Wednesday, August 15, 2012

በውኑ፣ ክርስቶስ ያማልዳልን?


በውኑ፣ ክርስቶስ ያማልዳልን?

 አንዳንዶች ስለክርስቶስ የማማለድ ሥራ ለመቃወም ሲሉ መጽሐፍ ቅዱስን እስከመደለዝ ደርሰዋል። ሰብዓ ሊቃናትና ዐበይት የአብያተ ክርስቲያናት ጉባኤያት ያጸደቋቸውን የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ትርጓሜ በመሰረዝ የራሳቸውን ክልላዊ መጽሐፍ ቅዱስ እስከማሳተም የደረሱት የክርስቶስን ሥጋ የመልበስን ምስጢርና አሁንም በአብ ቀኝ የተቀመጠበትን አምላክ ሰው የሆነበትን ማንነት ለመጠበቅ ሲሉ የግሪኩንና እብራይስጡን ትርጉም ሰርዘውታል። በአንድ በኩል መናፍቃን ለራሳቸው እንዲያመቻቸው የወንጌል ቃልን ይሰርዛሉ፤ ይደልዛሉ እያልን በሌላ መልኩ ወቃሾች፤ የተወቃሾችን ታሪክ መድገም መደለዝ በመሠረቱ አሳዛኝ ነገር ነው። አበው ያቆዩትንና የተጻፈልንን እውነት ይዞ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ቃል ግልጽልጽ አድርጎ መመለስ ሲገባ፤ የተጻፈውን ሰርዞ፤ ከማስተማር ለመደበቅ መሞከር አስደንጋጭ ነው። ይህንን ከእውነት የመሸሽ ተግባር በማብራራት ከታች የቀረበው ጽሁፍ አንድ ነገር ይጠቁመናል። መሰረዛቸውን የማይክዱ ግን በመሰረዛቸው ከሲኖዶሳውያት ጉባዔያት ጋር ለምን እንደተለያዩ ማሳመን የማይችሉ ሰዎች ይህን ጽሁፍ ሲያነቡ ጆሮአቸውን ሊያስክክ፤ ዓይናቸውንም ሊያጨልም ይችላል።
የጽሁፉ ባለቤት «አድነው ዲሮ» ይሰኛሉ።

አንዳንድ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ ያደረገውን ይህን የክርስቶስ የአማላጅነት አገልግሎት ትምህርትለመቀበል ለምን ተቸገሩ?

