Tuesday, January 27, 2015

ቃሉ እንደሚለን ድነት በእምነት

ቃሉ እንደሚለን ድነት በእምነት

1. እኔ ከቃሉ ላይ እንደተረዳሁት ሰው ድነትን (salvation) የሚያገኘው በእምነት ነው:: እምነት ሲደመር ሥራ ወይም ስርአትን በመፈፀም አይደለም

ማስረጃ
1.1 ኤፌ 2:8-9 "ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።" 

1.2 ሮሜ 3:28-30 "28 ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና። ወይስ እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ ደግሞ አምላክ አይደለምን? አዎን፥ የተገረዘን ስለ እምነት ያልተገረዘንም በእምነት የሚያጸድቅ አምላክ አንድ ስለ ሆነ የአሕዛብ ደግሞ አምላክ ነው።"

1.3 ሮሜ 4:5 "ነገር ግን ለማይሠራ፥ ኃጢአተኛውንም በሚያደድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ"

1.4 ሮሜ5:1 "እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ፤"

1.5 ሮሜ 9:30, "እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው፤"

1.6 ሮሜ10:4, "የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።"

1.7 ሮሜ 11:6 "በጸጋ ከሆነ ግን ከሥራ መሆኑ ቀርቶአል፤ ጸጋ ያለዚያ ጸጋ መሆኑ "

1.8 ገላትያ 2:16 "ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን አውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል።"

1.9 ገላትያ 2:21 "የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።

1.10 ገላትያ 3:5-6, " እንግዲህ መንፈስን የሚሰጣችሁ በእናንተም ዘንድ ተአምራት የሚያደርግ፥ በሕግ ሥራ ነውን ወይስ ከእምነት ጋር በሆነ መስማት ነው? እንዲሁ አብርሃም በእግዚአብሔር አመነና ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት"

1.11 ገላትያ3:24, "እንደዚህ በእምነት እንጸድቅ ዘንድ ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን ሆኖአል፤"

1.12 ፊሊጲሲቶስ 3:9 "በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤"
እንግዲህ በተደጋጋሚ ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን ካለ ሐዋርያው ያዕቆብስ ሥራ ብሎ የለም እንዴ ብሎ መጠየቅ ትክክለኛ ጥያቄ ነው

ያዕቆብ 2:14-25 “ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን? ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፥ ከእናንተ አንዱም። በደኅና ሂዱ፥ እሳት ሙቁ፥ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል?

እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው። ነገር ግን አንድ ሰው። አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል። 
እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል። አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን? 
አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን? እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን? መጽሐፍም። አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ። ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ። 

እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን? ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።”

መጀመርያ መረዳት ያለብን መፅሐፍ ቅዱስ እርስ በእርሱ አይጋጭም:: ሐዋርያው ጳውሎስ ፃፈው: ሐዋርያው ያዕቆብ: ምንጩ አንድ ነው: እሱም እግዝአብሔር መንፈስ ቅዱስ:: ስለዚህ ይህን መረዳት ከያዝን ጳውሎስ ሥራ ሳይሆን እምነት ነው የሚያድነው ካለ: የያዕቆብም መረዳት ከእዚህ የተለየ ሊሆን አይችልም:: ታዲያ ለምን ሥራን ጨመረ ብለን ብንጠይቅ ምክንያቱ ይህ ነው:-

ያዕቆብ ሰው በእምነት እና በሥራ ይድናል እያለ ሳይሆን: አንድ ሰው ምንም ዓይነት በጎ ሥራዎችን በሕይወቱ ሳይታዩ ነገር ግን በሕይወቱ የሚታየው ክፋት ብቻ ሆኖ: በአፉ ብቻ አምናለሁ ስላለ ብቻ ድነት ሊያገኝ አይችልም እያለ ነው፡፡ 

ያዕቆብ በክርሰቶስ የሆነ እውነተኛ እምነት የተለወጠን ህይወት እና በጎ ሥራዎችን ይፈጥራል የሚለውን ነጥብ እያጎላ ነው(የያዕቆብ መልዕክት 2፤20-26)፡፡ 

በድጋሚ ያዕቆብ መጽደቅ በእምነት እና በሥራም ጭምር ነው እያለ አይደለም:: ነገር ግን በእውነት በእምነት የጸደቀ ያ ሰው ይልቅ በህይወቱ በጎ ሥራዎች ይኖረዋል:: አንድ ሰው አማኝ እንደሆነ ቢናገር ነገር ግን በህይወቱ በጎ ሥራዎች ከሌሉ እሱ በክርስቶስ እውነተኛ እምነት የላቸውም ይሆናል፡፡ (የያዕቆብ መልዕክት 2፤14፤17፤20፤26)

