የወሊድ መከላከያ መጠቀም
ሃጥያአት ነውን??
የእኔ ሃሳብ ሃጥያአት አይደለም የሚል ነው::
ለምሳሌ እዚህ ከላይ ሃሳብ የሰጡ ሰዎች መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ አትግደል የሚል ተፅፍዋል የሚሉ አሉ:: ይህ መከላከያ ማለት እኮ ፅንስ እንዳይፈጠር የሚያደርግ እንጂ: የተፈጠረን ፅንስ የሚገድል ማለት አይደለም:: ስለዚህ አትግደል ከሚለው ትዕዛዝ ጋር ማገናኘት አንችልም::
ልጆችን በተመለከተ መፅሐፍ ቅዱስ ልጆች የእግዝአብሔር ስጦታ እንደሆኑ ይነግረናል እንጂ: ስለወሊድ መቆጣጠር አይናገርም:: ምናልባት ቢቀራረብ በዘፍ 38:8-10 እንዲህ የሚል አለ...
"ይሁዳም አውናን፦ ወደ ወንድምህ ሚስት ግባ፥ አግባትም፥ ለወንድምህም ዘርን አቁምለት አለው። አውናንም ዘሩ ለእርሱ እንዳይሆን አወቀ ወደ ወንድሙ ሚስት በገባ ጊዜ ለወንድሙ ዘር እንዳይሰጥ ዘሩን በምድር ያፈስስው ነበር። ይህም ሥራው በእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ ሆነበት፥ እርሱንም ደግሞ ቀሠፈው።"
እዚህ ጋር እግዝአብሔር አውናን የቀሰፈው ልጅ ላለመውለድ ዘሩን ምድር ላይ ስላፈሰሰ ሳይሆን: በተንኮል ሃሳቡ ምክንያት ነው:: ከጥቅሱ እንደምናነበው: በእዚያን ጊዜ በነበረው ሥርዐት: አንዲት ሴት ባልዋ ሳይወልድ ከሞተ: የባልዋን ወንድም ማግባት ነበረባት: የሞተው ባልዋ ዘር እንዲቀርለት:: አውናን ግን የሚወለደው ልጅ በእሱ ስም እንደማይቀጥል ስለተረዳ: በውስጡ በተፈጠረው ክፉ ሃሳብ: ለወንድሙ ዘር እንዳይቀርለት: ዘሩን በምድር ላይ አፈሰሰ:: ይህ ክፉ ሃሳቡ ደግሞ: እግዝአብሔርን አስቆጣና በእርሱ ላይ ሞት አመጣበት::
መጀመርያ ስለወሊድ መቆጣጠርያ ስንነጋገር: ሰዎች ወሊድን ለመቆጣጠር የተለያዩ ነገሮች እንደሚጠቀሙ እናስተውል:: እስቲ እንዘርዝራቸው...
ሴት ልጅ ፅንስ በማትይዝበት ጊዜ እየመረጡ ግንኙነት ማድረግ: ፅንስ መከላከያ ዘዴ ነው
ወንድ ልጅ በግኑኝነት ጊዜ ዘሩን ውጭ ማፍሰስ: ፅንስ መከላከያ ዘዴ ነው
የወንድ ወይም የሴት ኮንዶም መጠቀም: ፅንስ መከላከያ ዘዴ ነው
የወሊድ መከላከያ እንክብል መጠቀም: ፅንስ መከላከያ ዘዴ ነው
በማህፀን ውስጥ በሚቀመጥ ወይም ሌላ የህክምና ዘዴዎች መጠቀም: ፅንስ መከላከያ ዘዴ ነው
እዚህ ጋር ልብ ልንለው የሚያስፈልገው ስለተፀነሰ ፅንስና እሱን ስለማቋረጥ አይደለም:: እየተወያየን ያለነው እየተወያየን ያለነው ፅንስ ሳይፈጠር ስለመከላከል ነው::
ስለዚህ ከላይ የጠቀስኩዋቸው ፅንስ መከላከያዎች ዘዴዎች ሁሉ: አይነታቸው እና መንገዳቸው ይለያይ እንጂ: ሁሉም ፅንስ መከላከያዎች ናቸው:: ስለእዚህ የወሊድ መከላከያ እንክብል መውሰድ ሃጥያአት ነው ካልን: ኮንዶም መጠቀምም ሃጥያአት ሊሆን ነው:: ምክንያቱም ሁለቱም ዘድያቸው ይለያይ እንጂ ፅንስ መከላከያ ዘዴዎች ናቸው::
እንደገናም ሴት ልጅ ፅንስ በማትይዝበት ጊዜ እየመረጡ መገናኘት ማለት: ልክ እንደ የወሊድ መከላከያ እንክብል ዋናው አላማው ፅንስ እንዳይፈጠር ለማድረግ ነው:: ልዩነቱ አንደኛው በተፈጥሮ ዘዴ መጠቀም ሲሆን አንደኛው ደግሞ በሰው ሰራሽ መንገድ መጠቀም ነው::
ስለዚህ ለእኔ ሃጥያአቱ የተፈጠረን ፅንስ ማቋረጥ እንጂ: ያልተፈጠረን ፅንስ እንዳይመጣ በተለያዩ መንገዶች መጠቀም ሃጥያአት ነው ብዬ መቀበል ይከብደኛል::

ሴሰኝነት: ዝሙት: ፅንስ መከላከያ ወሰድክም አልወሰድክም ሃጥያአት ነው:: በትዳር ውስጥ ያሉ ባልና ሚስቶች የልጆቻቸውን ቁጥር በመገደብ: ልጆቻቸውንም በሥርዐቱ ለማሳደግ: ሴትየዋንም ብዙ ልጆች በመውለድ እንዳትጎዳ: የተለያዩ ተፈጥሮአዊም ሆነ ሰው ሰራሽ ዘዴዎችን ፅንስ እንዳይፈጠር የመከላከያ ዘዴ መጠቀም: ሃጥያአት አይደለም ብዬ ነው ነው የማምነው:: መጽሐፍ ቅዱስም አንድም ቦታ የፅንስ መከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም ሃጥያአት ነው ብሎ አይነግረንም::