Saturday, June 30, 2012

የሕይወት ትርጉም ምንድ ነው?

በሕይወቴ ውስጥ ምን ባደርግ ነው ዓላማ፣ ስኬትና እርካታ የማገኘው። ዘላቂ ውጤት ያለው ሥራ ለማከናወን አቅሙ ይኖረኝ ይሆን? ብዙ ሰዎች ስለዚህ ጉዳይ ጥያቄ ማንሳታቸው አይቀርም። በሕይወታቸው ለማሳካት ያሰቡትን ጉዳይ ቢፈፅሙም ከአመታት በኋላ መለስ ብለው ከሰዎች ጋር የነበራቸው ግንኙነት እንዴት እንደተበላሸና ባዶነት ለምን እንደሚሰማቸው ሳይገርማቸው አይቀርም። አንድ  ተጫዋች በዘርፉ ከፍተኛ ዝና ከተቀዳጀ በኋላ ጨዋታ ሲጀምር ሰዎች ምን ብለው ቢነግሩት ይመርጥ እንደነበር ቢጠይቁት “ከፍተኛ ደረጃ ከተደረሰ በኋላ ምንም እንደሌለ ቢነግሩኝ እመርጥ ነበር” ሲል በቁጭት ተናግሯል።

ብዙ ግቦች ባዶነታቸው የሚረጋገጠው እነሱን ለማከናወን በርካታ ዓመታት ካለፈ በኋላ ነው። በኛ ሰብዓዊ ሕብረተሰብ ትርጉም እናገኛለን ብለው በማሰብ ብዙ ሰዎች በርካታ ዓላማዎችን ያራምዳሉ። ከነዚህም የሕይወት ዓላማዎች የንግድ ስኬት፣ ሐብት፣ መልካም ግንኙነት፣ ወሲብ፣ መዝናናትና ለሌሎች ሰዎች ጥሩ ነገር መስራትን ያካትታሉ። ሰዎች ሲመሰክሩ እንደተስተዋለው ሐብት የማከማቸት፣ መልካም ግንኙነት የመመስረትና ደስታን የማግኘት ዓላማቸውን ቢያሳኩም ማንም ሊሞላው የማይችል ባዶነት እንደሚሰማቸው ተናግረዋል።

የመፅሐፈ መክብብ ፀሐፊ ይህንን ስሜት ለመግለፅ “ከንቱ!...የከንቱ ከንቱ! ሁሉ ከንቱ ነው” ይላል(መፅሐፈ መክብብ 1፡2)። የመፅሐፈ መክብብ ፀሐፊ የሆነው ንጉሥ ሰለሞን ከልክ በላይ የሆነ ሐብት፣ በእርሱ ዘመንና በኛ ጊዜ ከነበረ ማንም ሰው የሚበልጥ ጥበብ፣ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ዕቁባቶች፣ መንግስታት የሚቀኑበት ቤተመንግስትና የአትክልት ስፍራ፣ ምርጥ የሆነ ምግብ፣ ወይንጠጅና አለየተባለ መደሰቻና መዝናኛ ነበረው። ጠቢቡ አንድ ጊዜ ሲናገር ልቡ የተመኘውን ያሳድድ ነበር። በዓይኖቻችን የምናየውና በስሜቶቻችን የምናጣጥመው ኑሮ ብለን የምንኖረው “ከፀሐይ በታች ያለው ሕይወት” ከንቱ ነው ሲል አጣጥሎታል።

ይህ ባዶነት ለምን ተከሰተ? ምክንያቱም እግዚሐብሔር የፈጠረን የዚህና አሁን ከምንለማመደው ባሻገር ላለው ነገር ነው። ሠለሞን ስለእግዚሐብሔር ሲናገር “ሰው መርምሮ እንዳያገኝ ዘላለምነትን በልቡ ሰጠው” ብሏል። (መፅሐፈ መክብብ 3፡11)። ሁላችንም በልባችን እንደምናውቀው ያለው ነገር “እዚህና አሁን” ያለው ብቻ እንዳልሆነ እንገነዘባለን። የመፅሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ መፅሐፍ በሆነው በዘፍጥረት ውስጥ እግዚሐብሔር የሰው ልጅን በራሱ መልክ እንደሰራው እናነባለን። (ዘፍጥረት 1፡26)። እኛ ከሌላ ነገር (ከሌላ የሕይወት ቅርፅ) ይልቅ አፈጣጠራችን ወደ እግዚሐብሔር የቀረበ እንደሆነ የሚያሳየን ነው። ከዚህም በተጨማሪ የምናገኘው ነገር የሰው ልጅ በኃጢት ወድቆ የኃጢያት መርገም በምድር ላይ ከመምጣቱ በፊት የሚከተሉት ነገሮች ተግባራዊ ሆነዋል። 