ጳውሎስ በጽሑፎቹ ውስጥ ተመሳሳይ ነገር ይናገራል፡፡ የመልካም ፍሬ አማኞች በህይወታቸው በገላቲያ 5፤22-23 ውስጥ የተዘረዘሩትን ሊኖራቸው ይገባቸዋል፡፡ ጳውሎስ ወዲያውኑ እኛ በሥራ ሳይሆን በእምነት እንደዳንን ከነገረን በኃላ መልካም ሥራዎችን ለማድረግ እንደተፈጠርን ይነግረናል፡፡ (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፤10) ልክ ያዕቆብ ባዳረገው የህይወት ለውጥ ያህል ጳውሎስ ይጠብቃል፤

ለማጠቃለል አንድ ሰው ድነትን የሚያገኘው እግዝአብሔር የሰጠውን ፀጋ (ቲቶ 2:11"ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤") በእምነት በኩል እንጂ: በሥራ በጥረት አይደለም (ኤፌ 2:8-9 "ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።"):: 

ይህንን ስለድነት ቁልፍ የሆነ ነገር ከተረዳን: ሐዋርያው ጳውሎስም ሆነ ሐዋርያው ያዕቆብ እንደተናገሩት እውነተኛ የድነት እምነት ከሆነ ሰው ያመነው: በእዚህ አምኖ በዳነው ሰው ሕይወት ውስጥ: የሚታይ ፍሬ (ፍሬ ማለት ውጤት ማለት ነው) አለ:: ይህም ፍሬ መልካም ሥራ ማለት ነው: ልክ በገላ 5:22 የተጠቀሰው..."የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።"

እንዲሁም አምኖ የዳነ ሰው እንዲፈፅም የታዘዘው ነገር አለ እሱም አንደኛው ጥምቀት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የጌታ ራት ናቸው:: 

አንድ የተሰጠውን ፀጋ በእምነት ተቀብሎ የዳነ ሰው መጠመቅ አለበት:: #እደግመዋለሁ: አንድ የተሰጠውን ፀጋ በእምነት ተቀብሎ የዳነ ሰው መጠመቅ አለበት:: ይህ ሰው ግን የሚጠመቀው አንድ የጌታ ትዕዛዝ ስለሆነ: ሁለት መጠመቅ ማለት: ከኢየሱስ ጋር ተቀብሬ በትንሣኤው ተነስቻለሁ ብሎ መተባበሩን ደግሞ ለአለም ይህን የሚያውጅበት ነው

ማስረጃ
ሮሜ 6:3-5 "ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን። ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤"
እስቲ ከመፅሐፍ ቅዱስ ማስረጃ እንይ... 

የሐዋ ሥራ 10:44-47 "ጴጥሮስ ይህን ነገር ገና ሲናገር ቃሉን በሰሙት ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ። ከጴጥሮስም ጋር የመጡት ሁሉ ከተገረዙት ወገን የሆኑ ምዕመናን በአሕዛብ ላይ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ስለ ፈሰሰ ተገረሙ፤ በልሳኖች ሲናገሩ እግዚአብሔርንም ሲያከብሩ ሰምተዋቸዋልና። በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ። እነዚህ እንደ እኛ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ እንዳይጠመቁ ውኃን ይከለክላቸው ዘንድ የሚችል ማን ነው? አለ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስምም ይጠመቁ ዘንድ አዘዛቸው። ከዚህ በኋላ ጥቂት ቀን እንዲቀመጥ ለመኑት።"

የሐዋ ሥራ 19 1-7 "አጵሎስም በቆሮንቶስ ሳለ ጳውሎስ በላይኛው አገር አልፎ ወደ ኤፌሶን መጣ፥ አንዳንድ ደቀ መዛሙርትንም አገኘ። ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበላችሁን? አላቸው። እነርሱም። አልተቀበልንም መንፈስ ቅዱስ እንዳለ ስንኳ አልሰማንም አሉት። እንኪያ በምን ተጠመቃችሁ? አላቸው። እነርሱም። በዮሐንስ ጥምቀት አሉት። ጳውሎስም። ዮሐንስስ ከእርሱ በኋላ በሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ ዘንድ ለሕዝብ እየተናገረ በንስሐ ጥምቀት አጠመቀ አላቸው። ይህንም በሰሙ ጊዜ በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ፤ ጳውሎስም እጁን በጫነባቸው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው በልሳኖችም ተናገሩ፥ ትንቢትም ተናገሩ። ሰዎቹም ሁሉ አሥራ ሁለት ያህሉ ነበር።"