መልካምም ይሁን ጎጂ፣ የሰው ልጅ አንዴ የያዘውን አስተሳሰቡን፣ ልማዱንና ወጉን መተው ይቸገራል፡፡ እነዚህአስተሳሰቦች በአንድ ለሊት የተገነቡ ስላልሆኑ፣ በአንድ ለሊት ሊፈርሱ አይችሉም፡፡ ነጮች አሮጌ ልማዶችንየመሻር አስቸጋሪነትን «Old habits die hard!´ በማለት ይገልጻሉ፡፡ ትርጓሜውም አሮጌ ልማዶች በቀላሉአይሞቱም እንደማለት ነው፡፡ አንዴ ለዘላለም የሆነው የክርስቶስ ምልጃ፣ ምንም እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስምሆነ በአገራችን የእምነት ትውፊቶች በግልጽ የተነገረ ሥራ ቢሆንም በእኛ አገር ክርስትና አሁንም ድረስበቀላል ቁጥር በማይገመቱ ምእመናን ዘንድ በከፊል ተቀባይነት ለማግኝት አልቻለም፤ ወይም ግልጽ አይደለም፡፡የዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ ስለ ጉዳዩ ለማሰብ፣ መጽሐፍ ቅዱስን አስረጅ አድርጎ ከማቅረብ ይልቅ ለሰውአመክንዮ (logic) እና ልማድ ትልቅ ሥፍራ መስጠት እንደሆነ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ያምናል፡፡ ለምሳሌ«እንዴት አምላክ የሆነው ኢየሱስ ያማልዳል?´ «ምልጃ የፍጡራን ሥራ መሆን አለበት´ «ከማለደልንም፣ክርስቶስ ሊማልድልን የሚችለው በምድር ላይ ሳለ ብቻ መሆን አለበት´ የሚሉቱ አመክንዮዎች ለፍጥረታዊሰው አስተሳሰብ ተቀባይነት ለማግኘት ቀሊሎች መስለው ሊታዩ ይችላሉ፡፡ መታሰብ ያለበት ትልቅ ቁም ነገርግን፣ የትኛውም ውብ ተፈጥሮአዊ መነሻ አሳቦች ወደ ትክክለኛ መንፈሳዊ/መለኮታዊ /ማጠቃለያ ላይእንደማያደርሱን ሊታወቅ ይገባል፡፡ እንዲያውም ብዙዎቹ የእግዚአብሔር ሥራዎች -መዳናችንን ጨምሮ-ለእኛ ፍጥረታዊ አመክንዮ ግራና ሊቀበሏቸው የሚያስቸግሩ ናቸው (1ቆሮ. 118-21)፡፡ ለዚህ ነውየእግዚአብሔርን ነገር መረዳት ለፍጥረታዊ ሰው ሞኝነት የሚሆንበት፡፡ «ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔርመንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቀው አይችልም´ (1ቆሮ. 214)፡፡ ስለዚህ በመንፈስ የሚመረመረውን የእግዚአብሔርን አሳብ በራሱ ቃል መሰረት ለማረጋገጥከማጥናት ውጪ ከራሳችን አመክንዮና ሐይማኖታዊ ቅናቶች በመነሳት ድምዳሜ ላይ ለመድረስ የምናደርገውማንኛውም ጥረት ውጤቱ አደገኛ ነው፡፡ በአንድ ወቅት የሰማሁትን አንድ የእምነት ንግግር ላካፍላችሁናይህን ሃሳብ ልቋጭ፡፡ አንድ የእግዚአብሔርን መኖር የማያምን ሰው አንዱን አማኝ እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል፡- «እንዴት ዮናስ በታላቅ ዓሳ ሆድ ውስጥ ቀንና ለሊት ቆየ ብለህ ማመን ትችላለህ፤ ይህ ከሣይንስ ጽንሰሃሳቦች አኳያስ እንዴት ያስኬዳልብሎ ቢጠይቀው፣ «ወዳጄ አንተ የቸገረህ ይህን ማመን ቢሆንም  እንኳን ዮናስ በዓሳ አንበሪው ሆድ ውስጥ ማደር ይቅርና፤ ዓሣ አንበሪው ራሱ በዮናስ ሆድ ውስጥ 3 ቀናት አደረየሚል ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰፍሮ ባገኘው ለማመን አልቸገርም»´ አለውና ውይይቱ በዚያውተጠናቀቀ፡፡ የቱንም ያህል ለአእምሮአችንና ልማዶቻችን ይክበደው እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰፈሩትንግልጽ አሳቦች በመቃወም የራሳችንን የስሜት ሃሳብ ልናምን አይገባም፡፡      «ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትርበሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል» ዕብ 725 የሚለውን ግልጽ ቃል ያልተቀበለ «ዓሳ አንበሪ በዮናስ ሆድ ውስጥ አደረ» የሚል አስገራሚ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቢያገኝ በእርግጥም አይቀበልም።

የክርስቶስ የምልጃ አገልግሎት ከአብና መንፈስ ቅዱስ እንዲያንስ ያደርገዋልን?

ኢየሱስ ይህን የምልጃ ሥራ በመስራቱ ከአባቱም ሆነ ከመንፈስ ቅዱስ አያንስም፡፡ ለነገሩ፣ በግብር ላይተመስርተን የተግባሩን ባለቤት ክብር ወይም ሥልጣን መመዘንና ደረጃ ማውጣት የሰው ሥርዓት ስለ ሆነይህንን እርኩሰት የተሞላበትን ባህላችንንና አስተሳሰባችንን ለፈጣሪ ፍጹም ሥራ ምዘና ስናውለው ከፍተኛጥንቃቄ ማድረግ እንዳለብን መዘንጋት የለብንም፡፡ በዚህም ምክንያት ነው እግዚአብሔር ወልድ ያለማንምአስገዳጅነት በፈቃዱ በፈጸመው የምልጃ ሥራየተነሳ ወልድ፤ ከአባቱ እና ከመንፈስ ቅዱስ እንደሚያንስእንድናስብ የምንገደደው፡፡ እንግዲያው ሥላሴ በስልጣን፣ በገዢነት፣ በአምላክነት፣ ወዘተ አንድ ሲሆኑበግብር ግን እንደሚለያዩ ያስቀመጥነው የቤተክርስቲያኒቱ  የእምነት አቋም ፋይዳው ምኑ ላይ ነው?  በግብርአንጻር፡አብ በመውለዱ፣ ወልድ ደግሞ በመወለዱ ምክንያት አብ ወላጅ ስለሆነ የሚበልጥ፣ ወልድ ደግሞልጅ ስለሆነ የሚያንስ እንዳልሆነ መቀበል ካልከበደን፣ ለምን በመስቀሉ ሥራ ላይ በግብር፡አብ ተማላጅወልድ ደግሞ ማላጅ መሆኑን መቀበል ከበደንዛሬስ ወልድ የአብ ልጅ መሆኑን እናምናለን? ወይስ ልጅ መባሉ ከመስቀሉ በኋላ አብቅቷል? እንላለን። ልጅ የመባሉ ምስጢር ለአባቱ  የመታዘዙ ነገር ነው ካልን፤ የወልድን ማነስ እያመንን ነው ማለት ነው? ይህ አደገኛ ስህተት ነው። አብ ተማላጅ፤ ወልድ ማላጅ ነው ሲባል የአባትና የልጅነት ግብርን መናገራችን እንጂ የመለኮታዊ ዕሪና /እኩልነት/  ሚዛን እየሰፈርን አለመሆኑን ለመገንዘብ አለመቻል አስቸጋሪ ነገር ነው።