(1) እግዚሐብሔር ሰውን ማህበራዊ ፍጡር አድርጎ አበጀው።(ዘፍጥረት 2፡ 18-25)፣ 
(2) እግዚሐብሔር ለሰው ልጅ ሥራ ሰጠው። (ዘፍጥረት 2፡ 15)፣ 
(3)እግዚሐብሔር ከሰው ጋር ህብረት ነበረው። (ዘፍጥረት 3፡ 8) እና 
(4) ሰው ምድርን እንዲገዛ እግዚሐብሔር ሥልጣን ሰጠው። (ዘፍጥረት 1፡ 26)። 


የእነዚህ ነገሮች ትርጉም ምንድ ነው? እነዚህ እያንዳንዱ ለሕይወታችን እርካታ እንዲያስገኙልን ነው። እግዚሐብሔር አቅዶ የነበረው፣ ነገር ግን እነዚህ ሁሉ (በተለይም ሰው ከእግዚሐብሔር ጋር ያለው ህብረት) ተለዋውጠዋል። ምክንያቱም የሰው ልጅ በኃጢያት ከወደቀ በኋላ እርግማን በምድር ላይ ተግባራዊ በመሆኑ ነው። (ዘፍጥረት 3)።

የመፅሐፍ ቅዱስ የመጨረሻ ክፍል በሆነው በራዕይ መፅሐፍ እግዚሐብሔር አንድ ነገር አስቀምጧል። አሁን በተጨማጭ የምናውቃቸውን ምድርና ሰማይን አስወግዶ አዲስ ምድርና ሰማይን በመፍጠር ዘላለማዊ ሕይወትን ይተካል። በዚያን ጊዜ ከዳነው የሰው ልጅ ጋር ሙሉ ህብረት ያደርጋል። ያልዳኑትን ይፈርድባቸውና እርባናየለሽ ተብለው ወደ እሳትባህር ይጣላሉ። (ራዕይ 20፡ 11-15)። የኃጢያት መርገም ይወገዳል። ከዚህ በኋላ ኃጢያት፣ ሐዘን፣ በሽታ፣ ሞትና ስቃይ ከቶ አይኖርም።( ራዕይ 21፡ 4)። አማኞችም ሁሉን ነገር ይወርሳሉ፣ እግዚሐብሔር ከእነርሱ ጋር ይኖራል፣ እነሱም ልጆች ይሆኑታል። (ራዕይ 21፡ 7) ።

ስለዚህ ወደ ሙሉ ክብ መጣን ማለት ነው። እግዚሐብሔር ከእርሱ ጋር ህብረት እንድናደርግ ፈጠረን። የሰው ልጅ ኃጢያት በመስራቱ ህብረቱ እንዲቋረጥ አደረገ። እግዚሐብሔር ከመረጣቸው ጋር ህብረቱን እንደገና በማደስ በላይኛው ቤት ከእርሱ ጋር እንዲኖሩ ያደርጋል። በሕይወት ዑደት ውስጥ ብዙ ነገር ካሳኩ በኋላ ለዘላለሙ ከእግዚሐብሔር ጋር መለያየት ከውድቀት ሁሉ የከፋው ነው። ነገር ግን እግዚሐብሔር ዘላለማዊ ደስታ ዕውን የሚሆንበትን መንገድ ከመቀየሱም ባሻገር(ሉቃስ 23፡ 43) በምድርም ላይ ሕይወት አርኪና ትርጉም ያለው እንዲሆን ሁኔታዎችን አመቻችቶአል። እንዴት ነው ይህ ዘላለማዊ ደስታና “ገነት በምድር” የሚገኘው?

በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የታደሰው የሕይወት ትርጉም

አሁን በምድርና በሚቀጥለው ሕይወት በሰማይ የሕይወት እውነተኛ ትርጉም የሚገኘው ከእግዚሐብሔር ጋር ተቋርጦ የነበረው ግንኙነት እንደገና ሲታደስ ነው። ይህ ግንኙነት አዳምና ሔዋን በኃጢያት በመውደቃቸው ምክንያት ተቋርጦ ነበር። ዛሬ ያ ግንኙነት እውን የሆነው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው። (የሐዋሪያት ሥራ 4፡ 12፣ ዮሐንስ 14፡ 6፣ ዮሐንስ 1፡ 12)። የዘላለም ሕይወት የሚገኘው እርሱ/እርሷ ኃጢያታቸውን ተናዘው ሲፀፀቱ (በኃጢያታቸው ሥራ ላለመቀጠልና ክርስቶስ ለውጦ አዲሰ ሰው እንዲያደርጋቸው ሲፈልጉ ነው) እና ኢየሱስ ክርስቶስ እንደአዳኛቸው ተቀብለው ሲደገፉበት ነው። (በዚህ ጠቃሚ ጉዳይ የበለጠ ማብራሪያ ለማግኘት “የድነት ዕቅድ ምንድ ነው?” የሚለውን ጥያቄ ተመልከት)።

በሕይወት እውነተኛ ትርጉም የሚገኘው ኢየሱስን እንደየግል አዳኝ ብቻ በመቀበል አይደለም (ይህ በራሱ ድንቅ ቢሆንም) ይልቁንም የሕይወት እውነተኛ ትርጉም የሚገኘው አንድ ሰው እንደ ደቀመዝሙር ሲከተለውና ከእርሱ በመማር ቃሉ ከሆነው መፅሐፍ ቅዱስ ጋር ጊዜ ሲያሳልፍና በተጨማሪም በፀሎት ሕብረት ሲኖረውና ትዕዛዙን በማክበር እርምጃውን ከርሱ ጋር ሲያደርግ ነው። ምናልባት አንተ ያላመንክ ብትሆን (ወይም ምናልባት አዲስ አማኝ ከሆንክ) “በጣም የሚያጓጓ ወይም ለኔ ነገሩ አርኪ አይደለም” ልትል ትችላለህ። ነገር ግን እባክህን ንባብህን ለጥቂት ጊዜ ቀጥል። ኢየሱስ የሚከተሉትን ሐሳቦች ሰንዝሯል። “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፣ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፣ ከእኔም ተማሩ፣ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝና፣ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፣ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና” (ማቴዎስ 11፡ 28-30)። “እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ” (ዮሐንስ 10፡ 10)። “እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፣ ራሱን ይካድ፣ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፣ ስለእኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል።(ማቴዎስ 16፡ 24- 25)። በእግዚሐብሔር ደስ ይበልህ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።(መዝሙር 37፡ 4)። 

እነዚህ ሁሉ ጥቅሶች የሚያብራሩት ምርጫ እንዳለን ነው። የራሳችንን ኑሮ ልንመራ እንችላለን፣ ውጤቱ ግን ባዶ ሕይወት ነው። ወይም በሙሉ ልብ እግዚሐብሔርን በመከተል ለሕይወታችን ያለውን ዓላማ በመሻት እርካታና ስኬት ማግኘት ነው። ይህም የሚሆነው ፈጣሪያችን ስለሚወደንና መልካም የሆነውን ሁሉ ለእኛ ስለሚመኝልን ነው።(ቀላል ሕይወት ላይሆን ይችላል፤ ግን አርኪ ነው።) 