ሐዋ 8:12-16 "ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እየሰበከላቸው ፊልጶስን ባመኑት ጊዜ፥ ወንዶችም ሴቶችም ተጠመቁ። ሲሞንም ደግሞ ራሱ አመነ፤ ተጠምቆም ከፊልጶስ ጋር ይተባበር ነበር፤ የሚደረገውንም ምልክትና ታላቅ ተአምራት ባየ ጊዜ ተገረመ። በኢየሩሳሌምም የነበሩት ሐዋርያት የሰማርያ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንደተቀበሉ ሰምተው ጴጥሮስንና ዮሐንስን ሰደዱላቸው። እነርሱም በወረዱ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ይቀበሉ ዘንድ ጸለዩላቸው፤ በጌታ በኢየሱስ ስም ብቻ ተጠምቀው ነበር እንጂ ከእነርሱ በአንዱ ላይ ስንኳ ገና አልወረደም ነበርና።"

ዮሐ 20:21-22 "ኢየሱስም ዳግመኛ። ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ አብ እንደ ላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለሁ አላቸው። ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና። መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።"... 

እዚህ ጋር ደቀመዛሙርቱ ወይም ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ ሆነዋል ይህ ድነታቸውን ያሳያል ልብ በይ ሰው የሃጥያአት ይቅርታ አግኝቶ እንዲነፃ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሞቶ ዋጋ መከፈል ደሙን ማፍሰስ ነበረበት ስለዚህ ሐዋርያት መንፈሳዊ መንፃት ያገኙት ኢየሱስ ሞቶ ከተነሳ በሁዋላ ነው ስለዚህ እዚህ ጋር ድነትን አገኝተዋል የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ ሆነዋል

ቀጥሎ ምንም እንኩዋ የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ ቢሆንም በመንፈስ ቅዱስ በመጠመቅ ሃይል እንዲቀበሉ ከኢየሩሳሌም አትውጡ ይላቸዋል ኢየሱስ... 

የሐዋ ሥራ 1 4-8 "ከእነርሱም ጋር አብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፥ ነገር ግን። ከእኔ የሰማችሁትን አብ የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቁ፤ 5 ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኃላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ አለ። 6 እነርሱም በተሰበሰቡ ጊዜ። ጌታ ሆይ፥ በዚህ ወራት ለእስራኤል መንግሥትን ትመልሳለህን? ብለው ጠየቁት። 7 እርሱም። አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም፤ 8 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።"

ለማጠቃለል: በአዲስ ኪዳን ያለው የውሃ ጥምቀት አንድ ነው:: ነገር ግን ተጨማሪ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የሚባል አለ: ከላይ የሰጠሁት ማስረጃ እንደሚያሳየው:: እነዚህ ሁለት ጥምቀቶች በአንድ ጊዜ ሊሆኑ ይችላሉ:: ደግሞ አንዱ አንዱን ሊቀድም ይችላል:: ሁለቱም ጥምቀቶች ግን ለድነት (salvation) ብለን የምናደርጋቸው ሳይሆኑ: አንድ በእምነት የዳነ ሰው ከድነት በሁዋላ የሚፈፅማቸው ናቸው::

ስለዚህ አንድ አምኖ የዳነ ሰው እደግመዋለሁ: አምኖ የዳነ ሰው የውሃ ጥምቀት ይወስዳል:: መተባበሩን ለመግለፅ:: ከእዛም በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ አለበት:: ለአገልግሎት ሃይል ለማግኘት::
 እንግዲህ ስለድነት (salvation) በተቻለኝ መጠን በዝርዝር ለማስቀመጥ ሞክሪያለሁ አንተም ሆንክ እንዳንተ ተመሳሳይ መረዳት ያላቸው ሰዎች ትክክለኛው የእግዝአብሔር ቃል ስለድነት ምን እንደሚል ከነማስረጃው አስቀምጬልሃለሁ ስለድነት አስረግጬ ከጥምቀት በፊት የተናገርኩት ትክክለኛው መረዳት ስለድነት ከሌላህ ስለጥምቀት በትክክል መረዳት ስለማይኖር ነው

ሐዋርያው ጳውሎስ ድነት በእምነት ብቻ አይደለም ሕግንም በመጠቀም ጭምር ድነት እምነት + ሕግ መጠበቅ(መልካም ሥራ) ለሚሉ ለቀላቀሉ የገላትያ ሰዎች በደንብ ነው የነገራቸው ያ መልዕክት አሁንም ለሚቀላቅሉ ሰዎች ይሰራል

ገላ 3 1-5 "የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው? ይህን ብቻ ከእናንተ እንድማር እወዳለሁ፤ በሕግ ሥራ ወይም ከእምነት ጋር በሆነ መስማት መንፈስን ተቀበላችሁን? እንዲህን የማታስተውሉ ናችሁ? በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋ ትፈጽማላችሁን? በውኑ ከንቱ እንደ ሆነስ እንደዚህ ያለ መከራ በከንቱ ተቀበላችሁን? እንግዲህ መንፈስን የሚሰጣችሁ በእናንተም ዘንድ ተአምራት የሚያደርግ፥ በሕግ ሥራ ነውን ወይስ ከእምነት ጋር በሆነ መስማት ነው?"

