ማቴ 12: 40 ያለውን በመጥቀስ ነው "ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።"
ኢየሱስ ክርስቶስ "የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።" ስላለ: ይህ እንዲሙዋላ በግድ "ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት" በመቃብር ማሳለፍ አለበት::
ስለዚህ ኢየሱስ የተሰቀለው ሮብ ነው የሚል የተሳሳተ መረዳት ላላቸው ሰዎች ዝርዝር የሆነ መልስ
1. መጀመርያ በአይሁዳውያን ባህል ወይም በመፅሐፍ ቅዱስ ቃል ያለው ሰንበት አንድ ነው እሱም ቅዳሜ ነው እንጂ ሁለት ሰንበት የለም
ኦሪት ዘጸአት 20:8-9 "የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ። ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም።"
አንዳንዶች ዘሌ 23:5-7 ጠቅሰው ሁለት ሰንበት ነበረ ይላሉ
"በመጀመሪያው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ሲመሽ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው። በዚህም ወር በአሥራ አምስተኛው ቀን ለእግዚአብሔር የቂጣ በዓል ነው ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ብሉ። በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ የተግባር ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።"
እነሱ ይህን ጥቅስ ተደግፈው "የእግዝአብሔር ፋሲካ" ይህ ቀን ሰንበት ተብሎ ይጠራል ይሉና ይህ ቀን ደግሞ ሐሙስ ስለሆነ ኢየሱስ የተሰቀለው ሮብ ነው ይላሉ:: ስለዚህ እንደነሱ ከሆነ ሮብ ግማሽ ቀን ስለሆነ አይቆጠርም: የሚቆጠረው ከሮብ ማታ ጀምሮ ነው ይሉናል:: ሁላችንም እንደምናውቀው የእራኤላውያን ሰንበት ቅዳሜ ነው:: ታዲያ ይህ ሰንበት (ቅዳሜ) የሚጀምረው ከአርብ ከምሽቱ አስራሁለት ሰዓት ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ከምሽቱ አስራሁለት ሰዓት ነው:: በመፅሐፍ ቅዱስም እግዝአብሔር አንድ ቀን ብሎ ሲጠራ መጀመርያ የሚጀምረው ከሌሊት ነው...
ዘፍጥረት 1
5 እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን።
8 እግዚአብሔር ጠፈርን ሰማይ ብሎ ጠራው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ ሁለተኛ ቀን።
18 በቀንም በሌሊትም እንዲሠለጥኑ፥ ብርሃንንና ጨለማንም እንዲለዩ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ
ሆነ አየ።
19 ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አራተኛ ቀን።
ስለዚህ እስራኤላውያን ይህን የእግዝአብሔር ቀን አቆጣጠር ስለሚረዱ: እነሱም አንድ ሙሉ ቀን የሚጀምሩት ከማታ ጀምሮ ነው:: ስለዚህ ለምሳሌ ቅዳሜ የሚጀምረው ከአርብ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ነው ቅዳሜ ደግሞ የሚያልቀው ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ነው::
በእዚህ ትክክለኛ በሆነ የመፅሐፍ ቅዱስም ሆነ የእስራኤላውያን አቆጣጠር ከቆጠርን
ኢየሱስ የተሰቀለው ሮብ ነው የሚሉ ሰዎች እንደ እነሱ ሃሳብ ከሆነ ማታ ማታዎቹን እንቁጠራቸው....
·
ሮብ ከ12
ሰዓት በሁዋላ ሐሙስ ምሽት ነው --- አንድ ሌሊት
·
ሐሙስ ከ12
ሰዓት በሁዋላ አርብ ምሽት ነው --- ሁለተኛ ሌሊት
·
አርብ ከ12
ሰዓት በሁዋላ ቅዳሜ ምሽት ነው --- ሶስተኛ ሌሊት
·
ቅዳሜ ከ12
ሰዓት በሁዋላ እሁድ ምሽት ነው --- አራተኛ ሌሊት
እንግዲህ እንደነዚህ ሰዎች መረዳት ከሆነ: ኢየሱስ አራት ሌሊቶችን ነው በመቃብር ያሳለፈው ማለት ነው ምክንያቱም መፅሐፍ ቅዱስ ሲነግረን ኢየሱስ ከመቃብር የተነሳው እሁድ ማለዳ ነው (ማር 16:9)
ማር 16:9 "ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሣ ጊዜ፥ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግደላዊት ማርያም ታየ። When Jesus rose
early on the first day of the week"
ኢየሱስ የተሰቀለው ሮብ ነው የሚሉ ሰዎች: እንደ እነሱ ሃሳብ ቀኖቹን እንቁጠራቸው....
