ዌብሳይት ላይ ወይም በሰዎች ወይም መንገድ ላይ በነፃ ወይም በትንሽ ብር በPaul C Jong የውሃና መንፈሱ ወንጌል የሚል መፅሐፍ አግኝተው አንብበው ይሆን ከሆነ እነዚህ አስተውሉ...
ይህ ቃሉ ከሚያስተምረን የተለየ ወንጌል ስለሆነ ይጠንቀቁ!!!
• የድሮውን ምኞታችሁን አትከተሉ
• ቃሉን አድርጉ
• የኃጢአት ባሪያዎች አትሁኑ
• ኃጢአት አይገዛችሁም
• ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ
• ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥
• በሥጋችሁ ኃጢአት አይንገሥ
1 ዮሐ 2:1 " ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።"
ያዕ 5:16 "እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።"
1. ለመዳን ኢየሱስ በመጥምቁ ዮሐንስ ሲጠመቅ የዓለም ሁሉ ሃጥያአት እንደተላለፈበት ከመስቀሉ ሞት በተጨማሪ ማመን አለቦት ይሎታል መፅሐፉ
2. አንዴ በእነሱ ወንጌል አምነው ከዳኑ በሁዋላ እርሶ ሃጥያአት ቢሰሩ ችግር የለውም ሃጥያአቶ ይቅር ስለለተባሉ ይሎታል መፅሐፉ
3. በክርስትና ሕይወቶ ምንም ሃጥያአት ቢሠሩ መናዘዝ አያስፈልግም ይሎታል
ይህ ቃሉ ከሚያስተምረን የተለየ ወንጌል ስለሆነ ይጠንቀቁ!!!
የእግዝአብሔር ቃል ሲያስተምረን...
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ከእሱ በፊት በተላከው መጥምቁ ዮሐንስ መጠመቁን ከእዛም ማገልገሉን በመጨረሻም ሃጥያአታችንን በመስቀል ላይ ተሸክሞ ደሙን በማፍሰስ ዋጋ እንደከፈለልን በሶስተኛው ቀን እንደተነሳ ከእዛም ከጥቂት ጊዜ በሁዋላ እንዳረገ አሁን ተመልሶ እስኪመጣ ድረስ በአባቱ ቀኝ እንዳለ እንደተፃፈው እንደቃሉ እናምናለን
ከእዚህ በተረፈ
1. መጥምቁ ዮሐንስ ሊቀ ካህን ነው የሚለውን የPaul C Jong ፍልስፍና አናምንም:: ምክንያቱም መጥምቁ ዮሐንስ በነበረበት ጊዜ ሊቀ ካህን የነበረው ቀያፋ እንደነበር ነው ቃሉ የሚያስተምረው:: በአንድ ወቅት ደግሞ ሁለት ሊቀ ካህን በምድር ሊኖር አይችልም::
Paul C Jong መጥምቁ ዮሐንድ ሊቀ ካህን ነው የሚል መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደሌለ አልጠፋውም ነገር ግን በማጠጋጋት ኢየሱስ እንዲህ ያለውን " እነሆ፥ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ በመንግሥተ ሰማያት ግን ከሁሉ የሚያንሰው ይበልጠዋል።"
ይህ ጥቅስ መጥምቁ ዮሐንስ ሊቀ ካህን እንደሆነ በፍፁም አይናገረም ቃሉን ምንም መተንተን ሳያስፈልገን መጥምቁ ዮሐንስ ማን እንደሆነ ኢየሱስ ራሱ ይነግረናል እንዲህ ብሎ... "እነሆ፥ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ #መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ"... ስለዚህ ምንም እንኩዋ መጥምቁ ዮሐንስ የሌዊ የካህናት ወገን ቢሆንም መልዕከተኛ እንጂ ሊቀ ካህን አይደለም አልነበረምም
ምናልባት እንዲህ የሚለውን ብናይ..."ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤"... ይህ ሊቀ ካህን መሆኑን ሳይሆን የሚናገረው ከሌሎች ነቢያት ይልቅ ከእናቱ ማህፀን ጀምሮ በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ መሆኑ ምሳሊያዊ የሆነ ሕይወቱ መልዕክቱ የተለየ መሆኑ የተላከበት መልዕክት ከሌሎቹ የተለየ መሆኑ የክርስቶስን መንገድ የሚጠርግ የሚያዘጋጅ መሆኑ ስለክርስቶስ በአካል እያሳየ የመሰከረ መሆኑ ከሌሎች ነቢያት ሁሉ ያስበልጠዋል ይህ ነው እንጂ የሚለየው በፍፁም ሊቀ ካህን አልነበረም የእግዝአብሔር ቃልም ሊቀ ካህን ነበረ አይለንም
