ስለሚለውጥ ነው እንጂ በራሱ የእግዛብሔር ሐይል አይደለም። ስለዚህ የተያያዘ ዐረፍተ ነገር በሚኖርበት ጊዜ ከዐውዱ ወይንም ከመፅሕፍ ቅዱስ አጠቃላይ ሀሳብ ጋር ካላያያዝን ስህተት ላይ ልንወድቅ እንችላለን። ሌላም ምሳሌ እንይ ማቴ 22፡29 “እየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ ቅዱሳት መጻሕፍትንና የእግዛብሔርን ሐይል ሰለማታውቁ ትስታላችሁ” በእንግሊዘኛው “Jesus replied, "You are in error because you do not know the Scriptures or the power of God.” አሁንም ቅዱሳት መጻሕፍትንና የእግዛብሔርን ሐይል አንድ ላይ እያዛመደ ነው። ይህ ማለት ቁዱሳት መጻሕፍት በራሳቸው የእግዛብሔር ሐይል እየሆኑ አይደለም።
   
2) ሐዋ 10፡38 ላይ ደግሞ መንፈስ ቅዱስና ሐይል የተለያዩ እንደሆኑ እናያለን “እግዛብሔር የናዝሬቱን እየሱስ በመንፈስ ቅዱስና በኀይል ቀባው፤…” እንግዲህ መንፈስ ቅዱሰ የእግዛብሔር ሐይል ነው ካልን እየሱስ የተቀባው በሐይልና በሐይል ነው ማለት ነው።

3) ሌላው የመከራከርያ ነጥባቸው ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በግሪኩ በሚጠቀስበት ጊዜ ፆታ የለውም። ይህም የሚያሳየው ሰብዕና እንዴሌለው ነው። መንፈስ ቅዱስ በወንድ (masculine) ተጠርቶ ቢሆን ኖሮ ምናልባት ሰብዕና አለው ማለት ይቻል ነበር። እግዛብሔር ግን ሰብዕና እንደሌለው ሊያሳየን ፈልጎ ያለ ፆታ ገልጾታል ይላሉ።  
መልስ፡ 1) ከአንድ ነገር ማንነት ጋር ፆታ ሙሉ በሙሉ የሚያያይዘው ነገር የለም። የሚያያዘው ከቋንቋው ጋር ነው።
       2) በግሪኩ አዲስ ኪዳን ህፃናት (በሉቃ 1፡41; 44; 2፡16; 18፡15) ልጆች (ማር 5፡39-41) መንፈስ ቅዱስ አንዳንድ ቦታ ያለፆታ እንደተጠቀሰው እነዚህም ቦታዎች የለፆታ ነው የተጠቀሱት።
       3) ልጃገረድ( Girl) በማቴ 9፡24;25; ማር 5፡41;42 በግሪኩ ያለፆታ ነው የተጠቀሱት።
       4) መላእክት በዕብ 1፡14 በግሪኩ ያለፆታ ነው የተጠቀሱት
       5) አጋንንት በግሪኩ ከ45 ጊዜ በላይ ያለፆታ ነው የተጠቀሱት
       6) በዘፍ 1፡2 ላይ የተጠቀሰው መንፍስ በሴት ፆታ ነው።
       7) መንፈስ (Greek: pneuma) ምንም እንኳን ፆታ ባይኖረውም በአዲስ ኪዳን ውስጥ በሙሉ ሲጠራ እሱ(በወንድ ማንነት)( A masculine pronoun ("He" Greek: ekeinos, literal "that One") ነው የተገለጸው።
       8) ለእግዛብሄር አብ መንፈስ በዮሐ 4፡24 ሲያያዝ ፆታ የለውም። ከእየሱስ ጋር መንፈስ ሲያያዝ በ1ቆሮ15፡45 እንዲሁ ፆታ የለውም። ለህፃኑ እየሱስ በማቴ 2፡8, 11, 13, 14, 19-21 መነፈስ ተያይዞ ሲጠቀስ ፆታ የለውም።
       9) ይህ ከላይ በመንፈስ ቅዱስ ሰብዕና የማያምኑ ያቀረቡት መከራከርያ የግሪክ ቋንቋ እውቀት ላላቸው ሚዛን የሚደፋ አይደለም።          
 