እያለ ጳውሎስ የገላትያ ሰዎችን እምነትን ከሕግ መጠበቅ (መልካም ሥራ) ጋር መቀላቀላቸውን በማዘን ይናገራቸዋል ሲቀጥልም...

23-26 "እምነትም ሳይመጣ ሊገለጥ ላለው እምነት ተዘግተን ከሕግ በታች እንጠበቅ ነበር። እንደዚህ በእምነት እንጸድቅ ዘንድ ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን ሆኖአል፤ እምነት ግን መጥቶአልና ከእንግዲህ ወዲህ ከሞግዚት በታች አይደለንም። በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤"

ሙሉውን እንድታነብ አንተን እጋብዝሃለሁ

ከእዚህ ከጠቅላላው የገላትያ ሃሳብ እንደምንረዳው ሰው የሚድነው በእምነት ነው እንጂ እምነትንና ሕግን መጠበቅ (መልካም ሥራ) በመቀላቀል አይደለም መልካም ሥራ ከአንድ በእውነት አምኖ ከዳነ ሰው የሚጠበቅ ፍሬ ነው

ስለዚህ በእምነት ድነትን ከሥራ ጋር እንዲሁም በእምነት ድነትን ስርዐት ከመጠበቅ ጋር የምንቀላቅለው ከሆነ በጣም ተሳስተናል መልካም ሥራም ሆነ ስርአትን መጠበቅ ከአንድ በእምነት ከዳነ ሰው የሚጠበቅ እንጂ ለድነት ብሎ የሚጥረው አይደለም

ይህ በደንብ ከገባን ለድነት ብለን እንጠመቃለን አንልም 
ይህ በደንብ ከገባን ጥምቀት የሚል ባየን ቁጥር የውሃ ጥምቀት ብቻ ወደአእምሮአችን አይመጣም አንድ ማስረጃ እዚህ ጋር ልስጥ...
ድነትን ከውሃ ጥምቀት ጋር የሚያያዙ ሰዎች ይህንን ይጠቅሳሉ እንደማስረጃ

ገላትያን 3:27 ይጠቅሳሉ:: እስቲ አብረን እንየው...

"ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።"

በመጀመርያ ይኼን ወደመተርጎም ከመግባታችን በፊት ከእዚህ ጥቅስ በፊት ያለውን ቁጥር 26 እንየው...

"በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤" ይላል 

ስለዚህ ቁጥር 27 ላይ ጥምቀት የሚለውን ከመናገሩ በፊት በእምነት በኩል የእግዝአብሔር ልጆች ሆነዋል:: ያመነ እና የእግዝአብሔር ልጅ የሆነ ደግሞ የጥምቀትን ሥርአት ይፈፅማል:: ስለዚህ እዚህ ቦታ የተጠቀሰው ጥምቀት ለድነት አስፈላጊ ስለመሆኑ አይናገርም::

ይበልጥ ደግሞ እንየው እስቲ...

እዚህ ቦታ ላይ የሚናገረው "ጥምቀት" የውሃ ጥምቀት መሆኑን በምን እርግጠኞች እንሆናለን?? አንዳንድ ሰዎች "አንዲት ጥምቀት" እያለ የእግዝአብሔር ቃል ስለሚናገር: ይህ እዚህ ቦታ ላይ የተጠቀሰው "ጥምቀት" ውሃን ባይጠቅስም የውሃ ጥምቀት ነው ልትሉ ትችላላችሁ:: ትክክል ናችሁ: "የውሃ ጥምቀት" አንድ ብቻ ነው:: ነገር ግን "ጥምቀት" መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰው የውሃ ጥምቀት ብቻ አይደለም:: እስቲ ይኼን ጥቅስ እንየው...

ዕብ 6:1-2 "ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤ መሠረትን ደግመን አንመሥርት፥ እርሱም ከሞተ ሥራ ንስሐና በእግዚአብሔር እምነት፥#ስለ_ጥምቀቶችና እጆችንም ስለ መጫን ስለ ሙታንም ትንሣኤ ስለ ዘላለም ፍርድም ትምህርት ነው።"

እዚህ ቃል ላይ የሚናገረው ስለ አንድ ጥምቀት ሳይሆን ከአንድ በላይ ስለሆኑ ጥምቀቶች ነው:: ስለዚህ ጥምቀት የሚል ባየን ቁጥር የውሃ ጥምቀት ነው ካልን: ወደስህተት መረዳት ነው የምንገባው::

አሁን የገላ 3:27 "ጥምቀት" ምን ማለት እንደሆነ ለማስረዳት ሌላ አንድ ጥቅስ ልጨምር...