በእነሱ እምነት ሰው ይድናል የሚሉት:
""ኢየሱስ ክርስቶስ መጥምቁ ዮሐንስ (በእነሱ ሊቀ ካህኑ) ኢየሱስን ሲያጠምቀው: የዓለምን ሁሉ ሃጥያአት በኢየሱስ ላይ ጫነበት ወይም አስተላለፈበት:: ይህንን ጨምሮ በመስቀል ላይ ዋጋ መክፈሉን ስናምን እንድናለን ነው::""" ነገር ግን Paul C Jong በእዚህ በመጥምቁ ዮሐንስ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ከደህንነት ጋር አያይዞ የሚሰብከውን ነገር: መፅሐፍ ቅዱስ ግን በእዛ መልኩ በፍፁም አልጠቀሰውም:: እንዲያው ጳውሎስ የሚሰብከው ወንጌል ምን አይነት እንደሆነ ሲናገር እንዲህ ነው ያለው...
1ቆሮ 15:1-4 "ወንድሞች ሆይ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ፤ በከንቱ ካላመናችሁ በቀር፥ ብታስቡት፥ በምን ቃል እንደ ሰበክሁላችሁ አሳስባችኋለሁ። እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ። መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ" በPaul C Jong እምነት: ዋና መሠረት የሆነውን: የመጥምቁ ዮሐንስ የዓለምን ሃጥያአት ሁሉ በኢየሱስ ላይ አስተላለፈ የሚለውን: በፍፁም አልጠቀሰውም:: ለምን ሐዋርያቶች በመልዕክታቸው: አንዴም እደግመዋለሁ: አንዴም ይህ አስተማሪያችሁ: ዋና ነው የሚለውን አልጠቀሱም??
ይልቅስ ለመዳን የሚያስፈልጉትን ቃሉ በግልፅ የሚነግረን እንዲህ ብሎ ነው...
የሐዋ ሥራ 16:30-31 "ወደ ውጭም አውጥቶ። ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? ኣላቸው። እነርሱም። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።"
ሮሜ 10:9-10 "ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።"
ኤፌ 2:8 "ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
ከእዚህ ውጪ በዮሐንስ ጥምቀት ማለትም የዓለምን ሃጥያአት ሁሉ በኢየሱስ ላይ ጫነ የሚል ትምህርት መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሳይሆን የሚገኘው የPaul C Jong ፍልሰፍና መፅሐፍ በቻ ነው::
*** መፅሐፍ ቅዱስ ሲያስተምረን ድነት(Salvation) ወይም ፅድቅ(Justification) ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በሠራልን ሥራ በእምነት የምናገኘው ነገር ነው
*** ቅድስና (Sanctification) እኛ ከዳንን በሁዋላ በቃሉና በመንፈስ ቅዱስ እያደግን የምናፈራው ፍሬ ነው
አንድ የዳነ ሰው በሕይወቱ ፍሬ ማፍራት አለበት:: እንደሚያፈራው ፍሬም ሽልማት አለው:: ፍሬ (መልካም ሥራ) ለማፍራት ራሱን ወይም መንፈሱን: በእግዝአብሔር ቃል: በፀሎት: ሕብረት በማድረግ: በመፆም: በመሳሰሉት... መንፈሱን በመመገብ ራሱን ማሳደግ አለበት:: መንፈሱን ሁሌ የሚመግብ ሰው በሕይወቱ የመንፈስ ፍሬ ይታይበታል::
ቃሉ እንደሚነግረን የመንፈስ ፍሬ እነዚህ ናቸው::
ገላ 5:22 "የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።"
ስለዚህ በቃሉ የምንደገፍ እና የምንታመን ከሆነ ከአንድ የዳነ ሰው እነዚህ ፍሬዎች ይጠበቃሉ በአፉ ድኛለሁ እያለ በተግባር ወይም በሕይወቱ የሚታየው ሃጥያአት ከሆነ ራሱን ያታልላል እንጂ አልዳነም መጨረሻው ገሃነም ነው
ስለዚህ ቃሉ እንደሚል ሰው የሚድነው በእምነት ብቻ እንጂ በእምነትና በሥራ አይደለም:: ነገር ግን አንድ የዳነ ሰው በሕይወቱ ፍሬ መታየት አለበት የሚታየው ግን የሥጋ ሥራ ብቻ ከሆነ አልዳነም
ለመጨመር ያህል ቃሉ እንዲህ ይላል...