ኢየሱስ በመስቀል ላይ የተሰቀለው 6 ሰዓት ላይ ሲሆን የሞተው ደግሞ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ነው:: ስለዚህ
·
ሮብ ቀን
--- ግማሽ ቀን
·
ሐሙስ ቀን
--- አንድ ሙሉ ቀን
·
አርብ ቀን
--- አንድ ሙሉ ቀን
·
ቅዳሜ ቀን
--- አንድ ሙሉ ቀን
እንግዲህ እንደነዚህ ሰዎች መረዳት ከሆነ: ኢየሱስ ሶስት ሙሉ ከግማሽ ቀን ነው በመቃብር ያሳለፈው ማለት ነው::
በእዚያ ላይ ከላይ እንዳየነው እንደነዚህ ሰዎች መረዳት ከሆነ ኢየሱስ ተሰቅሎ ከሞተ ሶስተኛው ቀን ቅዳሜ (ሰንበት) ነው:: መፅሐፍ ቅዱስ ግን ኢየሱስ ተሰቅሎ ከሞተ ሶስተኛው ቀን ቅዳሜ (ሰንበት) ካለፈ በሁዋላ በሳምንቱ የመጀመርያ ቀን እሁድ እንደሆነ ነው የሚነግረን::
ሉቃስ 24
1 ነገር ግን #ከሳምንቱ_በመጀመሪያው_ቀን ያዘጋጁትን ሽቱ ይዘው ከእነርሱም ጋር አንዳንዶቹ ወደ መቃብሩ እጅግ ማልደው መጡ። ድንጋዩንም ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት፥ ገብተውም የጌታን የኢየሱስን ሥጋ አላገኙም።..... 13 እነሆም፥ ከእነርሱ
ሁለቱ #በዚያ_ቀን ከኢየሩሳሌም ስድሳ ምዕራፍ ያህል ወደሚርቅ ኤማሁስ ወደሚባል መንደር ይሄዱ ነበር፤ 14 ስለዚህም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር። 15 ሲነጋገሩና ሲመራመሩም፥ ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር፤ 16 ነገር ግን እንዳያውቁት ዓይናቸው ተይዞ ነበር። 17 እርሱም። እየጠወለጋችሁ ስትሄዱ፥ እርስ በርሳችሁ የምትነጋገሩአቸው እነዚህ ነገሮች ምንድር ናቸው? አላቸው። 18 ቀለዮጳ የሚባልም አንዱ መልሶ። አንተ በኢየሩሳሌም እንግዳ ሆነህ ለብቻህ ትኖራለህን? በእነዚህ ቀኖች በዚያ የሆነውን ነገር አታውቅምን? አለው። 19 እርሱም። ይህ ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት። በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፤ 20 እርሱንም የካህናት አለቆችና መኳንንቶቻችን ለሞት ፍርድ እንዴት አሳልፈው እንደ ሰጡትና እንደ ሰቀሉት ነው። 21 እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ አድርገን ነበር፤ ደግሞም ከዚህ ሁሉ ጋር #ይህ_ከሆነ_ዛሬ_ሦስተኛው_ቀን_ነው።... 45 በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤ 46 እንዲህም አላቸው። ክርስቶስ መከራ ይቀበላል #በሦስተኛውም_ቀን ከሙታን ይነሣል፥."