ኢየሱስ በመለኮቱ (በአምላክነቱከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል ስለመሆኑ የሚናገሩ በርካታ ጥቅሶችቢኖሩም ለአብነት የሚከተሉትን ይመልከቱ፡- « ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ፡እግዚአብሔርአባቴ ነው ስላለ፣ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት  ይፈልጉ ነበር´ (ዮሐ. 518)፡፡ «እኔና አብ አንድ ነን´ (ዮሐ. 1030)፡፡ « እኔን ያየ አብን አይቷል´ (ዮሐ. 149)፡፡ «ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው´ (ዮሐ. 1615)፡፡«በመጀመሪያ ቃል ነበር፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር፣ ቃልም እግዚአብሔር ነበር´ (ዮሐ. 11)፡፡ «እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው´ (1ዮሐ. 520)፡፡

ኢየሱስ እንደ አምላክነቱ ጸሎትን የሚሰማ ተማላጅ አምላክ ቢሆንም እንደ ሰውነቱ በግብሩ (ሊቀ ካህንነቱ)ደግሞ ሥለ እኛ በሰማያዊት መቅደስ ያለ ብቸኛ አማላጅ/አስታራቂ/መካከለኛ ነው፡፡ በአሁኑ ሰአት ያለውየኢየሱስ ምልጃ በምድር ላይ ከነበረበቱ ልዩ የሚሆነው ምልጃው  በተፈጸመ ሥራው ስለ እኛ በአብ ዘንድአንዴ የቀረበ ብቻ መሆኑ ነው (ዕብ. 92428)፡፡ ስለዚህ እኛም በምስጋናም በልመናም ሆነ በምልጃ ወደእግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል ስንቀርብ ኢየሱስ ክርስቶስ በአምላክነቱ ከአባቱ ጋር ጸሎታችንን የሚሰማናየሚቀበል ሲሆን በትስብእቱ ደግሞ ከእኛ ጋር ሆኖ ጸሎታችን ተሰሚነት እንዲኖረው በአባቱ ፊት ስለ እኛ ብቁሆኖ የሚታይ አማላጅ እንደሆነ ኅሊናችን ሊቀበለው ይገባል፡፡ ደም ሳይፈስ ስርየት እስከሌለ ድረስ ሃይማኖት የሌለው ሰው ወደክርስትና በእምነት ቢመጣ የሚታረቀው በማን ደም ነው? በአብ ዘንድ ተቀባይነት ባገኘው በእርቁ ደም በክርስቶስ በኩል ብቻ ነው።