 ጨዋታ ም  ለመከታተል ወደ እስታዲየም ብትሄድ ጥቂት  ከፈልክ ራቅ ያለ መቀመጫ ይሰጥሃል። በርካታ ሮች ከከፈልክ ግን ጨዋታውን ቀረብ ብለህ እንድታይ ጥሩ እይታ ያለው መቀመጫ ታገኛለህ። በክርስትና ሕይወትም እንዲሁ ነው። እግዚሐብሔር ተዓምር ሲሠራ ማየት ከተፈለገ እሁድ ብቻ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚሄዱ ሰዎች አይሆንም። ዋጋውን አልከፈሉማ። እግዚሐብሔር ተዓምር ሲሰራ የሚያዩት ከልባቸው የክርስቶስ ደቀመዝሙር በመሆን የራሳቸውን ሃሳብ ማሳደድ ትተው የእግዚሐብሔርን ዓላማ የሚያራምዱ ናቸው። ዋጋ ከፍለዋል(ለክርስቶስና ለቃዱ ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ሰጥተዋል)። ሕይወትን በደንብ ከማጣጣማቸውም በላይ ያለአንዳች ፀፀት በፈጣሪያቸው ፊት ሊቀርቡ ይችላሉ። በራሳቸው አያፍሩም። በሌላ ሰው ፊት ሲቀርቡም አይሸማቀቁም። አንተስ ይህንን ለመፈፀም ፈቃደኛ ነህን? እንዲህ ከሆነ ሕይወቴ ትርጉምና ዓላማ የለውም የሚል ቁጭት አያድርብህም።

Friday, June 29, 2012

ክርስቲያኖች የብሉይ ኪዳንን ህግ መታዘዝ ይኖርባቸዋል?

ክርስቲያኖች የብሉይ ኪዳንን ህግ መታዘዝ ይኖርባቸዋል?
ይህንን የመረዳቱ አቢይ ጉዳይ የብሉይ ኪዳን ህግ የተሰጠው ለክርስቲያኖች ሳይሆን ለእስራኤል ነገድ እንደሆነ ያን ማወቁ ነው፡፡ የተወሰኑቱ ህጎች እስራኤላውያን እንዴት መታዘዝ እና እግዚአብሔርን ማስደሰት እንዳለባቸው ለእነርሱ ለመግለጥ ነበር (ለምሳሌ አሥርቱ ትዕዛዛት)፡፡ ከህጎቹ የተወሰኑቱ እስራኤላውያን እንዴት እግዚአብሔርን እንደሚያመልኩ እና ከኃጥአት እንደሚነጹ ለማሳየት ነበር(የመስዋዕት ሥርዓት)፡፡ የተወሰኑቱ ህጎች እስራኤላውያንን ከሌሎች ነገዶች የተለዩ ለማድረግ የታሰቡ ነበሩ (የምግብ እና የአለባበስ ህግጋት)፡፡ ዛሬ አንዳች የብሉይ ኪዳን ህግ በእኛ ላይ የጸና አይደለም፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሞተበት ጊዜ ለብሉይ ኪዳን ህግ ፍጻሜን አደረገ (ወደ ሮሜ ሰዎች 10፤4፤ወደ ገላቲያ ሰዎች 3፤23-25፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፤15)

በብሉይ ኪዳን ህግ ምትክ እኛ በክርስቶስ ህግ ሥር ነን (ወደ ገላቲያ ሰዎች 6፤2) ያም “ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም መውደድ እና ባልንጀራህን እንደ ራስህ መውደድ የምለው ነው” (የማቴዎስ ወንጌል 22፤37-38)፡፡ እነዚያን ሁለቱን ትዕዛዛት ብንታዘዝ ክርስቶስ ከእኛ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ እየፈጸምን ነው ማለት ነው፤ “በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።” (የማቴዎስ ወንጌል 22፤40)፡፡ አሁን ዛሬ የብሉይ ኪዳን ህግ አላስፈላጊ ነው ማለት አይደለም፡፡ ብዙዎቹ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ ትዕዛዛት “እግዚአብሔርን መውደድ” እና “ባልንጀራህን መውደድ” በሚሉት ክፍሎች ውስጥ ይመደባል፡፡ የብሉይ ኪዳን ህግ እንዴት እግዚአብሔርን መውደድ እና ባልንጀራህን መውደዱ ምን እንደሆነ ለማወቅ ጥሩ መመሪያ ሊሆን ይችላል፡፡ በተመሳሳይም የብሉይ ኪዳን ህግ ለዛሬ ዘመን ክርስቲያኖች ይሠራል ማለት ስህተት ነው፡፡ የብሉይ ኪዳን ህግ መለኪያ ነው (የያዕቆብ መልዕክት 2፤10)፡፡ ሁሉም ይሥሩ ወይም አንዳቸውም አይሥሩ፡፡ ክርስቶስ የተወሰኑቱን የተወሰኑትን ነገሮቹን ከፈጸመ እነዚያም ፤የመስዋዕት ሥርዓት፤ ሁሉንም እሱ ፈጽሞታ፡፡

“ትዕዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነው፡፡ ትዕዛዛቶቹም ከባዶች አይደሉም” (1ኛ ዮሐንስ መልዕክት 5፤3)፡፡ በመሠረቱ አሥርቱ ትዕዛዛት አጠቃላይ የብሉይ ኪዳን ህግ ማጠቃለያ ነበር፡፡ ከአሥርቱ ትዕዛዛት ዘጠኙ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በግልጽ ተደግመዋል (ሁሉም የሰንበትን ቀን ለመመልከት ካለው ትዕዛዝ በስተቀር)፡፡ በእርግጠኝነት እኛ እግዚአብሔርን እየወደድን ከሆነ የውሸት አማልክቶችን የምናመልክ ወይም በጣኦቶች ፊት የምንሰግድ አንሆንም፡፡ ባልንጀሮቻችንን እየወደድን ከሆነ አንገድላቸውም፤አንዋሻቸውም፤በእነሱ ላይ አናመነዝርም ወይም የእነሱ የሆነውን ነገር አንመኝም፡፡ የብሉይ ኪዳን ህግ ዓላማ እኛ ሰዎች ህግን መጠበቅ አለመቻላችንን ለመውቀስ እና ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኝ መፈለጋችንን ያመለክተናል (ወደ ሮሜ ሰዎች 7፤7-9)፡፡ የብሉይ ኪዳን ህግ ለሁሉም ሰዎች ለሁልጊዜ የሚሆን ህግ እንዲሆን ፈጽሞ በእግዚአብሔር ታስቦ አያውቅም፡፡ እኛ እግዚአብሔርን እና ባልንጀሮቻችንን ልንወድ ይገባል፡፡ እነዚያን ሁለቱን ትዕዛዛት በታማኝነት ብንታዘዝ እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልጋቸውን ሁሉ እንጠብቃለን፡፡

መዳን በእምነት ብቻ ነው ወይስ በእምነት እና በሥራዎችም ጭምር ነው?


መዳን በእምነት ብቻ ነውን ወይስ በእምነት እና በሥራዎችም ጭምር ነው? በኢየሱስ በማመን ብቻ ነው የዳንኩት ወይስ በኢየሱስ ማመን እና የተወሰኑ ነገሮችን ማድረግ አለብኝ?

ወደ ሮሜ ሰዎች 32851 እና ወደ ገላቲያ ሰዎች 324 ከያዕቆብ መልዕክት 224 አወዳድር፡፡ 

የተወሰኑቱ በጳውሎስ (መዳን በእምነት ብቻ ነው) እና በያዕቆብ (መዳን በእምነት እና በሥራዎችም ጭምር ነው) መካከል ልዩነት ያያሉ፡፡ ስለዚህም እንዲህ የሚል ይመሥላቸዋል---

·         ጳውሎስ መጽደቅ በእምነት ብቻ እንደሆነ አጥብቆ ይናገራል (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 28-9) 
·         ያዕቆብ ደግሞ መጽደቅ በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራም ጭምር ነው እያለ ነው፡፡ 

ነገር ግን ያዕቆብ ሰው በእምነት እና በሥራ ይድናል እያለ ሳይሆን አንድ ሰው ምንም ዓይነት በጎ ሥራዎችን ሳያደርግ እምነት ሊኖረው ይችላል የሚለውን እምነትን ነው እያፈረሰ ያለው (የያዕቆብ መልዕክት 217-18)፡፡ 