እዚህ ጋር በጣም በግልፅ እንደምናየው: እነእዚህ የኤማዎስ መንገደኞች ለኢየሱስ ለእራሱ እሱ መሆኑን ሳያውቁ: ኢየሱስ በመሰቀል ላይ ከተሰቀለ ይህን ለእሱ በሚነግሩበት ቀን ላይ "ዛሬ ሦስተኛው ቀን ነው" ብለው እየነገሩት ነው:: "ዛሬ" የሚሉት ደግሞ ቁጥር 1 ላይ እንደምናየው "በሳምንቱ በመጀመርያው ቀን" ነው:: ያ ቀን ደግሞ እሁድ ነው:: ኢየሱስ ሲያስረዳቸው በመጨረሻ "በሦስተኛው ቀን" ከሙታን ይነሳል ነው ያላቸው::
ስለዚህ ሮብ ተሰቀለ ለሚሉ ሰዎች በእነሱ መረዳት መሠረት ሶስተኛው ቀን ቅዳሜ ሲሆን መፅሐፍ ቅዱስ ለሚከተሉ ሰዎች ደግሞ ሶስተኛው ቀን እሁድ ነው::
ሌላው የእነዚህ ሮብ ተሰቀለ የሚሉ ሰዎች መከራከርያ ነጥብ: ኢየሱስ በማቴ 12: 40 ያለውን በመጥቀስ ነው "ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።"
ኢየሱስ ክርስቶስ "የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።" ስላለ: ይህ እንዲሙዋላ በግድ "ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት" በመቃብር ማሳለፍ አለበት ይላሉ::
መጀመርያ ኢየሱስም ሆነ ሌሎች ስለዚህ ምን እንዳሉ እናስቀምጥ በተለያየ ቦታ...
#በሦስተኛውም_ቀን (On the third
day)
ማቴ 17:22-23 "በገሊላም ሲመላለሱ ኢየሱስ። የሰው ልጅ በሰዎች እጅ አልፎ ይሰጥ ዘንድ አለው፥ ይገድሉትማል፥ #በሦስተኛውም_ቀን ይነሣል አላቸው። እጅግም አዘኑ።
ማቴ 20:19 " ሊዘባበቱበትም ሊገርፉትም ሊሰቅሉትም ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፥ #በሦስተኛውም_ቀን ይነሣል አላቸው።"
ሉቃ 19:21-22 "እርሱ ግን። የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል በሽማግሌዎችም በካህናት አለቆችም በጻፎችም ሊጣል ሊገደልም #በሦስተኛውም_ቀን ሊነሣ ይገባዋል ብሎ ለማንም ይህን እንዳይናገሩ አስጠንቅቆ አዘዘ።"
የሐዋ ሥራ 10:40 "እርሱን እግዚአብሔር #በሦስተኛው_ቀን አስነሣው ይገለጥም ዘንድ ሰጠው፤
1 ቆሮ 15:4 " መጽሐፍም እንደሚል #በሦስተኛው_ቀን ተነሣ፥"
#ከሦስት_ቀን_በኋላ After three days
ማቴ 27 63 "ጌታ ሆይ፥ ያ አሳች በሕይወቱ ገና ሳለ። #ከሦስት_ቀን_በኋላ እነሣለሁ እንዳለ ትዝ አለን።"
ማር 8:31 የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም #ከሦስት_ቀንም_በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር።
እንግዲህ ኢየሱስ ከሙታን የተነሳው መቼ ነው ለሚለው መፅሐፍ ቅዱስ እነዚህ መልሶች አሉት....