 4.መጽሐፍ ቅዱስ መንፈሰ ቅዱስን ነገሮችን በምንጠራበት አጠራር (it)ሐፍ ሐ 7 ጊዜ ያህል ጠርቶታል። ይህም ሰብዕና እንዴሌለው ያሳያል ይላሉ።
 በ ዮሐ 1፡32; ሮሜ 8፡16,26; 1ቆሮ 12፡11; ዕብ 10፡15,17; 1ጴጥ 1፡11
1)  እየሱስም 5 ጊዜ ያህል ነገሮችን በምንጠራበት አጠራረ (it) ተጠርቷል። በማቴ2፡8, 11, 13, 14, 20, 21 ይህ ታዲያ ሰብዕና እንዴሌለው አያሳይም።
ሌላም ቦታ እንደነገር (it)ሐፍ ሐ ራሱን ጠርቷል እንደ በር (ዮሐ 10፡9)፤ እንደእንጀራ (ዮሐ 6፡41)፤ እንደወይን (ዮሐ 15፡1)፤ እንደእውነት (ዮሐ14፡6)፤ እንደዐለት (1ቆሮ 10፡4)፤ እንደብርሃን (ዮሐ 8፡12) እንደድንጋይ (1ጴጥ 2፡6-8)፤ እንደቃል (ዮሐ 1፡1)
2)  መጥምቁ ዮሐንስም 8 ጊዜ ነገሮችን በምንጠራበት አጠራር (it) ተጠርቷል ። ሉቃ 1፡59, 60, 62, 63, 66, 67
3)  ሰዎችም እንዲሁ ተጠርተዋል። በዮሐ 6፡39 but raise it up on the last day
 5. መንፈስ ቅዱስ ሰብዕና ካለው እንዴት ነው ታዲያ ሰበእና ያለው ነገር ሰዎችን የሚሞላው (ሉቃ 1፡41) በእሱ የሚጠመቁት (ማቴ 3፡11) ሰዎች የሚቀቡት       (ሐዋ 10፡38)። እነዚህ ነገሮች አንድ ሰብዕና ያለው ነገር መገለጫ አይደሉም። (Reasoning from the Scriptures, Spirit, p380, Jehovah's Witness publication) እንዲሁም ደግሞ በሐዋ 2፡1-4 ላይ መንፈስ ቅዱስ በክርስትያኖች ላይ እንደፈሰሰ እና እንደወረደ ይናገራል። ይህ የሚያሳየው ሰብዕና እንዴሌለው ነው ይላሉ።
             1) ይህ መሙላት የሚለውን አነጋገር መጽሐፍ ቅዱስ ለእየሱስ እንዴት እንደተጠቀመ እንይ። ኤፌ 4፡10 “ወደታች የወረደውም፣ መላውን ፍጥረተ ዓለም ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣውእርሱ ራሱ ነው” እንዲሁም በኤፌ 3፡19 “እስከእግዛብሔር ሙላት ሁሉ ልክ ደርሳችሁ እንድትሞሉ…” ይህን ለመንፈስ ቅዱስ ስለመሙላት በሐዋ 2፡4 ካለው ጋር አወዳድር
             2) ፊሊ 2፡17 “…እንደመጠጥ ቁርባን እንኳ ብፈስ…” ይላል ጳውሎስ በተጨማሪም 2 ጢሞ 4፡6 ማንነት ያለው ሰው ሆኖ እፈሳለሁ ይላል። ዳዊትም በመዝ22፡14 እንዲሁ “…እንደውሃ ፈሰስኩ…” ይላል ይህን ስላሉ ግን ማንነታቸውን (ሰብዕናቸውን) አልተጠራጠርንም። ይህን ለመንፈስ ቅዱስ ከሐዋ2፡17 ከሐ2፡33 ጋር አወዳድር።
             3) ሉቃ 3፡16 ላይ በእሳትና በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል ስለሚል እሳት ሆኖ እንዴት ሰብእና ይኖረዋል ይላሉ። ግን እግዛብሔርም የሚያጠፋ እሳት ተብሎአል ዕብ 12፡29 እና ዘዳ 4፡24
             4) 1 ቆሮ 6፡19 ላይ መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ውስጥ የሚኖር ስለሚል በክርስትያኖች ሁሉ የሚኖር ከሆነ እንዴት ሰብእና ይኖረዋል ይላሉ። ግን ክርስቶስም በእኛ ውስጥ ይኖራል 2 ቆሮ 13፡5፣ ሮሜ8፡10 ። ስለእግዛብሔር አብም በኤፌ 4፡6 “…በሁሉ የሚኖር…” ተብሎአል። 1 ዮሐ 4፡4 በእናንተ የሚኖረው ከአለም ይበልጣል ተብሎአል።
             5) 2 ቆሮ 1፡22 የመንፈስ ቅዱስ ዋስትና በልባችን ያኖረ ስለሚል እንዴት ሰብእና ይኖረዋል ይላሉ። እየሱስም በልባችን እንደሚያድር በኤፌ 3፡17 ይናገራል
             6) ሉቃ 8፡27-30 ላይ አጋንንት በሰው ላይ ገብተውበት ነበር ታዲያ በሰውየው ላይ የ ሁሉ አጋንንት መግባቱ አጋንንት ማንንት ወይም ሰብዕና የላቸውም ሊያስብለን ይችላል።
1.መንፈስ ቅዱስ የእግዛብሔር ሐይል በሰውኛ የተገለጠበት ነው እንጂ ሰብዕና ያለው አይደለም።በመጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ በተደጋጋሚ የምናየው የአጻጻፍ ዘይቤ ነው። ለምሳሌ ጥበብ ልጆች እነዳሏት ተጽፎአል። ሉቃ 7፡35 “እንግዲህ የጥበብ ትክክለኛነት በልጆቿ ሁሉ ዘንድ ተረጋገጠ”። እንዲሁም ሐጢአትና ሞትም እንደንጉስ ተጠርተዋል። ሮሜ 5፡14,21 “…ኀጢአት ባልሠሩት ላይ ሞት ነገሠ።…21 ይህም የሆነው ኀጢአት በሞት እንደነገሠ ሁሉ…” (Reasoning from the Scriptures, Spirit, p380, Jehovah's Witness publication)