ያዕ 1:22 "ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።"
1 ጴጥ 1:14-15 "እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ። ዳሩ ግን። እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።"
ሮሜ 6:11-18 "እንዲሁም እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ፥ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቈጠሩ። እንግዲህ ለምኞቱ እንድትታዘዙ በሚሞት ሥጋችሁ ኃጢአት አይንገሥ፤ ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ። ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና። እንግዲህ ምን ይሁን? ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላይደለን ኃጢአትን እንሥራን? አይደለም። ለመታዘዝ ባሪያዎች እንድትሆኑ ራሳችሁን ለምታቀርቡለት፥ ለእርሱ ለምትታዘዙለት ባሪያዎች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን? ወይም ለሞት የኃጢአት ባሪያዎች ወይም ለጽድቅ የመታዘዝ ባሪያዎች ናችሁ። ነገር ግን አስቀድማችሁ የኃጢአት ባሪያዎች ከሆናችሁ፥ ለተሰጣችሁለት ለትምህርት ዓይነት ከልባችሁ ስለ ታዘዛችሁ፥ ከኃጢአትም አርነት ወጥታችሁ ለጽድቅ ስለ ተገዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።"
*** እንግዲህ በግልፅ በእግዝአብሔር ቃል እንደምናየው አንዴ በኢየሱስ አምነን ከዳንን በሁዋላ ሰው ስለሆንን ሃጥያአት እየሠራን መቀጠል ትችላላችሁ በፍፁም በፍፁም አይልም:: ሃጥያአት የመስራት ፈቃድ
(Licence) አልተሰጠንም::
ቃሉ የሚለው በተቃራኒው...
• ቅዱሳን ሁኑ• የድሮውን ምኞታችሁን አትከተሉ
• ቃሉን አድርጉ
• የኃጢአት ባሪያዎች አትሁኑ
• ኃጢአት አይገዛችሁም
• ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ
• ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥
• በሥጋችሁ ኃጢአት አይንገሥ
ይህንን ነው የእግዝአብሔር ቃል አጥብቆ የሚነግረን::
ስለዚህ ወንድሞቼና እህቶቼ ሰው ስለሆንን ሃጥያአት ከመፅራት ልንቆጠብ አንችልምና ብንሠራ ችግር የለውን አንዴ በመስቀል ላይ ወይም በዮሐንስ ጥምቀት ተወግዶልናል የሚል ትምህርት መፅሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም::