·
ከሶስት ቀንና
ከሶስት ሌሊት በሁዋላ
·
በሦስተኛውም ቀን
·
በሦስተኛው ቀን
·
ከሦስት ቀን
በሁዋላ
እንግዲህ ኢየሱስ በመቃብር የቆየው “ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት” የሚለውን ወስደን “72 ሰዓት” ካደረግነው: በእዚህ መረዳት ከቃሉ ጋር ልንጋጭ ነው:: ምክንያቱም ከ72 ሰዓት በሁዋላ ከተነሳ: ከሦስት ቀን በሁዋላ የሚለው ጥቅስ እንጂ: በሦስተኛውም ቀን ሆነ: በሦስተኛው ቀን: የሚሉት ጥቅሶች ጋር ልንጋጭ ነው:: ቃሉ ደግሞ አይጋጭም:: ስለዚህ "ሶስት ቀንና ሶስት ሌሊት" የሚለው ነገር "ሶስት ቀን" ወይም "በሶስተኛው ቀን" ለማለት በጊዜው የሚጠቀሙበት አባባል እንጂ 72 ሰዓት ማለት አይደለም:: ለምሳሌ መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ "ሰውን" ለመጥቀስ "ሥጋና ደም" የሚል አባባል አለ:: ልክ እንደዛ "ሶስት ቀን" ለማለት የሚጠቀሙበት አባባል ነው::
ሌላ ምሳሌ ከመፅሐፍ ቅዱስ
የማቴዎስ ወንጌል ኢየሱስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት እንደፆመ ይነግረናል
ማርቆስና ሉቃስ ደግሞ አርባ ቀን እንደፆመ ይነግሩናል
ስለዚህ አርባ ቀንና ሌሊት ማለት አርባ ቀን ማለት ነው
ሌላ ምሳሌ ከመፅሐፍ ቅዱስ...
"ከሶስት ቀንና ከሶስት ሌሊት በሁዋላ" የሚለው አባባል 72 ሰዓት ነው የሚል መረዳት ላላቸው --- መፅሐፍ ቅዱስ ይህን "አራተኛው ቀን" ነው የሚለው
የሐዋ ሥራ 10 ...
1 በቂሣርያም ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራ የመቶ አለቃ የሆነ ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበረ።
3 ከቀኑም ዘጠኝ
ሰዓት ያህል። ቆርኔሌዎስ ሆይ የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው። ---- የመጀመርያ ቀን
9 እነርሱም በነገው ሲሄዱ ወደ ከተማም ሲቀርቡ፥ ጴጥሮስ በስድስት ሰዓት ያህል ይጸልይ ዘንድ ወደ ጣራው ወጣ። --- ሁለተኛ ቀን
23 እርሱም ወደ ውስጥ ጠርቶ እንድግድነት ተቀበላቸው። በነገውም ተነሥቶ ከእነርሱ ጋር ወጣ፥ በኢዮጴም ከነበሩት ወንድሞች አንዳንዶቹ ከእርሱ ጋር አብረው ሄዱ። --- ሦስተኛ ቀን
24 በነገውም ወደ ቂሣርያ ገቡ፤ ቆርኔሌዎስም ዘመዶቹንና የቅርብ ወዳጆቹን በአንድነት ጠርቶ ይጠባበቃቸው ነበር። --- አራተኛ ቀን
30 ቆርኔሌዎስም እንዲህ አለው። #በዚች_ሰዓት_የዛሬ_አራት_ቀን የዘጠኝ ሰዓት ጸሎት በቤቴ እጸልይ ነበር፤ እነሆም፥ የሚያንጸባርቅ ልብስ የለበሰ ሰው በፊቴ ቆመና።"
ከእዚህ እንደምንረዳው ልክ መልዐኩ በመጣበት ቀንና: ሰዎቹ ተልከው ጴጥሮስ ጋር ሲደርሱ -- 24 ሰዓት
ጴጥሮስ ከእነሱ ጋር ተነስቶ ሲሄድ --- 24 ሰዓት
በነጋታው ጴጥሮስ ከቆርኔሊዎስ ጋር ተገናኝቶ ቆርኔሊዎስ ስለሁኔታው ሲነግረው --- 24 ሰዓት
በጠቅላላው 72 ሰዓቶች በሰዎቹ ቀን አቆጣጠር ግን 4 ቀኖች
ሌላ ምሳሌ ከመፅሐፍ ቅዱስ...