1ቆሮ 12:12-13 "አካልም አንድ እንደ ሆነ ብዙም ብልቶች እንዳሉበት ነገር ግን የአካል ብልቶች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ፥ ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው፤ አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን#በአንድ_መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን #ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።"

እዚህ ጥቅስ ላይ ስለመጠመቅ ይነግረናል:: የምንጠመቀው ደግሞ በውሃ ሳይሆን #በመንፈስእንደሆነ ይነግረናል:: ስለዚህ ከክርስቶስ ጋር አንድ አካል እንድንሆን ወይም ክርስቶስን እንድንለብሰው የተጠመቅነው በውሃ ሳይሆን በመንፈስ (መንፈስ ቅዱስ) ነው::

ይህ በደንብ ከገባን በገላ 3:27 "ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።" የሚለው የተጠቀሰው ጥምቀት: የውሃ ጥምቀት ሳይሆን ስናምን የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ ስለምንሆን በመንፈስ ቅዱስ የሚሆንልንን የሚያሳይ ጥምቀት እንደሆነ በቀላሉ እንረዳለን::

ደግሞ የእግዝአብሔር ልጆች መሆናችን የሚመሰክርልንም ሆነ የምንታተምበት በመንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ በውሃ ጥምቀት አይደለም::

ኤፌ 1:13-14 " እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤ እርሱም የርስታችን መያዣ ነው፥ ለእግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እስኪዋጅ ድረስ፥ ይህም ለክብሩ ምስጋና ይሆናል።"

ሮሜ 8:16 "የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።"

ስለዚህ ጥምቀት ባየን ቁጥር ወደአእምሮአችን የውሃ ጥምቀት ብቻ መምጣት የለበትም

ሰዎች መንፈሳዊ መንፃት የሚያገኙት እንዴት ነው??

 
ሰዎች መንፈሳዊ መንፃት የሚያገኙት እንዴት ነው??

በሥጋዊው አለም መንፃት የሚካሄደው በውሃ በመታጠብ ነው:: ስለዚህ አንድ ሰው ለመንፃት በውሃ መታጠብ አለበት:: እንግዲህ የመንፈሳዊውም ነገር ለመግለፅ ሁልጊዜ የምንጠቀመው በሥጋዊ አለም በምንጠቀምበት መረዳት ስለሆነ: እንዲሁ እንደነፃን ለመናገር በመንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል: እንዲሁም በቃሉ አማካኝነት በውኃ ታጥባችሁዋል: ነጽታችሁል  የሚል ፅሁፍ ወይም አገላለፅ እናነባለን::

ስለዚህ ውሃ የሚል ባየን ቁጥር የውሃ ጥምቀት የሚል ነገር ሁልጊዜ የሚታሰበን ከሆነ
በውሃ ታጥባችሁዋል የሚል ባየን ቁጥር የውሃ ጥምቀት የሚታሰበን ከሆነ

ወደስህተት መረዳት እንገባለን::

አንድ ሰው ዳግም ከመወለዱ አስቀድሞ በቃሉ መንጻት አለበት:: በመንፈሳዊ አነጋገር በቃሉ መንፃት ማለት በሃጥያአት ምክንያት የጨቀየው ሕይወቱ ከቃሉ የተነሳ መንጻት ይቅር መባል ማለት ነው::

ይኽ የሚሆነው አንዴት ነው??

ይኽ የሚሆነው መጀመርያ አንድ ሰው የእግዝአብሔርን ቃል መስማት አለበት: የእግዝአብሔር ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ለሃጥያአትህ ሞቶልሃል ዋጋ ከፍሎልሃል:: ስለዚህ ከአንተ የሚጠበቀው ይህን ፀጋ በእምነት እንድትቀበል ነው:: ንስሃ እንድትገባ ነው:: የሚለውን መልዕክት ሰምቶ ሲቀበል እና በልቡ ሲያምን ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወቱ ጌታ አድርጎ ሲቀበል ያኔ መንፈሳዊ መንፃት: የሃጥያአት ይቅርታ ማግኘት ወይም በሥጋዊ አገላለፅ በውሃ መታጠብ ይሆንለታል:: ልብ ማለት ያለብን በአዲስ ኪዳን ነገሮች መንፈሳዊ ናቸው:: ለምሳሌ የልብ መገረዝ ነው እንጂ ከእኛ የሚጠበቀው የሥጋ መገረዝ አይደለም:: እንዲሁም ለእግዝአብሔር ስግደት በመንፈስና በእውነት እንጂ በሥጋ ጉልበታችን መሬት ላይ መንበርከክ አይደለም: ወዘተ... ስለዚህ ልክ እንደብሉይ ኪዳን ጊዜ በውሃ በመታጠብ መንፃት ሳይሆን መንፈሳዊ መንፃት ነው ከእኛ የሚጠበቀው::