3 ክርስቶስ ያማለደው በሥጋው ወራት (በምድር ሳለ) ብቻ ነው፡፡

ኢየሱስ በምድር ላይ በሰነበተበት 3አመት ተኩል ጊዚያት፣ በተለያየ ሁኔታ የምልጃ ሥራን ሰርቷል፡- ሉቃስ2231-32 ዮሐ 1721 ሉቃስ 2334 ዕብ. 57 - ነገር ግን አሁን በአባቱ ቀኝ በተቀመጠበት ጊዜ ይህቆሟል የሚሉ አንዳንድ ሰዎች አሉ፡፡ ይህ አስተያየት የክርስቶስን የክህነት ባሕሪ ጠንቅቆ ካለመረዳት ወይምከባዶ ቅንዓት የሚመነጭ ነው የሚሆነው፡፡ የክርስቶስ ክህነት እንደ አሮን ሞት የሚከለክለውና የሚቋረጥአይደለም (ዕብ. 717)፡፡ ሞት ያላስቀረው ሊቀ ካህናችን ስለ ሆነ ስለ እኛ «...ሲያማልድ ዘወትር በሕይወትይኖራል፡ ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል´ (ዕብ. 725)፡፡የኢሱስ ክህነት/ምልጃ ዘላለማዊና የማይለወጥ ክህነት/ምልጃ ነው « እርሱ (ኢየሱስ) ግን የማይለወጥክህነት አለው፤´፡፡ «... የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛየሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡´ (ሮሜ. 834) ይህ ጥቅስ የክርስቶስ ምልጃ/ክህነት በመሞቱ ምክኒያትያልተቋረጠ መሆኑን በግልጽ ያሳያል፡፡ ይህ ክህነት በምድር ላይ እያለ ብቻ ሳይሆን ከትንሳኤው በኋላ በአባቱቀኝ ተቀምጦም ሳለ አብሮት ያለ የዘላለም ሹመት እንደሆነ ያሳየናል፡፡ «አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመትለዘላለም ካህን ነህ´ (ዕብ. 56) ያለውን ትንቢት መዘንጋት የለብንም፡፡

«ልጆቼ ሆይ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህንን እጽፍላችኋለሁ፤ ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃአለን፤ እርሱም ጻድቅ የሆነ ክርስቶስ ነው፡፡´ (1ዮሐ. 21) የሚለው ጥቅስ የኢየሱስን የጥብቅና ማዕረግበጉልህ ያሳያል፡፡ ይህም ጥብቅና ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ሰዓት ብቻ ሳይሆን አሁንም ድረስ ወደእግዚአብሔር ለመቅረብም ሆነ የኃጢአት ይቅርታን ለመቀበል ትምክህት ሊሆነን የሚችል ጠበቃ ኢየሱስብቻ እንደሆነ የበስረናል፡፡ ጠበቃ አለን እንጂ ጠበቃ ነበረን አለማለቱን አንባቢ ልብ ይበል፡፡

«እርሱ (ክርስቶስ)  ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ´ (ዕብ. 1012) ስለ ተቀመጠ ምልጃውም አንዴ ለዘለዓለም የቀረበ የምልጃ/የክህነት ሥራ ስለሆነ ክርስቶስ ዛሬበምድር ላይ በነበረበት ወቅት እንደነበረው ሥርዓትና እንደ አሮን ክህነት በየአመቱ ወደ ቅድስት መስዋዕትይዞ መግባት አያስፈልገውም (ዕብ. 925)፡፡ በእግዚአብሔር ቀኝ ሆኖ ስለ እኛ ይማልዳል ማለት በመስቀል ላይየፈጸመውን ሥራ ይደጋግማል ማለት ሳይሆን በኢየሱስ በኩል ወደ እግዚአብሔር ስንቀርብ እርሱ ስለ እኛይታያል ማለት ነው እንጂ፡፡ «ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ» ዕብ 924

4 ኢየሱስ ካረገ በኋላም እንደሚማልድ የትውፊት መጽሐፍት ይናገራሉ፡-

«ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ የእኔ ስለ ሆኑት ምህረትን ወደ ምለምንበት ወደ ሰማይ ወደ አባቴ አርጋለሁአላቸው፡፡´ (መጽሐፈ ዚቅ ዘሰኔ ሚካኤል፣ ገጽ 189)

አብ ሆይ ስለ ኢየሱስ እርዳን፤ ክርስቶስ ወደ ቸር አባትህ አማጽነን/አማልደን የአብና የወለድ መንፈስአጽናናን (ሰዓታት ዘሌሊት ወዘንግህ፣ ገጽ 222)

5 መዳናችንን/መጽደቃችንን/መታረቃችንን ከዚህ የክርስቶስ ሥራ በተለየ መንገድ የምናገኘው ነው ወይ?