ሶስት ቀንና ሶስት ሌሊት የሚለው አባባል ሶስት ቀን ለማለት እንጂ 72 ሰዓት ማለት እንዳልሆነ
1 ሳሙ 30 12- 13 "ከበለሱም ጥፍጥፍ ቁራጭና ሁለት የወይን ዘለላ ሰጡት #ሦስት_ቀንና_ሦስት_ሌሊት እንጀራ አልበላም ውኃም አልጠጣም ነበርና በበላ ጊዜ ነፍሱ ወደ እርሱ ተመለሰች። ዳዊትም፦ አንተ የማን ነህ? ከወዴት መጣህ? አለው። እርሱም፦ እኔ የአማሌቃዊ ባሪያ ግብጻዊ ብላቴና ነኝ #ከሦስት_ቀንም_በፊት ታምሜ ነበርና ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ።"
ሌላ ምሳሌ ከመፅሐፍ ቅዱስ
ሦስት ቀን ሌሊቱንና ቀኑንማለት ሦስት ቀን ማለት ነው እንጂ 72 ሰዓት ማለት አይደለም
አስ 4:16; እና አስ 5:1
4:16 "ሄደህ በሱሳ ያሉትን አይሁድ ሁሉ ሰብስብ፥ ለእኔም ጹሙ #ሦስት_ቀን_ሌሊቱንና_ቀኑን አትብሉም፥ አትጠጡም እኔና ደንገጥሮቼ ደግሞ እንዲሁ እንጾማለን ምንም እንኳ ያለ ሕግ ቢሆን ወደ ንጉሡ እገባለሁ ብጠፋም እጠፋለሁ።"
5:1 "#በሦስተኛውም_ቀን አስቴር ልብሰ መንግሥትዋን ለብሳ በንጉሡ ቤት ትይዩ በንጉሡ ቤት በውስጠኛው ወለል ቆመች ንጉሡም በቤቱ መግቢያ ትይዩ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ በንጉሡ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ነበር።
የእስራኤላውያን ታሪክ ያጠኑ ሰዎች እንደሚሉት ሌሎቹ ቀኖች "የመጀመርያው ቀን": "ሁለተኛው": "ሶስተኛው" እያሉ ሲጠሩ አርብን ግን ስድስተኛው ቀን ብለው አይጠሩትም:: ልክ ቅዳሜን ሰባተኛው ቀን ብለው እንደማይጠሩት:: ስለዚህ አርብን
በአማርኛ - የመዘጋጃው ቀን
በእንግሊዘኛው -
reparation day
በአራማይክ - arubta
በግሪኩ - paraskeue
ብለው ነው ነው የሚጠሩት:: ኢየሱስ የተሰቀለው ደግሞ አርብ ለሰንበት የማዘጋጀት ቀን ነበር የተሰቀለው::
ስለዚህ ኢየሱስ
ለሰንበት በማዘጋጃ ቀን ተሰቀለ ከእዛም ሰንበት ካለፈ በሁዋላ ተነሳ -ማቴ 27:62; 28:1
--ማር 15:42; 16:1
ሌላው ኢየሱስ ሮብ ነው የተሰቀለው የሚሉ ሰዎች ለመከራከርያ የሚያቀርቡት ማር 16:1ን ነው ...
"ሰንበትም ካለፈ በኋላ መግደላዊት ማርያም የያዕቆብም እናት ማርያም ሰሎሜም መጥተው ሊቀቡት ሽቱ ገዙ። ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን እጅግ በማለዳ ፀሐይ ከወጣ በኋላ ወደ መቃብር መጡ።"
እነሱ እንደሚሉት ከሆነ ሮብ ኢየሱስ ተሰቀለ ሐሙስ ሰንበት ነበር ከእዛ አርብ ሽቶና የሚያስፈልገውን ገዙ: ከእዛም ሁለተኛው ሰንበት ካለፈ በሁዋላ እሁድ ጥዋት ወደመቃብሩ መጡ ነው::