      መልስ፡ 1) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነገሮችን በሰውኛ የመግለፅ አፃፃፍ የተለመደ ነው። ከብዙ በጥቂቱ ለምሳሌ ተራሮች ሲያጨበጭቡ ከዋክብት ሲዘምሩ የምናየው አለ። ነገር ግን ባለን ልምምድና ሰውኛ ዕውቀት እነዚህ ሰብዕና(personality) ያላቸው አይደሉም። መንፈስ ቅዱስ ግን አይደለም። ተራራ ሰብዕና እንዴሌለው በልምዳችን እንደምናውቀወ ሁሉ መንፈስ ቅዱስን በልምዳችን ሰብዕና የለውም ማለት አንችልም።
             2) በሰውኛ የተጠቀሱት ግን በልምዳችን የምናውቃቸው ነገሮች እንደ ተራራ ከዋክብት ጥበብ ወዘተ በዚያው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰብዕና እንዴሌላቸው ነገሮች (it) ተብለው ተጠቅሰው እናገኛቸዋለን። አንድም ቦታ ግን መንፈስ ቅዱስ በዚህ መንገድ ተጠቅሶ አናገኘውም።
 3) መንፈስ ቅዱስ በተጠቀሰበት ቦታ ሁሉ እሱ (HE) (ተባዕእ masculine) ተብሎ ነው የተጠቀሰው። ተራራና ከዋክብት ግን በዚህ መንገድ አልተጠሩም።
 4) ባብዛኛው ቦታ ላይ ከዋክብትና ተራሮች ወዘተ በሰውኛ ዘይቤ ሳይሆን በነገር(things) ነው የተጠሩት። በሰውኛ የተጠሩበት ጊዜ እጅግ በጣም ውስን ወይም አንዴ ብቻ ነው።
 5) መንፈስ ቅዱስ ግን ሁሌም በሰውኛ ነው የተጠራው።
 6) መንፈስ ቅዱስ ሰብዕና የለውም የሚሉ ትክክል ከሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ሁሌም በሰውኛ ስለሚጠራው ሰብዕና ያለውንና የሌለውን ነገር የመለያ መንገድ የለንም ማለት ነው።
 7) መንፈስ ቅዱስ ሰብዕና የለውም ለሚሉ እስኪ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የት ቦታ ነው መንፈስ ቅዱስ እንደ ነገር(thing) የተጠራው?