ያዕቆብ በክርሰቶስ የሆነ እውነተኛ እምነት የተለወጠን ህይወት እና በጎ ሥራዎችን ይፈጥራል የሚለውን ነጥብ እያጎላ ነው(የያዕቆብ መልዕክት 220-26)፡፡ 

ያዕቆብ መጽደቅ በእምነት እና በሥራም ጭምር ነው እያለ አይደለም ነገር ግን በእውነት በእምነት የጸደቀ  ሰው ይልቅ በህይወቱ በጎ ሥራዎች ይኖረዋል:: አንድ ሰው አማኝ እንደሆነ ቢናገር ነገር ግን በህይወቱ በጎ ሥራዎች ከሌሉ እሱ በክርስቶስ እውነተኛ እምነት የላቸውም ይሆናል፡፡ (የያዕቆብ መልዕክት 214172026)

ጳውሎስ በጽሑፎቹ ውስጥ ተመሳሳይ ነገር ይናገራል፡፡ የመልካም ፍሬ አማኞች በህይወታቸው በገላቲያ 522-23 ውስጥ የተዘረዘሩትን ሊኖራቸው ይገባቸዋል፡፡ ጳውሎስ ወዲያውኑ እኛ በሥራ ሳይሆን በእምነት እንደዳንን ከነገረን በኃላ መልካም ሥራዎችን ለማድረግ እንደተፈጠርን ይነግረናል፡፡ (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 210) ልክ ያዕቆብ ባዳረገው የህይወት ለውጥ ያህል ጳውሎስ ይጠብቃል፤

ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤አሮጌው ነገር አልፏል፤እነሆ አዲስ ሆኖአል” (2 ቆሮንቶስ 517) ድነትን በተመለከተ ያዕቆብ እና ጳውሎስ በትምህርታቸው አይቀዋወሙም፡፡ ተመሳሳይ ጉዳዮችን በተለያዩ አመለካከቶች ያያሉ፡፡ 

ጳውሎስ መጽደቅ በእምነት ብቻ እንደሆነ በቀላሉ ያን ሲያጎላ ያዕቆብ ደግሞ በክርስቶስ የሆነ እውነተኛ እምነት በጎ ሥራዎችን በመፍጠሩ እውነታ ላይ ያጠብቃል፡፡

ስለእዚህ መፅሐፍ ቅዱስ ሲነግረን ሰው የሚድነው በእምነት ብቻ ነው በእውነት የዳነ ሰው ግን ከአዲሱ ማንነት የተነሣ መልካመ ሥራን ያደረጋል በፍቅር ስለሚመላለሥ

1.       ሮሜ 3:28-30, " 28 ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና።  ወይስ እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ ደግሞ አምላክ አይደለምን? አዎን፥ የተገረዘን ስለ እምነት ያልተገረዘንም በእምነት የሚያጸድቅ አምላክ አንድ ስለ ሆነ የአሕዛብ ደግሞ አምላክ ነው።"
2.      ሮሜ4:5, "ነገር ግን ለማይሠራ፥ ኃጢአተኛውንም በሚያደድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ"
3.      ሮሜ5:1, "እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ፤"
4.      ሮሜ9:30, "እንግዲህ ምን እንላለን? ጽድቅን ያልተከተሉት አሕዛብ ጽድቅን አገኙ፥ እርሱ ግን ከእምነት የሆነ ጽድቅ ነው፤"
5.      ሮሜ10:4, " የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።"
6.      ሮሜ 11:6, " በጸጋ ከሆነ ግን ከሥራ መሆኑ ቀርቶአል፤ ጸጋ ያለዚያ ጸጋ መሆኑ "
7.      ገላትያ 2:16, "ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን አውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል።"
8.     ገላትያ 2:21, የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።
9.      ገላትያ 3:5-6, " እንግዲህ መንፈስን የሚሰጣችሁ በእናንተም ዘንድ ተአምራት የሚያደርግ፥ በሕግ ሥራ ነውን ወይስ ከእምነት ጋር በሆነ መስማት ነው?  እንዲሁ አብርሃም በእግዚአብሔር አመነና ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት"
10.  ገላትያ3:24, "እንደዚህ በእምነት እንጸድቅ ዘንድ ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን ሆኖአል፤"
11.   ኤፌሶን 2:8-9, " ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ 9 ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም"
12.  ፊሊጲሲቶስ 3:9, "በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤"