ይህ ስህተት የመጣው የአይሁድን ቀን አቆጣጠር ካለመረዳት ነው:: ምክንያቱም ከላይ እንዳስቀመጥኩት ሰንበት የሚጀምረው በአይሁድ አቆጣጠር አርብ ከምሽቱ 12 ሰዓት ሲሆን: ሰንበት የሚያልቀው ደግሞ ቅዳሜ ከምሽቱ 12 ሰዓት ነው:: ስለዚህ እነዚህ ሴቶች ቅዳሜ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ የሚፈልጉትን መግዛት ይችላሉ ሰንበት ስላለፈ:: ይህ የአይሁድ አቆጣጠር ከገባን ወደማይሆን ስህተት አንገባም::
ሌላው ኢየሱስ ሮብ እንዳልተሰቀለ ማስረጃው ይህ ነው
እነዚህ ኢየሱስ ሮብ ተሰቀለ የሚሉ ሰዎች እንዳሉት ኢየሱስ ሮብ ከተሰቀለ እና ሐሙስ እነሱ እንደሚሉት ሰንበት ከሆነ: እነዛ ኢየሱስን ሊቀቡ ሽቶ አዘጋጅተው የሄዱ ሴቶች ሽቶውን ማዘጋጀት የጀመሩት ኢየሱስ ተሰቅሎ የተቀበረ እለት እንደሆነ መፅሐፍ ቅዱስ ይናገራል:: ከእዛም ሀሙስ ሰንበት ነበረ የሚሉት ሰዎች እነዚህ ሴቶች ሐሙስ በሰንበት አረፉ ከእዛ አርብ ቀን ወደመቃብር ሄዱ ማለት ነው እንደእነዚህ ሰዎች አስተሳሰብ:: መፅሐፍ ቅዱስ ግን እነዚህ ሴቶች የሄዱት እሁድ በሳምንቱ መጀመርያ ቀን እንደሆነ ነው የሚነግረን:: ስለዚህ የእነዚህ ሰዎች መረዳት ከመፅሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጭ የስህተት መረዳት መሆኑን በቀላሉ መረዳት እንችላለን::
ሉቃ 23:50 - 56
"እነሆም፥ በጎና ጻድቅ ሰው የሸንጎ አማካሪም የሆነ ዮሴፍ የሚባል ሰው ነበረ፤ ይህም በምክራቸውና
በሥራቸው አልተባበረም ነበር፤ አርማትያስም ከምትባል ከአይሁድ ከተማ ሆኖ እርሱ ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር። ይኸውም ወደ ጲላጦስ ቀርቦ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው፤ አውርዶም በተልባ
እግር ልብስ ከፈነው፥ ማንም ገና ባልተቀበረበት ከዓለትም በተወቀረ መቃብር አኖረው። የመዘጋጀት ቀንም ነበረ፤ ሰንበትም ሊጀምር ነበረ። ከገሊላም ከእርሱ ጋር የመጡት ሴቶች ተከትለው መቃብሩን ሥጋውንም እንዴት እንዳኖሩት አዩ። ተመልሰውም ሽቱና ቅባት አዘጋጁ። በሰንበትም እንደ ትእዛዙ ዐረፉ።"
በመጨረሻም እንደመፅሐፍ ቅዱስ መሠረት በአጭሩ ልመልስ...
ሦስተኛው ቀን -- the third day -- 3 day and 3 night -- ሦስት ቀን ሌሊቱንና ቀኑን -- ከሦስት ቀንም
በኋላ --- በሦስተኛው ቀን
ተነሣ፥ -- በሦስተኛውም ቀን
እነዚህ ሁሉ አንድ አይነት አባባል ናቸው ስለዚህ -- ሦስት ቀን
ሌሊቱንና ቀኑን -- የሚለው አባባል
72 ሰዓት ማለት አይደለም ነገር ግን 72 ሰዓት ነው ብለን ካሳብን የቆርኔሊዎስን ታሪክ በሐዋርያት ሥራ ላይ ከላይ እንዳነበብነው አራተኛው ቀን ማለት ነው
ስለዚህ ኢየሱስ በመዘጋጃው ቀን አርብ ተሰቀለና ሞተ ተቀበረ --- አንደኛው ቀን
ኢየሱስ በሰንበት ቀን በመቃብር ውስጥ ነበር --- ሁለተኛ ቀን
ኢየሱስ እሁድ ማለዳ ከሞት ተነሳ --- ሶስተኛ ቀን
ይህ ነው እንደመፅሐፍ ቅዱስ የሆነ ትክክለኛ መረዳት
No comments:
Post a Comment