2.በሥላሴ የማያምኑ በሉቃ 1፡35 ላይ መንፈስ ቅዱስ የእግዛብሔር ሐይል ተብሎ ተጠርቷል ይላሉ።

      መልስ፡ 1) መጀመርያ እስቲ ጥቅሱን እናንብበው ሉቃ 1፡35 “…መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑሉ ኀይል ይጸልልሻል፤…” ጥቅሱ መንፈስ ቅዱስ የእግዛብሔር ሐይል ነው አይልም። የምናየው ሁሉት የተያያዙ ዐረፍተ ነገሮችን ነው። በሥላሴ የማያምኑ ለማያያዝ የፈለጉት መንፈስ ቅዱስና ሐይል የሚለውን ነው። እስቲ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሌላ ይኽን የሚመስል እንዲረዳን እንይ ። ሮሜ 1፡16 “ በወንጌል አላፍርም፤ ምክንያቱም ለሚያምን ሁሉ ለድነት የሚሆን የእግዛብሔር ሐይል ነው።” እዚህ ላይ እንደምናየው፡ ወንጌልና የእግዛብሔር ሐይል የተለያዩ ነገሮች ናቸው። የእግዛብሔር ሐይል ያረገው ቃሉን ለሚያምን ስለሚለውጥ ነው እንጂ በራሱ የእግዛብሔር ሐይል አይደለም። ስለዚህ የተያያዘ ዐረፍተ ነገር በሚኖርበት ጊዜ ከዐውዱ ወይንም ከመፅሕፍ ቅዱስ አጠቃላይ ሀሳብ ጋር ካላያያዝን ስህተት ላይ ልንወድቅ እንችላለን። ሌላም ምሳሌ እንይ ማቴ 22፡29 “እየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰ፤ ቅዱሳት መጻሕፍትንና የእግዛብሔርን ሐይል ሰለማታውቁ ትስታላችሁ” በእንግሊዘኛው “Jesus replied, "You are in error because you do not know the Scriptures or the power of God.” አሁንም ቅዱሳት መጻሕፍትንና የእግዛብሔርን ሐይል አንድ ላይ እያዛመደ ነው። ይህ ማለት ቁዱሳት መጻሕፍት በራሳቸው የእግዛብሔር ሐይል እየሆኑ አይደለም።
   
2) ሐዋ 10፡38 ላይ ደግሞ መንፈስ ቅዱስና ሐይል የተለያዩ እንደሆኑ እናያለን “እግዛብሔር የናዝሬቱን እየሱስ በመንፈስ ቅዱስና በኀይል ቀባው፤…” እንግዲህ መንፈስ ቅዱሰ የእግዛብሔር ሐይል ነው ካልን እየሱስ የተቀባው በሐይልና በሐይል ነው ማለት ነው።

3) ሌላው የመከራከርያ ነጥባቸው ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በግሪኩ በሚጠቀስበት ጊዜ ፆታ የለውም። ይህም የሚያሳየው ሰብዕና እንዴሌለው ነው። መንፈስ ቅዱስ በወንድ( masculine) ተጠርቶ ቢሆን ኖሮ ምናልባት ሰብዕና አለው ማለት ይቻል ነበር። እግዛብሔር ግን ሰብዕና እንዴሌለው ሊያሳየን ፈልጎ ያለ ፆታ ገልጾታል ይላሉ።  
መልስ፡ 1)ከአንድ ነገር ማንነት ጋር ፆታ ሙሉ በሙሉ የሚያያይዘው ነገር የለም። የሚያያዘው ከቋንቋው ጋር ነው።
       2)በግሪኩ አዲስ ኪዳን ህፃናት (በሉቃ 1፡41;44; 2፡16; 18፡15 ) ልጆች (ማር 5፡39-41) መንፈስ ቅዱስ አንዳንድ ቦታ ያለፆታ እንደተጠቀሰው እነዚህም ቦታዎች የለፆታ ነው የተጠቀሱት።
       3) ልጃገረድ( Girl) በማቴ 9፡24;25; ማር 5፡41;42 በግሪኩ ያለፆታ ነው የተጠቀሱት።
       4) መላእክት በዕብ 1፡14 በግሪኩ ያለፆታ ነው የተጠቀሱት
       5) አጋንንት በግሪኩ ከ45 ጊዜ በላይ ያለፆታ ነው የተጠቀሱት
       6) በዘፍ 1፡2 ላይ የተጠቀሰው መንፍስ በሴት ፆታ ነው።
       7) መንፈስ (Greek: pneuma) ምንም እንኳን ፆታ ባይኖረውም በአዲስ ኪዳን ውስጥ በሙሉ ሲጠራ እሱ(በወንድ ማንነት)( A masculine pronoun ("He" Greek: ekeinos, literal "that One") ነው የተገለጸው።
       8) ለእግዛብሄር አብ መንፈስ በዮሐ 4፡24 ሲያያዝ ፆታ የለውም። ከእየሱስ ጋር መንፈስ ሲያያዝ በ1ቆሮ15፡45 እንዲሁ ፆታ የለውም። ለህፃኑ እየሱስ በማቴ 2፡8, 11, 13, 14, 19-21 መነፈስ ተያይዞ ሲጠቀስ ፆታ የለውም።
       9) ይህ ከላይ በመንፈስ ቅዱስ ሰብዕና የማያምኑ ያቀረቡት መከራከርያ የግሪክ ቋንቋ እውቀት ላላቸው ሚዛን የሚደፋ አይደለም።          
 