*** ሰው ከዳነ በሁዋላ ሃጥያአት አይሰራም??
እንደሰዉ ዓይነት የሚሠራው ሃጥያአት ሊበዛም ሊያንስም ይችላል እንጂ ሃጥያአት መሥራቱ አይቀርም
*** ታዲያ ሃጥያአት ቢሠራ ምን ያድርግ??
የእግዝአብሔር ቃል እንዲህ ይለናል1 ዮሐ 2:1 " ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።"
ያዕ 5:16 "እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።"
****ኑዛዜ Confession እና ንሰሃ Repentance የሚያመሳስላቸው ነገር እንዳለ ሁሉ የሚለያያቸውም ነገር አለ
አንድ ሰው መጀመርያ: የእግዝአብሔርን ቃል አንብቦ: ወይም ሰምቶ: ሃጥያአተኝነቱን አውቆ: ሃጥያአቱን ተናዞ (Confessed) ንሰሃ ከገባ (Repent) ኢየሱስ በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶ ዋጋ እንደከፈለለት አምኖ ከተቀበለ ያ ሰው ሃጥያአቱ በሙሉ ተሰርዮለታል::
ንሰሃ (Repentance) ማለት: የኑሮውን: የአስተሳሰቡን ወይም በሥጋ መመላለሱን: ቀይሮ በመንፈስ መመላስ የሕይወቱን አቅጣጫ መቀየሩን የሚያሳይ ነው::
ስለዚህ እንዲህ ንሰሃ የገባ ሰው ድነትን ስላገኘ ከፍርድ አምልጥዋል::
ይህ የዳነ ክርስትያን በሕይወቱ ሲኖር: ሃጥያአት መሥራቱ አይቀርም:: ይህም ከአምላኩ ጋር ያለውን ግንኙነት ያበላሸዋል:: ስለዚህ ሃጥያአት መሥራቱን በተገነዘበ ቁጥር ለአምላኩ መናዘዝ (confess)
አለበት::
የእግዝአብሔር ቃል የሚለውን እንይ...
1ዮሐ1:6-10 "ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤ ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል። ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም። በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።"
ከእዚህ የእግዝአብሔር ቃል የምንረዳው መጀመርያ ይህን መልዕክት ሐዋርያው ዮሐንስ የፃፈው ህብረት አለን ለሚሉ በብርሃን ለሚመላለሱ ለዳኑ ክርስትያኖች ነው:: ለእነዚህ ክርስትያኖች...."ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።"... ይላቸዋል:: ምክንያቱም ወደፍፁምና ገና ስላልደረሱ: በሕይወታቸው ሃጥያአትን መሥራታቸው አይቀርም:: ስለዚህ ሃጥያአታቸውን እንዲናዘዙ ይነግራቸዋል ይመክራቸዋል::
ከእዛም ይቀጥልና እንዲህ ይላል...
1ዮሐ 2:1 "ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።"...
አንድ ፀጋውን አምኖ የዳነ ክርስትያን: መጀመርያ ንሰሃ የገባ ጊዜ: ሃጥያአቱ ሁሉ ተሰርዮለታል:: ይህ ማለት ግን በሰዋዊው ተፈጥሮ ምክንያት: በሕይወቱ በኑሮው ሃጥያአትን እንዲሰራ ፈቃድ አግኝትዋል ማለት አይደለም:: ቃሉም እንደሚል...
ሮሜ 6:15 "እንግዲህ ምን ይሁን? ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላይደለን ኃጢአትን እንሥራን? አይደለም።"
ስለዚህ የዳነ ሰው ገና ለገና ሃጥያአቱ ሁሉ ስለተሰረየለት: ሃጥያአትን የመሥራት ፈቃድ የለውም:: ግን አሁንም ቃሉ እንደሚል...."ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።"...ሃጥያአትን መሥራቱ አይቀርም:: ለእዚህ ከድነት በሁዋላ ለሚሠራው ሃጥያአት መናዘዝ አለበት:: አሁን ቃሉ እንደሚለው.."በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።"
ሌላም ቦታ ሐዋርያው ያዕቆብ እንዲህ ይላል....
ያዕ 5 16 "እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ።"
ለማጠቃለል: ቃሉም ስለሚያዝ: አንድ የዳነ ክርስትያን ሃጥያአት የማድረግ ፈቃድ የለውም:: ሃጥያአትን ቢሰራ ግን በሰማይ ጠበቃ ስላለው ሃጥያአቱን መናዘዝ አለበት::
ነገር ግን አንዴ በንሰሃ ሃጥያአቴ ሁሉ ይቅር ስለተባለ: ደግሞም በተፈጥሮዬ ሰው ስለሆንኩኝ: ሃጥያአትም መሥራቴ ስለማይቀር: ኑዛዜ አያስፈልገኝም: ዝም ብዬ እንደተለመደው ሃጥያአት እየሰራሁ እቀጥላለሁ ሰው ስለሆንኩ የምንል ከሆነ: ቃሉ እንዲህ ይለናል....
ዕብ 10:26-27 "የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፥ የሚያስፈራ ግን የፍርድ መጠበቅ ተቃዋሚዎችንም ሊበላ ያለው የእሳት ብርታት አለ።"