 1 ቆሮ 6:9-11 አብረን እንየው... "ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።"

እዚህ ጋር በግልፅ እንደምናየው በተለያዩ ሃጥያአቶች የቆሸሹ ዓመፆኞችን ከጠራ በሁዋላ እነዚህ የቆሸሹ ዓመፆኞች የእግዝአብሔርን መንግሥት አይወርሱም ብሎ ይነግረናል:: ከእዛም የዳኑትን እናንተም እንደነዚህ ነበራችሁ ይላል:: አሁን ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል ይላል። ይህ ማለት የቆሸሹት ዓመፆች አሁን ነጽተዋል:: ስለዚህ ወደ እግዝአብሔር መንግሥት መግባት ይችላሉ:: ይህ እንግዲህ ከቃሉ የተነሳ የሚደረግ መንፈሳዊ መንፃት እንጂ: ስለውሃ ጥምቀት የሚናገር አይደለም:: ምክንያቱም የሃጥያአት መንፃት የሚገኘው በኢየሱስ ደም ብቻ ነውና::

 ኤፌ 5:25-26 "ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ That he might sanctify and cleanse it with the washing of water by the word,"

እዚህም ጋር በውሃ መታጠብን በመግለጫነት ቢጠቀምም: የውሃ መታጠቡ ግን በቁሳዊ ውሃ መታጠብ ሳይሆን: ከቃሉ የተነሳ ስለሚሆንል መታጠብ ወይም መንፈሳዊ መንፃት የሚናገር ነው:: ምንም ስለጥምቀት የሚናገር አይደለም:: ሁላችንም እንደምናውቀው ጥምቀት የውሃ መታጠብ ሳይሆን ከክርስቶስ ጋር ተቀብረን ከትንሣኤው ጋር መነሳታችንን ከእሱ ጋር መተባበራችንን ለአለም የምናውጅበት ነው::

ዮሐ 15:3 "እናንተ ስለ ነገርኋችሁ ቃል አሁን ንጹሐን ናችሁ፤"

እዚህ ጥቅስ ላይ ስለመንፃት ይናገራል በግልፅ እንደሚናገረው የነፁት በቃሉ ነው

 እዚህ ድረስ ከተግባባን ወደዮሐ 3:5 "ውሃና መንፈስ" የሚለውን ለማስረዳት ልሞክር...

መጀመርያ ዳግም መወለድ ወይም ድነት የሚገኘው እንዴት እንደሆነ ከአጠቃላይ የአዲስ ኪዳን ትምህርት የምንረዳው በእምነት ነው:: አንዳንዶች መልካም ሥራስ ማለታችሁ አይቀርም:: እንደእግዝአብሔር ቃል ከሆነ ግን መልካም ሥራ የድነት ውጤት እንጂ ለመዳን ብለን የምንጥረው አይደለም:: እዚህ ጋር አንድ ሰው ካመነ በሁዋላ እንደፈለገ ሃጥያአት እየሰራ መኖር ይችላል እያልኩ አይደለም:: የእውነተኛ እምነት ፍሬ መልካም ሥራ ብቻ ነው:: ስለዚህ አንድ ሰው እውነተኛ ድነት ወይም እምነት እንዳመነ የሚታወቀው በፍሬው ወይም በመልካም ሥራው ነው::

በጌታ እንድንፈፅማቸው የታዘዝነው ስርአቶች አሉ:: ለምሳሌ ጥምቀት: የጌታ እራት: የመሳሰሉት:: እነዚህ ነገሮች አንድ አምኖ የዳነ ሰው የሚፈፅማቸው ስርአቶች ናቸው::

እንግዲህ ጥምቀት አንድ ሰው አምኖ ከዳነ ወይም ዳግም ከተወለደ በሁዋላ የሚፈፅመው ስርአት ከሆነ: በዮሐ 3:5 ላይ "ውሃ" የሚል ቃል ስለተገለፀ: የሚያሳየው የውሃ ጥምቀት ነው ማለት: ወደተሳሳተ መረዳት ነው የሚወስደን:: ሌላ ቦታ ላይ ስለመወለድ የተገለፀበት ቦታ አለ:: እሱን ማየት ይበልጥ ዮሐ 3:5 እንድንረዳው ይረዳናል እስቲ እንየው...
1 ጴጥ 1:23 "ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።"