ስለዚህ ሰው የሚፀድቀው በሥራ ወይም ሕግን በመጠበቅ ሳይሆን በእምነት ነው እውነተኛ እምነት ደግሞ ፍሬ አለው ፍሬ ከሌለው ግን እውነተኛ አይደለም


ያዕቆብ 2:14-25 “ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን? ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፥  ከእናንተ አንዱም። በደኅና ሂዱ፥ እሳት ሙቁ፥ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል?
 እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።  ነገር ግን አንድ ሰው። አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል።  
 እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።  አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን? 
 አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?   እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን?   መጽሐፍም። አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ።  ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን በሥራ እንዲጸድቅ ታያላችሁ። 
  እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?   ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።

ለማጠቃለል መፅሐፍ ቅዱስ በግልፅ እንደሚናገረው ሰው የሚድነው በእምነት ብቻ ነው:: እውነተኛ እምነት ወይም በእውነት የዳነ ሰው የሚታይበት ፍሬ (መልካም ሥራ) አለ:: ይህም መልካም ፍሬ የሚታይበት በውስጡ ከሚያድረው መንፈስ ቅዱስ የተነሣ ነው:: ይህም የእግዝአብሐር መንፈስ ፍሬ ምን እንደሆነ በገላትያ 5:22 ላይ ተገልጥዋልየመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።ይህ ቨው መልካም ሥራ:: ይህ ፍሬ የማይታይበት ከሆነ ግን መዳኑ አጠራጣሪ ነው::

በተቃራኒው ሰው ሕግን በመጠበቅ ወይም ደግሞ በሥራ ነው የምፀድቀው ካለ ልክ እንደገላትያ ሰዎች መሆኑ ነው (ገላትያ 3 አንብብ)

1 የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን   
2 ይህን ብቻ ከእናንተ እንድማር እወዳለሁ፤ በሕግ ሥራ ወይም ከእምነት ጋር በሆነ መስማት መንፈስን ተቀበላችሁን?   
3 እንዲህን የማታስተውሉ ናችሁ? በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋ ትፈጽማላችሁን?   
4 በውኑ ከንቱ እንደ ሆነስ እንደዚህ ያለ መከራ በከንቱ ተቀበላችሁን?   
5 እንግዲህ መንፈስን የሚሰጣችሁ በእናንተም ዘንድ ተአምራት የሚያደርግ፥ በሕግ ሥራ ነውን ወይስ ከእምነት ጋር በሆነ መስማት ነው? 
6 እንዲሁ አብርሃም በእግዚአብሔር አመነና ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት።   
7 እንኪያስ ከእምነት የሆኑት እነዚህ የአብርሃም ልጆች እንደ ሆኑ   
8 መጽሐፍም እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ። በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ። 
 9 እንደዚህ ከእምነት የሆኑት ካመነው ከአብርሃም ጋር ይባረካሉ። 
 10 ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ በእርግማን በታች ናቸውና፤ በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና። 
11 ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው።   
12 ሕግም ከእምነት አይደለም ነገር ግን። የሚያደርገው ይኖርበታል ተብሎአል።   
13 በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤
14 የመንፈስን ተስፋ በእምነት እንድንቀበል፥ የአብርሃም በረከት ወደ አሕዛብ በኢየሱስ ክርስቶስ ይደርስላቸው ዘንድ።

ስለእዚህ እናስተውል ሰው የሚድነው በእምነት ነው የዳነ ሰው ግን የሚታይ መልካም ሥራ አለው በአፉ በእምነት ድኛለሁ አያለ ነገር ግን ምነም የሚታይ መልካም ሥራ (ፍሬ) ከሌለው መዳኑ ያጠራጥራል

ዮሐንስ 15:1-6 “እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው።   ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል።   እናንተ ስለ ነገርኋችሁ ቃል አሁን ንጹሐን ናችሁ፤   በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም።   እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።   በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፥ ያቃጥሉአቸውማል።