መዳናችንን/መጽደቃችንን/መታረቃችንን ከዚህ የክርስቶስ ሥራ በተለየ መንገድ እንደምናገኝ ማሰብ ወይምለማግኘት መሞከር የእግዚአብሔርን የማዳን መንገድ ለማሻሻል ከመሞከር ሌላ የተለየ ትርጉም ሊሰጠውአይችልም፡፡ ጽድቅ በሕግ በኩል ከሆነ፣ መዳን በሰው ምልጃ በኩል የሚገኝ ከሆነ፣ ወደ እግዚአብሔርለመቅረብ ሌላ የተሻለ መንገድ ካለ፣ እንግዲያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ (ገላ. 221)፡፡

6 እኔ ኃጢአተኛ ስለ ሆንኩ በእግዚአብሔር ፊት ልቀርብ አልችልም፤ ስለዚህ መካከለኛ ሰዎችያስፈልጉኛል?

ከአዳም ውድቀት በኋላ፣ ሰውን ከሰው ሳይለይ ሁሉ (ሮሜ. 39-11) በእግዚአብሔር ፊት መቅረብ አይችልምነበር፡፡ እግዚአብሔር ጻድቅ ስለ ሆነ እርሱ ፊት ሊቀርብ የሚችለው ልክ እንደርሱ ቅዱስ የሆነ ሰው ብቻነው፡፡(ማቴ. 548)፡፡  «እንግዲያስ ከሰው ዘር እንደ እርሱ ቅዱስ የሆነ ማን ሊገኝ ይችላል? የሚል ጥያቄ ያነሱይሆናል፡፡ መልሱ በእርግጥ ተችሏል የሚል ነው! ይህም ሰው ኢየሱስ ይባላል፡፡ «እኛ በእርሱ ሆነን (በክርስቶስሆነን) የእግዚአብሔር ጻድቅ እንባል ዘንድ ኀጢአት ያላወቀውን እርሱን (ክርስቶስን) ስለ እኛ ኃጢአትአደረገው» (2ቆሮ. 521)፡፡ ይህ አስደናቂ የልውውጥ ሥራ ኃጢአተኞቹን እኛን ጻድቅ፣ ጻድቁን ጌታ ደግሞኃጥእ ያሰኘ መለኮታዊ ሥራ ነው፡፡ በዚህ ሥራ አማካኝነት (በእርሱ በኩል) ሁላችን እንደ ጻድቅ ወደእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ድፍረት አግኝተናል (ዕብ. 1019-20 ኤፌ. 213 216)፡፡ እንግዲህከአዳም ዘር የሆንን ሁላችን ማንንም ከማንም ሳይለይ ኃጢአተኞችና በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብየማንችል ብንሆንም በክርስቶስ በተደረገልን ቤዛነት፣ በእርሱ ፍጹም ሥራ በኩል ወደ እግዚአብሔርመቅረብም ሆነ መጸለይ እንችላለን፡፡ ወደ እግዚአብሔር የመቅረቢያ ድፍረታችን የለበስነው የኢየሱስ ጽድቅእንጂ የእኛ መልካም ነገር አይደለም፡፡ በራሴ መልካም ሥራ በኩል ወይም ከእኔ በተሻሉ በምላቸው ሌሎችሰዎች በኩል ወደ እግዚአብሔር መድረስ እችላለሁ የምትል ነፍስ ራሷን ከቅዱሱ ከኢየሱስ ጋር እያወዳደረችመሆኗን ልትገነዘብና ንስሀ ልትገባ ይገባታል፡፡ ስለዚህ ከእርሱ ሌላ ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብባቸውሌሎች መካከለኞች፣ ሌሎች አማላጆች ፈጽሞ የሉንም፡፡ ወደእግዚአብሔር የምንደርስበት ሌላ መንገድ ራሱ ክርስቶስ በወንጌል ነግሮን ሳለ እኛ ግን ሌሎች ሰዎች ያደርሱናል ማለት  ክርስቶስን ተሳስተሃል ማለት ይሆናል።«ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም» ዮሐ146

7 ልክ እንደ ብሉይ ኪዳን በሐዲስ ኪዳንም ለክህነት የተመረጡ ጥቂት ግለሰቦች አሉ?

በሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያንን የመምራት፣ የማስተዳደርና ምእመኑን የመመገብ ኃላፊነት የተሰጣቸውአማኞች ጳጳሳት፣ ኤጲስ ቆጶሳት፣ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች፣ ዲያቆናት (ሐዋ. 2028 1423 ፊሊ. 11) ተብለው ስያሜን ከማግኘት ውጪ ከምእመናን በተለየ መልኩ ካህን ወይም ሊቀ ካህን የሚል ሹመትአልተሰጣቸውም፡፡ ይህንን የሚያሳይ አንድም ገጽ የለም። መጽሐፉ እንደሚል የሐዲስ ኪዳን ብቸኛ ሊቀ ካህንኢየሱስ ብቻ ሲሆን (ዕብ. 217 96-11) በእርሱ ያመኑ ምእመናን ሁሉ ዘር፣ ቀለም፣ ጾታ፣ የትምህርትደረጃ ሳይለይ የእርሱ ካህናት ተብለዋል (1ጴጥ. 25-9 ራዕ. 510)፡፡  አሁንም የብሉይ ኪዳን ክህነት አለብለው የሚያስቡ ካሉ እንግዳው ይህም ክህነት ቢሆን ለአሮን ቤተሰብ ብቻ የተሰጠ መሆኑን ማስታወስይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ ያለ ክህነት እግዚአብሔር የማያውቀው ክህነት አይደለም፡፡ ቃሉ የሚናገረውን አለመበቀል መብት ቢሆንም የሰዎች አለመቀበል ግን የወንጌልን ቃል እውነተኛነት አይቀይረውም። «እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ» 1 ጴጥ 25

ሊቀ ካህናት ክርስቶስ ኢየሱስ በመሐላ የተሾመ ዘላለማዊ ሊቀካህን ነው ካልን ሌላ በመሃላ የሚሾም፤ ዘላለማዊ ሊቀ ካህን ከየት ይመጣል?

ማጠቃለያና የንስሃ ጥሪ፡-

ወዳጆቼ ሆይ የኢየሱስ መካከለኛነት አንድ ሰው ለሌላው ሰው ጸሎት የማድረስ አገልግሎት አይነት ብቻ ነውን? «ፈጽሞ! ምልጃ ስለ ሌላው ሰው መሞትንም የሚያጠቃልል ነው እንጂ´ የሚሉኝ ከሆነ እንግዲያው ከኢየሱስውጪ ስለ ሰው የሞተ ማን ነው? ስለ ምልጃ ስናወራ ምሉእ ስለሆነው ስለ ኢየሱስ መሥዋዕት መሆን፣መጸለይና ምትክ መሆን እያወራን መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ከዚህ ምሉእ አገልግሎትውስጥ ስለ ሌሎች መጸለይ የምትለዋን ብቻ በማውጣት ምልጃን ለመተርጎም ስለሚሞክሩ የተሳሳተ ማጠቃለያላይ ይደርሳሉ፡፡

የጸሎት ምልጃን በተመለከተ ማንም ሰው ለማንም መጸለይ ይችላል (ያዕ. 514 ቆላ. 42-4 12)፡፡ እርግጥነው እግዚአብሔር የሚፈሩትን ሰዎች ጸሎት ይሰማል ፡፡ ይህ ማለት ግን የእግዚአብሔር ጆሮዎች መቁጠር ለምንችላቸውና  እኛ ለምናውቃቸው ቅዱሳን ብቻ የተከፈተ ነው ማለት አይደለም፡፡ ማናችንም ብንሆንእግዚአብሔርን በመውደድና በእምነት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ጸሎታችንን በኢየሱስ ስም ብንጸልይእግዚአብሔር የሁላችንን ጸሎት ያለ ልዩነት ይሰማል፡፡ የማናችንም ሥራ በእርሱ ፊት ብቃትን ሊሰጠንአይችልም። ከክርስቶስ ውጪ ስንታይ እንኳን ዐመጻችን ፤ጽድቃችንም ቢሆን የመርገም ጨርቅ ነው፡፡እንግዲያውስ ሁላችንም፣ ገና ዛሬ እግዚአብሔርን ያወቀ አዲስ ክርስቲያን ቢሆን፣ የሰነበተ ዲያቆን፣ ጀማሪቄስ ይሁን፣ የበቃ ጳጳስ፣ የአንድ አመት መጋቢ ይሁን የቆየ ሽማግሌ፣  በእግዚአብሔር ፊት ለመጸለይናወደ ፊቱ ለመቅረብ የምንችለው በክርስቶስ ሥራ ብቻ ነው፡፡

ይህን ለራሳችንም ሆነ ለሌላ ሰው የምናደርሰው ጸሎት፣ ጸሎትን ወደ ሚሰማና ወደ ሚመልስ እግዚአብሔርሊደርስ የሚችለው በአንድ መንገድ ብቻ ነው (ዮሐ. 146)፡፡ ሊሎች አማራጮች የሉንም፤ አያስፈልጉንምም፡፡ይህም መንገድ ኢየሱስ ነው፡፡ በስሙ (በኢየሱስ ሰም) የምንለምነውን ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚሰማናእንደሚመልስ ተጽፏል (ዮሐ. 1413-14 1623-24)፡፡