እዚህ የጴጥሮስ መልእክት ላይ ስለዳግም መወለድ ሲናገር የተወለድነው በእግዝአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር እንደሆነ ይነግረናል እንጂ ስለጥምቀት በጭራሽ አይናገርም::

ያዕ 1:18"ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።"

እዚህም በያዕቆብ መልእክት ላይ የተወለድነው በእውነት ቃል እንጂ በፍፁም ስለጥምቀት አይናገርም::
ቲቶ 3:5 "እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤"

እዚህም ጋር ስለአዲስ ልደት ወይም ስለዳግም ልደት ይናገራል:: በእዚህም አዲስ ልደት ለማግኘት ከእኛ ምንም አይነት ሥራ እንደማይጠበቅ ነው የሚነግረን:: ከላይ እንዳየነው መንፈሳዊ መንፃት በሥጋዊ አገላለጽ ሲነገር ወይም ሲገለፅ በውሃ መታጠብን ስለሚጠቀም: እዚህም ጋር በውሃ መታጠብ የሚገልፀው መንፈሳዊ መንፃትን ነው:: መንፈሳዊ መንፃትን የምናገኘው ደግሞ በቃሉ ነው:: ቃሉም የሚነግረን ከምህረቱ የተነሣ የተሰጠንን ፀጋ ነው:: ፀጋው ደግሞ እኛ ሃጥያአተኞች የነበረን ሞት የሚገባን: ኢየሱስ ለእኛ ሲል ሞተልን ደሙን አፈሰሰልን:: የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከሃጥያአት ሁሉ ያነፃል ነው:: ስለዚህ በእዚህም መሠረት ቃሉን አምነን ንስሃ ስንገባ መንፈሳዊ መንፃት ወይም የሃጥያአት ይቅርታ እናገኛለን:: ከእዛም በመንፈስ ቅዱስ እንወለዳለን::

እዚህም ቦታ ምንም ስለውሃ ጥምቀት የሚናገር ነገር የለም::

መንፈሳዊ መንፃት በትክክል ከገባን ውሃ ባየን ቁጥር ወይም መታጠብ የሚል ባየን ቁጥር የውሃ ጥምቀት ነው እያልን ወደተሳሳተ መረዳት አንገባም
እንግዲህ እስካሁን ከላይ የተናገርኩት ስለመንፈሳዊ መንጻት (የሃጥያአት ይቅርታ) በሥጋዊ አነጋገር ወይም አገላለፅ መታጠብ ወይም በውሃ መታጠብ ከገባን: በዮሐ 3:5 ላይ የተገለፀው "ውሃ" የሚያሳየን ከቃሉ የተነሳ በደሙ ስለሚሆንልን መንፈሳዊ መንፃት ነው::

ከአጠቃላይ የመፅሐፍ ቅዱስ አዲስ ኪዳን ሐሳብ ስንነሳ: ድነት የሚገኘው በሥራ አይደለም:: ወይም ስርዐትን በመፈፀም አይደለም:: ስለዚህ በዮሐ 3:5 ላይ ስለዳግም መወለድ ወይም ስለድነት የሚናገረው ላይ "ውሃ" የሚገልፀው ጥምቀትን ነው ካልን: ጥምቀት ያድናል ወደሚል በጣም ወደተሳሳተ መረዳት ውስጥ እንገባለን:: የኢየሱስን ደም ወደማቃለል የእግዝአብሔርን ፀጋ ወደመናቅ እንገባለን:: ነገር ግን ድነት በእምነት ብቻ ነው: መልካም ሥራም ቢሆን ስርአት መፈፀም: የድነታችን ውጤት ነው:: ብለን ልክ እንደቃሉ ካመንንን ግን: በዮሐ 3:5 ላይ ያለውን "ውሃ" የሚለውን ቃል ጥምቀት ነው ብለን አንረዳውም ምክንያቱም ከቃሉ ጋር እንስማማለን እንጂ አንጋጭም::
ጥምቀት ወይም ሥራ ለድነት እንደማያስፈል ከላይ ተናግርያለሁ:: እሱም የሚደግፍ ግልፅ የሆነ የእግዝአብሔር ቃል ጠቅሻለሁ::

ኤፌ 2:8-9 "ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።"

የሚለውን: ስለዚህ አካራካሪ የሆኑ ቦታዎችን ስንተረጉም: እዚህ በኤፌሶን መልዕክት የተነገረውን ግልፅ ጥቅስ ተደግፈን: አከራካሪዎቹን ለመተርጎም እንሄዳለን እንጂ: ከእግዝአብሔር ቃል ጋር በሚጋጭ ሁኔታ አንተረጉምም::

በእዚህም መረዳት ጥምቀት ለድነት ያስፈልጋል የሚሉ ሰዎች ገላትያን 3:27 ይጠቅሳሉ:: እስቲ አብረን እንየው...

"ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።"

በመጀመርያ ይኼን ወደመተርጎም ከመግባታችን በፊት ከእዚህ ጥቅስ በፊት ያለውን ቁጥር 26 እንየው...

"በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤" ይላል

ስለዚህ ቁጥር 27 ላይ ጥምቀት የሚለውን ከመናገሩ በፊት በእምነት በኩል የእግዝአብሔር ልጆች ሆነዋል:: ያመነ እና የእግዝአብሔር ልጅ የሆነ ደግሞ የጥምቀትን ሥርአት ይፈፅማል:: ስለዚህ እዚህ ቦታ የተጠቀሰው ጥምቀት ለድነት አስፈላጊ ስለመሆኑ አይናገርም::

ይበልጥ ደግሞ እንየው እስቲ...

እዚህ ቦታ ላይ የሚናገረው "ጥምቀት" የውሃ ጥምቀት መሆኑን በምን እርግጠኞች እንሆናለን?? አንዳንድ ሰዎች "አንዲት ጥምቀት" እያለ የእግዝአብሔር ቃል ስለሚናገር: ይህ እዚህ ቦታ ላይ የተጠቀሰው "ጥምቀት" ውሃን ባይጠቅስም የውሃ ጥምቀት ነው ልትሉ ትችላላችሁ:: ትክክል ናችሁ: "የውሃ ጥምቀት" አንድ ብቻ ነው:: ነገር ግን "ጥምቀት" መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰው የውሃ ጥምቀት ብቻ አይደለም:: እስቲ ይኼን ጥቅስ እንየው...

ዕብ 6:1-2 "ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤ መሠረትን ደግመን አንመሥርት፥ እርሱም ከሞተ ሥራ ንስሐና በእግዚአብሔር እምነት፥ #ስለ_ጥምቀቶችና እጆችንም ስለ መጫን ስለ ሙታንም ትንሣኤ ስለ ዘላለም ፍርድም ትምህርት ነው።"

እዚህ ቃል ላይ የሚናገረው ስለ አንድ ጥምቀት ሳይሆን ከአንድ በላይ ስለሆኑ ጥምቀቶች ነው:: ስለዚህ ጥምቀት የሚል ባየን ቁጥር የውሃ ጥምቀት ነው ካልን: ወደስህተት መረዳት ነው የምንገባው::

አሁን የገላ 3:27 "ጥምቀት" ምን ማለት እንደሆነ ለማስረዳት ሌላ አንድ ጥቅስ ልጨምር...

1ቆሮ 12:12-13 "አካልም አንድ እንደ ሆነ ብዙም ብልቶች እንዳሉበት ነገር ግን የአካል ብልቶች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ፥ ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው፤ አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን #በአንድ_መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን #ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።"

እዚህ ጥቅስ ላይ ስለመጠመቅ ይነግረናል:: የምንጠመቀው ደግሞ በውሃ ሳይሆን #በመንፈስ እንደሆነ ይነግረናል:: ስለዚህ ከክርስቶስ ጋር አንድ አካል እንድንሆን ወይም ክርስቶስን እንድንለብሰው የተጠመቅነው በውሃ ሳይሆን በመንፈስ (መንፈስ ቅዱስ) ነው::

ይህ በደንብ ከገባን በገላ 3:27 "ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።" የሚለው የተጠቀሰው ጥምቀት: የውሃ ጥምቀት ሳይሆን ስናምን የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ ስለምንሆን በመንፈስ ቅዱስ የሚሆንልንን የሚያሳይ ጥምቀት እንደሆነ በቀላሉ እንረዳለን::

ደግሞ የእግዝአብሔር ልጆች መሆናችን የሚመሰክርልንም ሆነ የምንታተምበት በመንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ በውሃ ጥምቀት አይደለም::

ኤፌ 1:13-14 " እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤ እርሱም የርስታችን መያዣ ነው፥ ለእግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እስኪዋጅ ድረስ፥ ይህም ለክብሩ ምስጋና ይሆናል።"

ሮሜ 8:16 "የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።"

ይኼን ሃሳቤን ለማጠቃለል...

ውሃ ባየን ቁጥር የውሃ ጥምቀት ነው የምንል ከሆነ
ጥምቀት የሚል ባየን ቁጥር የውሃ ጥምቀት ብቻ የሚታየን ከሆነ

አሁንም ወደተሳሳተ መረዳት መግባታችን ነው:: ስለዚህ የተፃፈውን ስንረዳ: ከአጠቃላይ የእግዝአብሔር ሃሳብ መሠረት ከቃሉ ጋር ሳንጋጭ ለመረዳት እንሞክር::