 4.መጽሐፍ ቅዱስ መንፈሰ ቅዱስን ነገሮችን በምንጠራበት አጠራር (it)ሐፍ ሐ 7 ጊዜ ያህል ጠርቶታል። ይህም ሰብዕና እንዴሌለው ያሳያል ይላሉ።
 በ ዮሐ 1፡32; ሮሜ 8፡16,26; 1ቆሮ 12፡11; ዕብ 10፡15,17; 1ጴጥ 1፡11
4)  እየሱስም 5 ጊዜ ያህል ነገሮችን በምንጠራበት አጠራረ (it) ተጠርቷል። በማቴ2፡8, 11, 13, 14, 20, 21 ይህ ታዲያ ሰብዕና እንዴሌለው አያሳይም።
5)  መጥምቁ ዮሐንስም 8 ጊዜ ነገሮችን በምንጠራበት አጠራር (it) ተጠርቷል ። ሉቃ 1፡59, 60, 62, 63, 66, 67
6)  ሰዎችም እንዲሁ ተጠርተዋል። በዮሐ 6፡39 but raise it up on the last day
 5. መንፈስ ቅዱስ ሰብዕና ካለው እንዴት ነው ታዲያ ሰበእና ያለው ነገር ሰዎችን የሚሞላው (ሉቃ 1፡41) በእሱ የሚጠመቁት (ማቴ 3፡11) ሰዎች የሚቀቡት       (ሐዋ 10፡38)። እነዚህ ነገሮች አንድ ሰብዕና ያለው ነገር መገለጫ አይደሉም። (Reasoning from the Scriptures, Spirit, p380, Jehovah's Witness publication) እንዲሁም ደግሞ በሐዋ 2፡1-4 ላይ መንፈስ ቅዱስ በክርስትያኖች ላይ እንደፈሰሰ እና እንደወረደ ይናገራል። ይህ የሚያሳየው ሰብዕና እንዴሌለው ነው ይላሉ።
             1) ይህ መሙላት የሚለውን አነጋገር መጽሐፍ ቅዱስ ለእየሱስ እንዴት እንደተጠቀመ እንይ። ኤፌ 4፡10 “ወደታች የወረደውም፣ መላውን ፍጥረተ ዓለም ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣውእርሱ ራሱ ነው” እንዲሁም በኤፌ 3፡19 “እስከእግዛብሔር ሙላት ሁሉ ልክ ደርሳችሁ እንድትሞሉ…” ይህን ለመንፈስ ቅዱስ ስለመሙላት በሐዋ 2፡4 ካለው ጋር አወዳድር
             2) ፊሊ 2፡17 “…እንደመጠጥ ቁርባን እንኳ ብፈስ…” ይላል ጳውሎስ በተጨማሪም 2 ጢሞ 4፡6 ማንነት ያለው ሰው ሆኖ እፈሳለሁ ይላል። ዳዊትም በመዝ22፡14 እንዲሁ “…እንደውሃ ፈሰስኩ…” ይላል ይህን ስላሉ ግን ማንነታቸውን (ሰብዕናቸውን) አልተጠራጠርንም። ይህን ለመንፈስ ቅዱስ ከሐዋ2፡17 ከሐ2፡33 ጋር አወዳድር።
             3) ሉቃ 3፡16 ላይ በእሳትና በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል ስለሚል እሳት ሆኖ እንዴት ሰብእና ይኖረዋል ይላሉ። ግን እግዛብሔርም የሚያጠፋ እሳት ተብሎአል ዕብ 12፡29 እና ዘዳ 4፡24
             4) 1 ቆሮ 6፡19 ላይ መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ውስጥ የሚኖር ስለሚል በክርስትያኖች ሁሉ የሚኖር ከሆነ እንዴት ሰብእና ይኖረዋል ይላሉ። ግን ክርስቶስም በእኛ ውስጥ ይኖራል 2 ቆሮ 13፡5፣ ሮሜ8፡10 ። ስለእግዛብሔር አብም በኤፌ 4፡6 “…በሁሉ የሚኖር…” ተብሎአል። 1 ዮሐ 4፡4 በእናንተ የሚኖረው ከአለም ይበልጣል ተብሎአል።
             5) 2 ቆሮ 1፡22 የመንፈስ ቅዱስ ዋስትና በልባችን ያኖረ ስለሚል እንዴት ሰብእና ይኖረዋል ይላሉ። እየሱስም በልባችን እንደሚያድር በኤፌ 3፡17 ይናገራል






No comments:

Post a Comment