«እኔም እላችኋለሁ። ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።
የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልግም ያገኛል፥ መዝጊያውንም ለሚያንኳኳው ይከፈትለታል» ሉቃ 119-10

ይህ ሁኔታ በአገራችን የትውፊት መዛግብት ላይ ሳይቀር እንግዳ አለመሆኑን ከድርሳነ ማኅየዊ የተወሰደውንየሚከተለውን ክፍል ይመልከቱ «አቤቱ ጌታችን ተቀዳሚ ተከታይ ስለ ሌለው ስለ ልጅህ ስለ ወዳጅህ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ስለ አማኑኤል ብለህ ይቅርታህን ከእኛ አታርቅ፤ መሀላህንም አታፍርስ´ (ድርሳነ ማኅየዊ፣ምዕራፍ 1 ቁጥር 13 ገጽ 5)፡፡

በመጨረሻም፣ በዚህ ጽሁፍ የቀረቡትን አሳቦች በመጠቅለል መቋጫ እናበጅና እንለያይ፡፡ የሰው ዘርከውድቀት በኋላ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሆኖ መቅረብ ባለመቻሉ፣ ክርስቶስ ለዚህ ተስፋ ቢስ የሰው ዘርወኪል በመሆንና በመታዘዝ ጻድቅ ሕይወቱን በሰው ልጅ ፈንታ ለእግዚአብሔር አቀረበ፡፡ የሰው ልጅሊሸከማት ያልቻለውን የኃጢአት ቅጣት በእርሱ ፈንታ በመሸከም የኃጢአት ስርየትን አስገኘለት፡፡ ከዚህምየተነሳ ሰው በእግዚአብሔር ፊት እንደ ጻድቅ ተቆጠረ፤ ክርስቶስ ግን እንደ ኃጢአተኛ ተቆጠረ፡፡ ሐዋሪያውይህን ታላቅና አስደናቂ ልውውጥ «እኛ በእርሱ (በክርስቶስ) ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድኃጢአት ያላወቀውን እርሱን (ክርስቶስን) ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው´ በማለት ገልጦታል (2ቆሮ. 521)፡፡በአንድ በኩል ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ጋር እርቅና ሰላም የሚኖረው ክርስቶስ በእርሱ ስፍራ የሕግንቅጣትና እርግማን በመሸከሙ ሲሆን (ገላ. 313) በሌላ በኩል ደግሞ በክርስቶስ ጽድቅ ውስጥ በመቆሙ ነው(1ቆሮ. 130-31)፡፡ አንዳንዶች የክርስቶስን የማዳን ስራ ለመሸርሸር ሲፈልጉ ቶሎ ብለው ቅዱሳን ተብለው ከሚጠሩ ሰዎች ማንነት ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራሉ። ሰዎች የክርስቶስን ምትክ አልባነት ሲነግሯቸው ቅዱሳንን በክርስቶስ ቦታ በመተካት የመዳን ሊቀ ካህናት እንደሆኑ ለመስበክ ይፈልጋሉ። ቅዱሳን በማስተማር፤ በመስበክ፤ በመምከርና  በመገሰጽ እንዲሁም ክርስቲያናዊ ፈለጋቸው ወደ እምነታችን ጥንካሬ ሊያመጣን ካልሆነ በስተቀር የክርስቶስን የማዳን ሥራ ሊተኩ አይችሉም። ይህንን የሚልም ማንም ቅዱስ የለም።

ቅዱስ ጳውሎስ ከመሰከረው እውነት ውጪ የሚናገር ማን ይሆን? እኛ ወይስ ቅዱሳኖቹ?  ቅዱስ ሰው የወንጌል አገልግሎቱ ሰው ሁሉ በክርስቶስ ፍጹም እንዲሆን እየገሰጸ፤ እያስተማረ፤ በጥበብ እየሰበከ የሚያቀርብ ማለት እንጂ ራሱ አዳኝ የሆነ ማለት አይደለም።

«እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው» ቆላስ 128

እናም የክርስቶስ ሞት የእኛ ምትክ መሆኑ የሚያስገነዝበን ነገር ቢኖር እርሱ በእኛ ምትክ መሞቱን፣ የእኛንህማም መታመሙን፣ የእኛን በደል መሸከሙን (ኢሳይያስ 53) ነው፡፡ ኢየሱስ ስለ እኛ ቆሰለ፣ ስለ እኛ ተዋደረየማይገባውን ያውም የመስቀል ሞት ለመሞት የታዘዘ ሆነ (ፊሊ. 28)፡፡ ጤነኛ የሆነ አእምሮ ሁሉ የህንካነበበ በኋላ «ግን ለምን ብሎ ሊጠይቅ ይገባዋል፡፡ መልሱም ሊያድነን፣ ከፈጣሪያችን ጋር ሊያስታርቀን፣ቅዱስ ሕዝብ ሊያደርገን፣ ቀድሞ ወደ ነበርንበቱ ክብር መልሶ ሊያመጣን የሚል ይሆናል፡፡ ይህ የመዳንመንገድ ብቸኛው የመዳን መንገድ ነው (ዮሐ. 14 6) ከዚህ የተሻለ የመዳን መንገድ ለመፈለግ ማሰብምሆነ ማድረግ ከእግዚአብሔር ይልቅ ጥበበኛ ነኝ ከሚል ትእቢተኛ ልብ የሚመነጭ ከመሆኑ ባሻገር የኢየሱስንሞት ከንቱ ማድረግ ይሆናል (ገላ. 221) ደሙንም ማክፋፋት ይሆናል ፡፡

ኢየሱስ ይህን ሁሉ ከፈጸመልኝ የእኔ ድርሻ  ምንድር ነው? አንተን ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ የሚቀርሌላ መሥዋዕት እንደሌለ እወቅ፣ የኢየሱስ መሥዋዕት ፍጹም፣ ንጹህ፣ ቅዱስ፣ በቂ በመሆኑ አንተን ለማዳንየሚችል እንደሆነ እመን፡፡ ይህንን የማዳን መንገድ ሙሉ ለማድረግ ከእምነት ውጪ ከአንተ ምንምእንደማይጠበቅ እመን፡፡ ከዚህ ውጪ ምንም ነገር ለማድረግ በምትንቀሳቀስበት ቅጽበት የኢየሱስ የመስቀልሥራ ጎዶሎና ያለእኔ እርዳታ በራሱ ሊቆም የማይችል ደካማ ሥራ ነው እያልክ እንደሆነ አትዘንጋ፡፡ «ለመዳን(ከእግዚአብሔር ጋር ለመታረቅ) ከማመን ውጪ ከኔ የሚጠበቅ እኔ የማዋጣው ነገር የለም ነው የምትለኝየሚሉኝ ከሆነ፣ እኔ ደግሞ በተራዬ አንድ ጥያቄ እንድጠይቅዎ ይፍቀዱልኝ፡- «ከእግዚአብሔር ጋር ለመታረቅእርስዎ ሊያደርጉት የሚችሉት አንዳች ነገር ቢኖር ኖሮ እግዚአብሔር አብ አንድያ ልጁን ለዚህ ሥቃይአሳልፎ የሚሰጠው ይምስልዎታል?

እኔ ግን እላለሁ፤ እመን ትድናለህ? ከዳንክ ደግሞ ተመልሰህ እነበርክበት እንዳትገባ እምነትህን በስራ አሳይ! ክርስቲያናዊ ሕይወት ማለት ነው።

ጸሎት መጸለይ፣ ጦም መጦም፣ ችግረኛ መርዳት፣ በቅድስና ለመኖር ራስን መግዛትና የመሳሰሉት ነገሮች ሁሉ ከአምላኩ ጋር ከተታረቀና የዘላለም ሕይወት እንዳለው ከሚያምን አማኝ ሁሉ የሚጠበቅ ብቻ ሳይሆን በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት እያንዳንዱ ሰው ሽልማት የሚቀበልበት መመዘኛዎች ናቸውና የሚናቁ ነገሮች አይደሉም (ራዕ. 2212)፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ ነገሮች ለድኅነት በአንድ ላይ ተከምረው እንደተራራ ቢከመሩ ክርስቶስ ለእርስዎ ካደረገልዎ የመስቀል ሥራ አንጻር የኢምንት መጠን እንኳ ዋጋ የሚቸራቸው አይደሉም፤ፈጽሞም ከእግዚአብሔር ጋር ሊያስታርቁ አይችሉም፡፡ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔርምፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከእርስዎ ጋር ይሁን፤ አሜን፡፡  (ጥናታዊ ፅሁፍ በወንድሞች)